Breaking News
Home / Amharic / አፄ ምኒልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት ዘመናዊ ግብአቶች !

አፄ ምኒልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ ያስገቡት ዘመናዊ ግብአቶች !

1882 ዓ.ም. ———————ስልክ
1885 ዓ.ም. ———————ወፍጮ
1886 ዓ.ም. ———————ፖስታ
1886 ዓ.ም. ———————ባህር ዛፍ
1886 ዓ.ም. ———————ገንዘብ
1886 ዓ.ም. ———————የውሃ ቧንቧ
1887 ዓ.ም. ———————ጫማ
1887 ዓ.ም. ———————ድር
1887 ዓ.ም. ————–የሙዚቃ ት/ቤት
1887 ዓ.ም. ————-የፅህፈት መኪና
1889 ዓ.ም. ———————ኤሌክትሪክ
1889 ዓ.ም. ————ዘመናዊ ህክምና
1889 ዓ.ም. ———————ሲኒማ
1889 ዓ.ም. ————የሙዚቃ ሸክላ
1889 ዓ.ም. ————ቀይ መስቀል
1890 ዓ.ም. ———————ሆስፒታል
1893 ዓ.ም. ———————ባቡር
1893 ዓ.ም. ———————ብስክሌት
1896 ዓ.ም. ———————መንገድ
1897 ዓ.ም. ———————ፍል ውሃ
1898 ዓ.ም. ———————ባንክ
1898 ዓ.ም. ———————ሆቴል
1898 ዓ.ም. ———————ማተሚያ
1898 ዓ.ም. ———————ላስቲክ
1899 ዓ.ም. ————-አራዊት ጥበቃ
1899 ዓ.ም. ————የጥይት ፋብሪካ
1900 ዓ.ም. ———————ጋዜጣ
1900 ዓ.ም. ———————አውቶሞቢል
1900 ዓ.ም. ———-የሚኒስትሮች ሹመት
1901 ዓ.ም. ————–ፖሊስ ሰራዊት
1904 ዓ.ም. ———–የመድሃኒት መሸጫ ሱቆች
 
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደሀገራችን ያስገቡት ታላቁ አባታችን እምዬ ሚኒሊክ ናቸው!!!

እኔ እንደገባኝ ከሆነ ። ጤፍ ገዝተህ ልታስፈጭ ወደ ወፍጮ ቤት ስትሄድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወፍጮ ያስገባው ምንሊክ መሆኑ ትዝ ይልህና ትደሰታለህ !

ጤፍ ማስፈጨቱን ትተህ ምግብ ልትበላ ሆቴል ስትገባ የመጀመሪያውን ሆቴል የከፈተውም ምንሊክ መሆኑ ትዝ ይልህል።

ተናደህ ጓደኛህ ጋ ልትደውል ስልክህን ስታወጣ ስልክን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስገባው ምንሊክ መሆኑ ትዝ ይልሃል።

በንዴት ጨጓራህ ተልጦ ውሀ ልትጠጣ ቧንቧ ስትከፍት የቧንቧ ውሀን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስገባው ምንሊክ መሆኑ ትውስ ይልህና በጨጓራህ ላይ ጋንግሪን ይይዘሀል።

ማስታገሻ ልትገዛ ፋርማሲ ስትሄ የመጀመሪያውን ፋርማሲ የከፈተው ምንሊክ መሆኑን ታስታውስና አየር ለመቀየር ወደ ሌላ ሀገር ልትሄድ ትወስናለህ።

ሻንጣህን ይዘህ አስፓልት ዳር ቆመህ መኪና እየጠበቅህ እያለ መኪና ያስገባው ምንሊክ መሆኑ ድንገት ትውስ ይልህና ራስህን ታዝናናለህ።

ባቡር ጣቢያ ደርሰህ ትኬት ልትቆርጥ ስትል ባቡርንም ያስመጣው ምንሊክ መሆኑን ይነገሩህና መሀል ከተማ ላይ ኡ ኡ ኡ ብለህ ታወራለህ።

የጮህክበት ጉሮሮህ ድምፅህ ተዘግቶ ባህርዛፍ ልታጠን ብለህ ባህር ዛፍ ቅጠል ስትፈልግ ባህርዛፍንም ከአውስትራሊያ ያስመጣው ምንሊክ መሆኑ ትዝ ይልህና ድጋሜ ታስባለህ።

በቃ ልረጋጋ ብለህ ፊልም ለማየት ሲኒማ ስትሄድ የመጀመሪያውን ሲኒማ የከፈተው ምንሊክ መሆኑን ይነግሩህና ፌንት በልተህ የተወሰነ ደቂቃ ራስህን ትስታለህ።

ነገር አለሙ ዞሮብህ በሙዚቃ ራስህን ልታፍታታ ዘፈን ስትከፍት የመጀመሪያውን የሙዚቃ መቅጃ መሳሪያ ምንሊክ እንዳስገባው ያነበብከው ትዝ ይልህና እመቤቴ ድረሺልኝ ብለህ ራስህ ልታጠፋ ጥይት ልትገዛ ትሄዳለህ።

ጥይት ሻጭ ጋ ሄደህ ስትደራደር ለመጀመሪያ ጊዜ የጥይት ፋብሪካን የከፈተው ምንሊክ መሆኑን ሲነግርህ ሊፈነዳ የደረሰ ጭንቅላትህን ይዘህ ድጋሜ ትሮጣለህ።

የመጨረሻው አማራጭ የስሙኒ ገመድ ትገዛና ለመጀመሪያ ጊዜ ጫማን ያስገባው ምንሊክ መሆኑን አስታውሰህ ጫማህን ታወልቅና ራስህን ሲጥ ታደርጋለህ።

ወዳጄ ከምንሊክ መንፈስ ከማምለጥ ራስን ማጥፋት ይቀላል። የምንሊክ አምላክ በያላችሁበት ይጠብቃችሁ። ዳጊ ነኝ ከፒያሳ ምንሊክ አደባባይ :))

ሼር ሼር ሼር

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.