Breaking News
Home / Amharic / አዲስ አበባ ደህና ሁኚ ! ዝም ብላችሁ አብይን የምትደግፉ ቦሀላ ለቅሶ እንዳይመጣ ያልነው ለዚህ ነበር ! አዲስ አበባ ተወሰደች:: ፍንፍኔ መጣች ! ተደራጁ ብለን ነበር !

አዲስ አበባ ደህና ሁኚ ! ዝም ብላችሁ አብይን የምትደግፉ ቦሀላ ለቅሶ እንዳይመጣ ያልነው ለዚህ ነበር ! አዲስ አበባ ተወሰደች:: ፍንፍኔ መጣች ! ተደራጁ ብለን ነበር !

OBN ግንቦት 17,2013-
የፊንፊኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በይፋ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኩመላ ቡሳ የፊንፊኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የኦሮሚያ ክልል መንግስት ፍርድ ቤቶች አደረጃጀት ሥልጣን እና ተግባር እንደገና ለመወሰን የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 216/2011ን መሠረት በማድረግ በይፋ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ለOBN ተናግረዋል።

የፊንፊኔ ከተማ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልሉ መንግስት መቀመጫ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ የክልሉን መንግስት የተመለከቱ ወንጀል ነክና የፍትሃ ብሔር ጉዳዮች በዚህ ፍርድ ቤት ይታያሉ ብለዋል።
 
በፊንፊኔ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችም ሕገ መንግስታዊ መብታቸዉን በመጠቀም በዚህ ፍርድ ቤት በቋንቋቸዉ የመዳኘትና ተደራሽ የሆነ የፍትህ አገልግሎት የማግኘት መብትም ያገኛሉ ብለዋል።

በፊንፊኔ ከተማ የሚኖሩ የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ከአሁን በፊት ፍትህ ለማግኘትና በቋንቋቸዉ ለመዳኘት ገንዘባቸዉንና ጊዜአቸዉን በማባከን በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ወደሚገኙ ፍርድ ቤቶች ሲመላለሱ እንደ ነበር የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ ይህ ፍርድ ቤት በይፋ ተከፍቶ ሥራ መጀመሩ ግን ይህንን እንግልትና ዉጣ ዉረድ ያስቀራል ብለዋል።
በፍርድ ቤቱ የአገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት: የኦሮሚያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ: የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
የፊንፊኔ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በይፋ ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ የኦሮሞ ሕዝብ ከፊንፊኔ ከተማ ማግኘት የሚገባዉን ሕገ መንግስታዊ መብት ከማረጋገጡም በላይ የኦሮሞን ሕዝብ ለረጅም አመታት ሲጠይቅ የነበረዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ የሚመልስ መሆኑንም በፍርድ ቤቱ ስራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙ የክልሉ ከፍተኛ የፍትህ ተቋማት አመራሮች ተናግረዋል።
 
ወንድማገኝ አሰፋ
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.