Breaking News
Home / Amharic / አስቸኳይ መልዕክት ከአማራ ክልል !

አስቸኳይ መልዕክት ከአማራ ክልል !

የሙቀት መለኪያን ለመግዛት ስለወሰንን በማርቆስ አካባቢ ያላችሁ ወገኖቸ ይህንን ማሽን በመፈለግ ባስቸኳይ ታሳውቁን ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን!!

መርዳት የምትችሉ እባካችሁ አሳውቁን

e-mail: amhara1@amharaonline.org

Letenah Ejigu Wale
ሰበር ዜና፤

ኮሮና ባህር ዳር እና እንጅባራ እንደተገኘ ሰምተናል ። እንድትደነግጡ ሳይሆን የበለጠ ጥንቃቄና ዝግጅት እንድናደርግ ነው ። ባህር ዳር ከተማዋ ብትዘጋ ጥሩ ነው ። ሰው ገብያ ባይሄድ እና ቤቱ አርፎ ቢቀመጥ ጥሩ ነው ። በቀን ገቢ የሚተዳደሩትንና ለመደጎም ወደ ማዕከላት እየገቡ የሚረዱበት ሁኔታ አሁኑኑ መደረግ አለበት ። የክልሉ መንግስት የሃብት አሰባሳቢ ቡድን አዋቅሯል ። አራት አይነት ሃብት ይፈለጋል ። ሃሳብ ፤ በጎ ፈቃደኛ ፤ ገንዘብ ፤ የህክምና እና የምግብ ቁሳቁስ ። በ12 ባንኮች ሂሳብ እንደተከፈተ ሰምተናል ። ዝርዝሩን እናቀርባለን ። በፍጥነት መረጃ በመለዋወጥ እና በመደጋገፍ ይህን ጊዜ ማለፍ አለብን ። ህዝባችንን ማንቃትና ማስተማር አለበት ። መፍራት ሳይሆን መጠንቀቅ አለብን ። መረጃ እንደደረሰን እናሳውቃለን ። በምንችለው ሁሉ ለመረባረብ እንዘጋጅ ።

 አስቸኳይ መልዕክት በ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና መቆጣጠር ከተቋቋመው ኮማንድ ፖስት!!

1. ባለፋት 3 ሣምንታት ከውጭ ሀገር ወደ ሀገር ቤት የተመለሳችሁ እና በአማራ ክልል ውስጥ የምትኖሩ በአስቸኳይ በየአካባቢያቸሁ ወደሚገኝ የመንግስት የጤና ጥበቃ ተቋም ሪፖርት እንድታደርጉ እና ራሳችሁን እና ያገኛችኋቸውም ሠዎች ራሣቸውን እንዲያቅቡ፣

2. ለመላ የክልላችን የገጠር ነዋሪዎች በሙሉ ያጋጠመን ችግር መድሀኒት ያልተገኘለት ወረርሽኝ መሆኑን ተረድታችሁ ለግብይትም ሆነ ለሌላ ማህበራዊ ጉዳዮች ወደ ከተማ የምታደርጉትን ጉዞ በማቆም ባላችሁበት እራሳችሁን ከበሽታው እንድትከላከሉ፣

3. መላው የክልላችን ነዋሪዎች አሁን ካለው የወረርሽኙ አሣሣቢ ሁኔታ አንፃር እንደ አስፈላጊነቱ ታይቶ በክልሉ ውስጥ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ትዕዛዝ ሊሠጥ ሥለሚችል ይኸንኑ አስቀድማችሁ በማወቅ ወደ ቋሚ የመኖሪያ (መቆያ) ቦታችሁ ላይ በመሆን ከመንግስት የሚሠጠውን ትዕዛዝ በትኩረት እንድትጠባበቁ እንዲደረግ እናሳውቃለን፡፡

በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሁለት ሰዎች በአማራ ክልል የሚገኙ ናቸው – የጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው እለት በተጨማሪነት በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ሁለት ሰዎች በአማራ ክልል የሚገኙ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ግለሰቦቹ አንደኛዋ ከዱባይ ቆይታ ወደ ባህር ዳር የተመለሰች ሲሆን፥ ሌላኛው ደግሞ ከአሜሪካ የመጣ የአዲስ ቅዳም ነዋሪ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል።

ሁለቱም ግለሰቦች ላለፉት ቀናት ክትትል ሲደረግላቸው መቆየቱንም ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ የነበራቸውን ሰዎች የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ለሁለቱ ግለሰቦች በክልሉ ለይቶ ማቆያ የህክምና ክትትል እና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።

በሃገሪቱ ለ19 ሰዎች በለይቶ ማቆያ የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፥ አንድ ግለሰብ በፅኑ ህሙማን ክትትል እየደረላት መሆኑ ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም ሁለት የውጭ ዜጎች ወደ ሃገራቸው ሲመለሱ ሁለት ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ አገግመዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.