Breaking News
Home / Amharic / አቢይ አህመድ አቡነ ጴጥሮስን ከአይሮፕላን ጣቢያ መለሳቸው።

አቢይ አህመድ አቡነ ጴጥሮስን ከአይሮፕላን ጣቢያ መለሳቸው።

አንዳንድ ነጥቦች በብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ መከልከል ዙሪያ፦

1. ለዚህ አሳዛኝ ድርጊት የተቀነባበረ ሽፋን በቅርብ ሲሰጥ እንደምንሰማ የታወቀ ነው። በመንግሥት አካላት ተደርሶ የሚቀርበው ድራማና ዶክመንተሪ አያልቅምና ያልሠሩትን ወንጀል ሲያሸክሟቸውና ሲያጥላሉዋቸው እንሰማ ይሆናል። ስለዚህም ከሚዲያ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ልሳን የሆኑ ሚዲያዎችን ብቻ እንከታተል።

2. መንግሥት ይህን መሰል አንገት ሰባሪና ድፍረት የተሞላበት ድርጊት ሲፈፅምም ብፁዕነታቸው ያሉበትን ኃላፊነት ከግምት አላስገባም። ክብራቸውን የሚወክሉትን ቤተ ክርስቲያንና ሕዝባቸውን አላከበረም። በዚህ ጸያፍ ድርጊቱ እርሳቸውን ብቻ ሳይሆን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አማኝን እንዳሳዘነ መታወቅ አለበት።

3. ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ፓትርያርኩን ሸክም ጎንበስ ብለው የሚሸከሙ አባት ናቸው። የዛሬው የመንግስት ድርጊት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ከሜዳው በማግለል የቅዱስ ሲኖዶስን ማዕከላዊነት የመናድ ሙከራ ነው።

4. ብፁዕነታቸውን ወደ ሀገራቸው እንዳይገቡ የማድረግ ርምጃ የቤተ ክርስቲያንን በር የበግ ለምድ ለለበሱ ተኩላዎችና ለእንደ ልቡዎች ክፍት የማድረግ ዕቅድ አካል ነው። ከዚያም ውጪ ሌሎች ውጪ የሚኖሩ አበው ብፁዓን አባቶችንም አፍ የማስያዣ አካሄድ ነው።

5. በሌላ በኩል በውጪ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባቶች ቁጣቸውን ማሳደር አለባቸው። ምክንያቱም መንግሥትም ሆነ ሕገ ወጥ አካላት በተለያዩ ሚዲያዎች በኩል ይህን ነገር እያራገቡ ጫና ፈጥረው ሌላ ሲኖዶስ እናቋቁም የሚል ሀሳብ እንዲፈጠር መሥራታቸው አይቀርምና በዚህ በኩል ረጋ ብሎ መጠንቀቅ ተገቢ ነው። ተተኪ ጸሐፊ ይመረጥ የሚል ሤራ እንዳይሸርብም ነቅቶ መጠበቅና መሥመር ማስያዝ እንደሚገባው ሳይረሳ!!

6. ይህ ድርጊት ቤተ ክርስቲያንን ለመከፋፈል የታሰበ እቅድ ነው። ስለዚህም እንደ ምእመን በበለጠ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ላይ ማተኮርና ቤተ ክርስቲያናችንን በንቃት መጠበቅ አለብን።

7. ይሄ ጉዳይ መሥመር እንዲይዝ የሚያደርጉ አባቶችን በሚያስፈልጋቸው ሁሉ ማገዝና ትዕዛዛቸውንም እንደ ልጅ መፈጸምም ይገባናል።

ልዑል እግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን

#ኢንፈርህሞተ
#ሞትንአንፈራውም

Via Birhanu Tekleyared

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.