Breaking News
Home / Amharic / አብይ 7 የወደብ አማራጮች አለው። አብይ ለምን ሀርጌሳ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ አለ?

አብይ 7 የወደብ አማራጮች አለው። አብይ ለምን ሀርጌሳ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ አለ?

አብይ ሴረኛነቱን ሁሉም ተረድቷል። የአብይ አህመድ ቀጣይ ሤራ? ሶማሌ ላንድ ወይንም ሞት ለኦሮምያ ምስረታ መንገድ ጠረጋ ይሆን?

አብይ 7 የወደብ አማራጮች አለው። አብይ ለምን ሀርጌሳ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ አለ? አብይ NPD በሚባል የአይምሮ ህመም የተጠቃ ሰው ነው።  ይህ በሽታ ጨርቅ የሚያስጥል ድንጋይ የሚያስወረውር በሽታ አይደለም። ይህ በሽታ በአለም ላይ የተዋጣለት ውሸታም፤ አታላይ፤ እራስ ወዳድና እራስን ከፍ አድርጎ የሚያሳይ በሽታ ነው።  ስለዚህ ለአብይ የማታላለል እንጂ የመጸጸት ህሊና አልፈጠረበትም።

1ኛ፡ ለምሳሌ የኤርትራ አሰብ ወደብ በነጻ ተጠቀም ተብሎ በኤርትራ ተሰጥቶት ነበር።  ይህ ወደብ ኢትዮጵያ ከዜሮ አንስታ በአጼ ኃይለስላሴና በመንግስቱ ግዜ ለመሀል ሀገር እንዲጠቅም ብላ ይሳደገችው ወደብ ነው።  ከአሁኑ የኢትዮጵያ ወሰን 70 ኪሎሜትር ገደማ ሲሆን የሀርጌሳ ወደብ ሰግሞ 780 ኪሎ ሜትር በሱማሌ ግዘት ውስጥ ተጉዞ ነው። ይህ ማለት ኢትዮጵያ በአጭር መንገድ ገቢና ወጪን በደረቅ ወደብ በኢትዮጵያ ወደብ በመግዘት ፈጣን እና ዋጋ ቆጣቢ የባህር አገልግሎት መስጠት ያስችላል። 

ወደ ጅቡቲ የተዘረጋው የባቡርና የመኪና መንገድ ጋር ለማገናኘት ብዙ ወጪ አይጠይቅም። አሰብ ኢትዮጵያ መጠቀም ስታቆም  ለኤርትራም ብዙ ጥቅም የሚሰጥ ወደብ አልሆነም። ብዙ መጋዘኖች ብዙ ሆቴሎች ብዙ ተቋማት ያሉባትና ያለ ብዙ ወጪ ለኢትዮጵያም ለኤርትራም ጥቅም ሊያመጣ የሚችል ወደብ ነው።  ይሄንን ወደብ ለመጠቀም መንገድ መሰራት ተጀምሯል ብሎ አብይ ኤርትራንም ኢትዮጵያንም አታሏል።  

ምናልባትም ኢትዮጵያ የባህር ኃይልም ላቋቋምና የኤርትራንና የኢትዮጵያን የጋራ ጥቅም ሊያስከብር የሚችልና የሚተጋገዝ የባህር ሀይል እንፍጠር ብላ ኢትዮጵያ ብትጠይቅ ኤርትራ እንቢ አትልም ነበር። ኢሳያስ አፈወርቄ ሰውን የሚያምን ባህርይ አልፈጠረበትም። ይሁንና አብይን አንዳመነውና በአብይ እንደተታለለ በማንም ተታሎ አያውቅም። ታድያ ለምን አብይ ይሄንን ወደብ አልፈለገም?  ለምንስ አንድ መርከብ አንኳን አሰብ ላይ እንዲያራግፍ ፈለገ?

