Breaking News
Home / Amharic / አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከስራቸው ተባረሩ:: አብይ አህመድ ዮሐንስ ቧያለውን የባሰ አጀገነው !

አቶ ዮሐንስ ቧያለው ከስራቸው ተባረሩ:: አብይ አህመድ ዮሐንስ ቧያለውን የባሰ አጀገነው !

አቶ ዮሐንስ ቧያለው እንኳን ደስ አለህ !!
********
ገፊው ከበዛው የአማራ ህዝብ ጎን የመቆም መልካም ዕድል
********
ይህ በአማራ ጠሉ አገዛዝ ስርዓት ውስጥ የአማራ ህዝብ ሰቆቃ ይቁም ለሚል፣ ከአማራ ህዝብ ጎን ለቆመ ሰው የተዘጋጀ የመጀመሪያው ጥፊ ነው። ቀጣዩ ደግሞ ከጥፊ የባሰም ሊሆን ይችላል። ሆኖም እንደ ደመቀ መኮንን፣ብናልፍ አንዱአለም፣ተመስገን ጥሩነህ ሆነው ከሚያገኙት ማዕረግ ይልቅ እንደ ዮሃንስ ቧያለው ሆነው የሚያገኙት ጥፊ በስንት ጣዕሙ !
በነገራችን ላይ አቶ ዮሃንስ ለአብይ ቀርቶ ለመለስ ዜናዊ የማይመለሱ ልበሙሉ ሰው ናቸው። አቶ ዮሃንስ ገፊው ከበዛው የአማራ ህዝብ ጎን የመቆምን መልካም ዕድል መርጠዋልና ደስ ሊልወት ይገባል !!!
አብይ ሲሾም እና ሲሽር ምን ማለት እንደሆነ የቆሙለት የአማራ ህዝብ አሳምሮ ያውቃል፤ ከጎኑ በመቆምዎ የከፈሉትን ዋጋ ይረሳ ዘንድ የአማራ ህዝብ ውለታ ቢስ አይደለም! ፤ የቆሙለት ህዝብ ሁሌ ከጎንዎት ነው….
ይህ ደብዳቤ አባራሪው እንዳሰበው መቃለያዎት ሳይሆን በቁርጥ ቀን ከአማራ ህዝብ ጋር የመቆምዎት መልካም ስም የታተመበት የክብር ልብስዎት ነው! የአማራህዝብ ያመሰግንዎታል 🙏🙏🙏
 
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.