Breaking News
Home / Amharic / አማራ ባንክ አ.ማ. ማስታወቂያ !

አማራ ባንክ አ.ማ. ማስታወቂያ !

 
 
አማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ)
ክቡራን የአማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) ባለአክስዮኖች ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ጥቅምት 10 ቀን 2014 ዓ.ም ለሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ በጻፈው ደብዳቤ ባለአክስዮኖች በሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ፊት ቀርበው በባንኩ መመስረቻ እና መተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማቸውን እንዲያኖሩ ፈቃድ ሰጥቷል፡፡
ክቡራን ባለአክስዮኖች ፊርማችሁ ባንኩን ስራ ለማስጀመር እና የባንኩ ባለአክስዮን መሆናችሁን ለማረጋገጥ የግድ አስፈላጊ ተግባር መሆኑን እያስታወቅን ፣ ባለአክስዮኖች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ቦታዎች ከጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት ቀርባችሁ በባንኩ የመመስረቻ ጽሁፍ እና የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ፊርማችሁን እንድታኖሩ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ባለአክሲዮኖች ለፊርማ ሲመጡ፦
● አክስዮን የገዙበትን ፎርም እና ክፍያ የፈጸሙበትን የባንክ ስሊፕ ፣ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ የታደሰ መታወቂያ ካርድ ፣ ፖስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ፤ ትውልደ ኢትዮጵያዊ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሆኑ ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቢጫ ካርድ እና ፓስፖርት ወይም የመኖሪያ ፈቃድ ፤ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
● ወኪል ከሆኑ ውል ለመዋዋል ሥልጣን በተሰጠው አካል የተረጋገጠ የውክልና ሥልጣን ማስረጃ ዋናውን ከአንድ ኮፒ ጋር እና ማንነታችሁን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዞ በመቅረብ መፈረም የምትችሉ መሆኑን እያስታወቅን ፣ የትውልደ ኢትዮጵያውያን ወኪሎች ከውክልና ማስረጃ በተጨማሪ የወካዮቻችሁን የትውልደ ኢትዮጵያዊነት ማስረጃ ቢጫ ካርድ ይዛችሁ መቅረብ ያስፈልጋል፡፡
● የንግድ ማህበራትን በተመለከተ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችንና ቅድመ ሁኔታዎችን በተመለከተ ለተጨማሪ መረጃ ጥቅምት 14 ቀን 2014 ዓ.ም. በሪፖርተር እና አዲስ ዘመን ጋዜጣ የወጣውን ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡
ማሳሰቢያ
● ከዚህ ቀደም አማራ ባንክ አ.ማ. (በምስረታ ላይ) ያደረገውን ጥሪ ተቀብላችሁ ፣ በሰነዶች ምዝገባ እና ማረጋገጫ ኤጀንሲ እንዲሁም በህግ ስልጣን በተሰጣቸው አካላት ፊት ቀርባችሁ ለባንኩ አደራጆች ውክልና የሰጣችሁ ባለአክስዮኖች በወኪሎቻችሁ አማካኝነት የሚፈረምላችሁ በመሆኑ ፣ በድጋሜ ቀርባችሁ መፈረም የማይጠበቅባችሁ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
● አክስዮን በምትፈርሙበት (በምትገዙበት) ጊዜ ሙሉ ስማቹህን እና አድርሻቹህን አሟልታቹህ ያላስመዘገባቹህ ባለአስክዮኖች ፣ ከዚህ ቀደም ውክልና ብትሰጡም ባትሰጡም በግንባር ቀርባቹህ መረጃቹህን የማሟላት ግዴታ ያለባቹህ መሆኑን እናስታውቃለን። መረጃቹህ ያልተሟላ ባለአክስዮኖች ፣ መረጃቹህ እስኪሟላ ድረስ ስማቹህ በባንኩ የአክስዮን መዝገብ የማይገባ እና ባለአክስዮን ለመሆን የማትችሉ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
● በኮቪድ19 ወረርሽኝ ምክንያት ከተደቀነው ስጋት አንጻር ለፊርማ በምትመጡበት ጊዜ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል አድርጋችሁ እንድትመጡ እያሳሰብን ፣ ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ጥንቃቄዎችን እንድታደርጉ እናስታውቃልን፡፡
አማራ ባንክ አ.ማ.
(በምስረታ ላይ)
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.