ከኤርትራ ጋር ፍቅር ጀምሬያለሁ ብሎ ቆሎና የቡና ቁርስ ካላጎረስኩ ብሎ ቪዲዮ ለቆ ነው የኖቤል ሽልማት የተሰጥው።  ተዋዶ ተፋቅሮ የኤርትራን ጦር ኢሳያስን ዋሽቶ፤ አታሎ፤ ጋብዞ አምጥቶ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲዋጉ ከዛም አልፎ ህይወታቸውን እስከሚሰጡ ድረስ አምነውት ነበር።  ታድያ ለምን አብይ ይሄንን ወደብ ለመጠቀም አልፈለገም? ምክንያቱን በዝርዝር እንመለስበታለን። ግን በአጭሩ አብይ ሴማዊ ብሎ በጠላት የመደበውና ሊያጠፋው ከመደበው እና ዝርያዎች አንደኛው ኤርትራውያን መሆናቸው ነው።

2ኛ፡ ኛ ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ቀርቶ ለ9 ሐገራት (ፈረሣይ፡ አሜሪካ፤ ጀርመን፤ ቻይና፤ ጃፓም፡ ስፔን፡ ጣልያን፤ ዮናይትድ ኪንግደም እና ሳውዲ አረብያ) መሬት አከራይታ የባህር ሀይላቸውን አስፍረዋል። እስቲ  ጠጋ ጠጋ በሉና አንዱ ቦታ ወሽቅ ልበል ኢትዮጵያ ብትል ጅቡቲ ከጀርመንና ከጃፓን መቼም ኢትዮጵያ ትቀርባታለችና እንቢ አትልም ነበር። 

3ኛ ጅቡት ብዙ ገቢዋ ከወታደራዊ ካንፕ ኪራይ ነው። ባለፈውም እራሷ ፈራ ተባ እያለች የታጁራን ወደብ ልሰጥሽ ብላ ጠይቃ የኢትዮጵያ መንግስት እውቅና እንኳን እውቅና ስላልሰጥቻት ወደ ኋላ አፈግፍጋለች።

 4ኛ፡  ኬንያ ደቡብ ሱዳንና ኢትዮጵያ አንድ ላይ ሆነው የላሙ ኮሪደርና ወደብ ማልማት ጀምረው ነበር። ስለዚህም የኦፒዲኦ ሰዎች ሲያንሱም አይታዩም።

5ኛ፡ የሀርጌሳም ወደብ ከዱባይ ጋር በአክሲዎን ገብታ 19% በመቶ ገዝታ ነበር። አብይ ይሄንን ያለቀ ጉዳይ የአክሲዮ ባለመክፋሉ  ከስምነቱ ፈርሷል። 

6ኛ፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ የጅቡት ወደብ በስፋት ለመጠቀም የ750 ኪሎ ሜትር ባቡር መስመር በ4 ቢሊዩን ዶላር ብድር ተገንብቶ  ስራ ላይ ውሎ ነበር።  ይህ ባቡር በኦሮምያ ስለሚያቋርጥ ሰዉ በባቡሩ ሀዲድ ላይ ከብትና ግመል እንዲያስግጥ ስለተፈቀደ።  ባቡሩ 30 ኪሎ ሜትር በሰአት ተወስኗል። ስለዚህ ከጅቡቲ አዲስ አበባ በ48 ሰአት ነው የሚገባው። ዶሮዋ የንጉስ ዶሮ ነኝና እሽ አትበሉኝ እንሳለችው የኦሮሚያ ፍየሎች ባቡሩ ቆሞ ያሳልፋል እንጂ ፈጠን ብላችሁ ፍየላችሁን ንዱ የሚል ኢትዮጵያዊ ባለ ስልጣን የለም። ባቡሩም የሰው ማጓጓዣና መተኛው ለኦፒዲኦ ካድሬዎች ህገወጥ ኮንትሮባንድ ማጓጓዣና ጫት መቃሚያ አድርጎት አልጋው ሁሉ በቱሀን ተወሮ ማንም ደፍሮ አይሳፈርበተም። የኦፒዲኦ የኮንትሮባንድ ነጋዴ ካልሆነ በስተቀር ምንም ደፍሮ በባቡር ተሳፍሮ ኦሮምያን የሚያቋርጥ ኢትዮጵያዊ፣ ጅቡቲያዊ ወይንም የሌላ ሀገር ዜጋ የለም።

