Breaking News
Home / Amharic / አብን 10 የስራ አስፈፃሚ አባላትን አገደ።

አብን 10 የስራ አስፈፃሚ አባላትን አገደ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ፓርቲ ዐሥር አባላቱን ማገዱን አስታወቀ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ “የተጣለባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶችየተሳተፉ” መሆኑን የገለጸው አብን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው በተረጋገጠ የፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው ደብዳቤ አስታውቋል። አቶ ክርስቲያን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ፣ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው።

ዛሬ ግንቦት 1 ቀን፣ 2014 የተጻፈው እና በፓርቲው ሊቀ-መንበር አቶ በለጠ ሞላ ፊርማ እና ማኅተም ይፋ የሆነው ደብዳቤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ “ከዚህ ቀደም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ” ተሰጥቷቸው እንደነበር ገልጿል።

የፓርቲው የፖሊሲና ስትራቴጂ ኃላፊ የሆኑት አቶ ክርስቲያን “በንቅናቄው ሥራ አስፈፃሚነታቸውም ሆነ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው በጋራ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመሆን እና ንቅናቄውን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አንጃኞች ጋር ሕብረት በመፍጠርና ፣ ንቅናቄው የሃሳብና የተግባር አንድነት እንዳይኖረው በሚያደርጉ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ስተለገኙ” የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አስታውቋል።

ከፓርቲው የታገዱት ዐሥር የንቅናቄው መካከለኛ አመራር እና አባላት
“የተጣለባቸውን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተው በሕገ ወጥ ድርጊቶች ላይ ተሳታፊና መሪ” ሆነው መገኘታቸውን አብን አስታውቋል። ዐሥሩ የአብን አባላት “የጠቅላላ ጉባኤ ተወካይ ነን በማለት ሕገወጥ ቅስቀሳና አድማ መምራትና በንቅናቄው ውስጥ አንጃ መፍጠር” እንዲሁም “በእጅ አዙር ለመንጠቅ መሞከር” የሚሉትን ጨምሮ ስድስት ክሶች ተመስርተውባቸዋል። ሌሎች ሁለት አባላት ደግሞ “ጥብቅ ማስጠንቀቂያ” እንደተሰጣቸው የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አስታውቋል።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.