Breaking News
Home / Amharic / አማራ ባንክ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ ይጀምራል !

አማራ ባንክ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ ይጀምራል !

አማራ ባንክ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ ይጀምራል

*****************

በምስረታ ላይ የቆየው የአማራ ባንክ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ እንደሚጀምር ባንኩ አስታውቋል።

በእለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ ይከፍላል ተብሏል።
የአማራ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፈንታ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት፤ ባንኩ ሰኔ 11 ስራውን በይፋ የሚጀምር ሲሆን፤ እስከ ሰኔ ሰላሳ ሰራ የሚጀምሩት ቅርንጫፎች ቁጥር ከ100 በላይ እንደሚያሳድግም ጠቁመዋል።
ባንኩ በኢትዮጵያ ባለ አክሲዮኖች ብዛት ክብረ ወሰን መስበሩን ያመላከቱት አቶ መላኩ፤ ከፍተኛ የባለ አክሲዮን ቁጥር ማብዛት ብቻም ሳይሆን በውጪም በአገር ውስጥም ያሉ ኢትዮጵያውያን መጠነ ሰፊ ተሳትፎ የተመሰረተ ባንክ ነው ብለዋል።
የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሄኖክ ከበደ በበኩላቸው እንደገለፁት፤ ባንኩ በተለያዩ የተግባቦት ስርአት የመጣ ሲሆን በዋነኝነትም “ከጎንዎ ማን አለ” የሚለው ማስታወቂያ እንደሚገኝበትም ገልፀዋል።
ሰኔ 11 ስራውን በይፋ የሚጀምረው ባንኩ በእለቱ ለአዲስ አበባና ዙሪያው ነዋሪዎች በሙሉ በአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ የሙሉ ቀን የጉዞ ክፍያን ባንኩ ይከፍላል ተብሏል።
በእለቱ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች በተመረጡ ሆስፒታሎች ለሚወልዱ እናቶች በባንኩ ስም የእንኳን ደስ ያላችሁ ስጦታም ይበረከትላቸዋልም ተብሏል።

ኢፕድ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.