ታከለ ኡማ የአዲስ አበባን መሬት ቸብችቦ፣ ከዛ ደግሞ የመአድን ፈቃድን ቸብችቦ አሜሪካ ቪላ ገዝቶ ዶላር አሽትቶ ኑሮ ጀምሮ ነበር። የሱ የትምህርት ደረጃና እና የሚኒስቴርነት የስራ ልምድ እንደነ ዶ/ር ካሳ ተክለ ብርሀን ኡበር ታክሲ ከመንዳት ሌላ የስራ እድል አልፈጠረለትም። ስለዚህ ተደራድሮ ተመልሶ የባቡሩን የኮንትሮባንድ ንግድ ተሰጥቶታል። 

ባጫ ደበሌና የሺመልስ ኡብዲሳ የሞያሌን የወርቅ፣ የመአድንና ንድዱን መስመር ስለተቆጣጠሩት ታከለ ኡማ ደግሞ የራሱን የወንጀልና የህገወጥ ንግድ ለማካሄድ እንዲቻለው ባቡሩ ይሰጠኝ ብሎ ድርሻውን ወስዷል።

7ኛ አትዮጵያ የሞንባሳን ከኬያ የሱዳንን ወደቦች ለመጠቀም ትችላለች። ለረጅም ግዜ ነዳጅ ከሱዳን ወደብ በመተማ በኩል ሲገባ የቆየው። 

እነዚህ ሁሉ አማራጮች እያሉ ታድያ አብይ አህመድ አሊ ለምን ሀርጌሳ ወይም ሞት ብሎ ተነሳ?  

ታድያ ይሄንን ለምን አመጣሀው ካላችሁ። አብይ አህመድ  የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ በተቀሰቀሰ ጊዜ የፕሮቴስታንት የሆኑ የኦፒዲኦ ባለስልጣኖችን ሰብስቦ ንግግር አድርጎ ነበር። አንድም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆነ ኦሮሞ ኦፒዲኦም አልተጋበዘም።እነሱን አብይ በአንድ ጣሳ ውሀ አጥምቆ ሃይማኖታቸውን ዘረኝነት አድርጎ ካላስቀየራቸው ሰውን በአምሳሉና በመልኩ አንድ አድርጎ ላስገኘ የሰማይና የምድር ፈጣሪን ለሚያስከትል እምነት አይበቁም። እምነታቸው ስስትና ሆድ ነው፤ አምልኮ አፈጻጸማቸው ሀሰተኝነትና ደም ማፍሰስ ።

በዚህ ውይይት ላይ አብይ ኢትዮጵያን በሁለት ይከፍላል። ከላይ ያለውን ሴማቲክ ይልና ሌላውን ኩሻቲክ ይላል። ሴምና ኩሽ የአንድ የእናት አባት ልጆች ቢሆኑም አብይ ሴም የኩሽ ህዝብ  ጠላትና ነው ብሎ ይመድባል። ሴማውያን መጥተው ከተማቻችንን ተቆጣጥረው፣ ለ150 ዓመታት ጨቁነውናል። አሁንም የኦርቶዶክስ ተቃውሞ ሲነሳ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም አወገዘን።  ስለዚህ ኤርትራን፣ ትግራይን እና አማራን እስር በእርሳቸው በሁመራ፣ ጠገዴና በራያ ጦርነት ካላጫረስናቸውና በማያባራ ጦርነት ካልከፈትንባቸው ተመልሰው መጥተው ስልጣን ይቀሙናል የሚል ነበር። ስለዚህ የአብይ አህመድ ፕላን አንድ ብሎ የወሰነው ኢትዮጵያን ለመግዛት ሶስቱን ማፋጀትና ማዳከም ነው የሚል ነበር።

ይህንን የተረዳ ስው አብይ በነጻ የተሰጠውን የአሰብ ወደብ አልጠቀምም ለንን እንዳለ ይረዳል። አብይ አህመድ አሊ ይህ ኮሪዶር ከተከፈተ ዐመሓራው፣ ትግሬው፣ ኤርትራውያን በኢኮኖሚ ይገናኛል፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ይነቃቃል ስለዚህ እንዲጡፋና የተፈረደበት ጠላት ተጠቃሚ ሊሆን ነው። ስለዚህ አብይ አብይ ለኢሳያስ የቡና ቁርስ እያቀረበ ኢትዮጵያ የአሰብንና የምጽዋን ወደብ መጠቀምን ከጅምሮ አልፈለገውም። 

ለብዙ ሰዎች አብይ ህይወቱን ያዳነውን ኢሳያስ አፈወርቄና የኤርትራን ጦር በአንድ ግዜ ጠላት አደረገ ብሎ ለጠየቀ መልሱ ኤርትራ ምንም ያህል ትርዳ አብይ ጠላት ብሎ ከፈረጀው የሴም ወገን ናቸው ብሎ ስላሰበ ብቻ ነው። አብይ በሽታው ያጎናጸፈው የማታለል ችሎታውን ተጠቅሞ ኢሳያስን ስቦ አስገብቶ አስጨርሶ አዳክሞ ተጠቅሞበት ጣለው። 

የአብይ አህመድ አሊ ሁለተኛ ፕላን ብሎ ለኦፒዲኦ ፕሮቴስታንት ባለስልጣን ያቀረበው ኢትዮጵያን መግዛት ካልቻልን፡ ኦሮሞ በመላው ኢትዮጵያ ላይ ጎፍታ የማይሆን ከሆነ ኩሽ የሚባለውን ምድር ከሴማዋያን መገንጠል ነው። 

ይህ እንግዲህ በነ ጃዋር መሀመድ የተሰጠው ስልጠና ውጤት ነው። ኩሽ እንግዲህ አፋርን፣ አገውን ከቀይ ባህር ጀምሮ ሱማሌንና ኦሮምያን ጠቅሎ 75 በመቶ የሚሆነውን ህዝብ ላይ ኦሮሞ ጌታ ሆኖ የሚያስተዳድረው ሀገር መፍጠር ነው። ደሀ በህልሙ ቂቤ ባይጠጣ ኖሮ በድርቀት ይሞት ነበር እንደሚባለው። አንዴ አፋር፣ ሱማሌ እና አገው አሳምኖ ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ከገነጠለ በኋላ የኦሮሞን የበላይነት በግድም በውድም ይቀበላሉ። ያኔ የአፋርን ከአሰብ እስከ ምጽዋ ስንይዝ ኢሬቻን ቀይ ባህር ላይ እናከብራልን ብሎ ነበር።

አብይ በዚህ ንግግሩ ውስጥ ደቡብ የሚኖረወውን ወገናችንን እንደ ሰውም አይቆጥራቸውም። ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ አደሬ፣ ጋሞ ወዘተ እንደ 16ኛው ክፍለ ዘመን በገርባ (ባርነት የነ በቀለ ገርባ)፣ ሚዴቻ (ከባርነት የተለቀቀ)፡ ሞጋሳ (እንዳለ የብሄረሰብ ማንንነቱን ጥሎ ለኦሮሞ ገባር መሆን) ፣ እና ጉዲፈቻ ኦሮሞነትን እንዲቀበሉ ይደረጋሉ ነበር ያለው። ከዚህ ውስጥ እንደ ሰንሰለት ሆኖ ያስቸገረው ጉራጌ ነው። ጉራጌ ምንም ቢፍጨረጨር ክልልነት አንሰጠውም ምክንያቱም ጉራጌ፣ ስልጤ እና ጨቦ ጉራጌ በቅርብ ግዜ ኦሮሞ እንዲሆን የተወሰደ (የነ ገርማ ብሩ፡ ባልቻ ሳፎ)፣ እንዲሁም ቀያዮቹ እንደ በየነ በየነ ጴጥሮስ ያሉቱ  ሀድያዎች የጎሳ ምንጫቸው በእሌኒ ግዜ ሀድያ ላይ የሰፈረው የጎንደር ሰራዊት ስለሆኑ ጉራጌም ከጉደው ወንጪ ጀመሮ እስከ ጥቁር ውሀ ሊያስተሳስር ስለሚችል በምንም አይነት ለጉራጌ ክልል አንሰጠውም ነበር ያለው። ከእንብር ጀምሮ በትንሽ ኪሎሜትር በናዝሬት በኩል ከምንጃር ጋር ስለሚገናኝ  ክልል ከተሰጠው በኢኮኖሚ ሊበለጽግና ግንኙነቱን ከሰሜነኛ ሴማቲክ ብለው በጠላትነት  ከፈረጁት  ጋር ስለሚያደርግ በጭራሽ ክልል አንሰጠውም ብሏል ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.