ጎንደር፣ ጎጃም፣ ወሎ፣ ሸዋ የቦታ ስሞች ናቸዉ፣ ድሮ በንጉሱ ጊዜ ጠቅላይ ግዛት፣ በደርግ ደግሞ ክፍለ ሀገር በሚል ይታወቁ ነበር። በእነዚህ ቦታዎች የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸዉን ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ወልዬ፣ ሸዌ ብለዉ ይጠራሉ በሌለዉም ተብለው ይታወቃሉ በሚኖሩበት ሀገርና አካባቢ ሲጠሩ። እነዚህ ሰዎች አብዛኞች በነገድ፣ በብሔር ሲገለጡ ግን አማሮች ነዉ ሚባሉት። እንግዲህ በጎንደርም፣ በጎጃምም፣ በወሎም፣ በሸዋም የሚኖሩት አብዛኞች አማሮች ናቸዉ። በአማራነት አንድ ናቸዉ፣ በቦታዎች ምክንያት ያሉት ልዩነቶች በአማራነታቸዉ ላይ ምንም ልዩነት አያመጡም፣ የላቸዉም፣ ሁሉም አማሮች ናቸዉ። ግፋ ቢል የጎንደር አማራ፣ የጎጃም አማራ፣ የወሎ አማራ፣ የሸዋ አማራ የሚል የቦታ ስም ከመጨመራቸዉ ዉጭ። ይህ ደግሞ የነበረ፣ ያለ፣ የሚኖር ነዉ፣ የልዩነት ምክንያትም፣ ስበብም ሊሆን አይችልም። ልክ እንደዚሁ በሙዚቃዉም፣ በቋንቋዉም በአማረኛዉ አነጋገራዊ ዘይቤ የጎንደር የወሎ፣ የጎጃም፣ የሸዋ አማረኛ ቅላጤ አለዉ፣ ግን ሁሉም አንድ አማረኛ ቋንቋ ነዉ። በሙዚቃዉና በእስክስታዉም እብዲሁ፣ ሆኖም ሁሉም አንድ አማሮች ናቸዉ። አንደ አማረኛ ትንሽ በተለየ ዘይቤ ተናጋሪዎች ናቸዉ። የአካባቢያዊ ልዩነቶች ከቦታ ቦታ አኳያ ይኖራል፣ ይህ የነበረ፣ ያለና የሚኖር ነዉ፣ ድሮም ቢሆን በክፍለ ሀገር ደረጃ በነበሩበት ጊዜም በአዉራጃና በወረዳ፣ በቀበሌ ደርጃ እንዲህ አይነት ልዩነቶች አሉ። ይህ ማለት ግን በአማራነታቸዉ ላይ ምንም ልዩነት የለዉም። ሁሉም አንድ አማሮች ናቸዉ። አሁን የአማራ ህዝብ አንድነት የሚያስፈራቸዉ ፀረ አማሮች የአካባቢ ልዩነቶችን እያጋነኑ ለመለያየትና ልዩነትን ለመፍጠር ሲጥሩ ይታያል። የወሎ ጀግና የወሎ ብቻ አይደለም፣ የጎንደር ጀግና የጎንደር ብቻ አይደለም፣ የጎጃም ጀግና የጎጃም ብቻ አይደለም፣ የሸዋ ጀግና የሸዋ ብቻ አይደለም፣ ባይገርማችሁ የኢትዮጵያ ጀግና ከሄትኛዉም ብሔርና አካባቢ ይሁን የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጀግና ነዉ፣ ምሳሌ አሊ በርኬ የኦሮሞን የወለጋ ብቻ አይደለም የኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጅግና ነዉ። ስለዚህ የአንዱ አካባቢ አማራ ጀግኖች የሁሉም አማራ ጀግኖች ናቸዉ። የወሎ ችግር የወሎ ብቻ አይደለም፣ የጎንደር ችግር የጎንደር ብቻ አይደለም፣ የጎጃም ችግር የጎጃም ብቻ አይደለም፣ የሸዋ ችግር የሸዋ ብቻ አይደለም፣ የሁሉም አማራ ችግር ነዉ። ስለዚህ አማራ አካባቢዎችን የአካባቢ ማንነቶችን ያከብራል እንጅ በአካባቢ ማንነት አይከፋፈልም። ሁሉም አማራ አንድ ነዉ፣ ከልሉ ዉጭ ያለዉን ጨምሮ። ለመሆኑ ከክልሉ ዉጭ ያለዉን አማራ ጠላቶቹ ሲገሉት ሲያፈናቅሉት፣ ሲያገሉት፣ አማራ ብለዉ እንጅ ወሎዬ፣ ሸዌ፣ ጎንደሬ፣ ጎጃሜ ብለዉ አይደለም፣ ከዚህ መማር ይገባል። የምትገደልበትን፣ የምትገፋበትን፣ የምትሳደድበትን፣ የምትፈናቀልበትን፣ የሆናችሁትን አለመሆን የማትችሉትን አማራነታችሁን በአካባቢና በጥቃቅን ልዩነት ሳትለዩ በጋራ በአንድነት ስትከላከሉ ነዉ ህልዉናችሁን ማስከበር የምትችሉት። ጠላቶቻችሁን የምትቋቋሙት። የሚከፋፍለዉ አማራን ለማዳከም የሚፈልገዉ የአማራ ጠላት ብቻ ነዉ።
ሌላዉ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ለምንወድ ሁሉ፣ ኢትዮጵያን ከአማራ ዉጭ የምናስብ ከሆነ በጣም ተሳስተናል። ለኢትዮጵያ መኖር የአማራ መኖር በጣም ወሳኝ ነዉ። የጠነከረ አማራ መኖር የጠነከረች ኢትዮጵያ መኖር ዋስትና ነዉ። አማራ ከኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት ተቃርኖ ቅራኔ የለዉም። በኢትዮጵያ ዉስጥ አማራ በአማራ ዉስጥ ኢትዮጵያዊነት አለ። ይሄን በደንብ መረዳት ግድ ይላል፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር አንድ ናት፣ ባለ ብዙ ባህል፣ ቋንቋ፣ ነገድ፣ አንዳቸውም እንዲጎሉባት አትሻም፣ እያንዳንዳቸው በየ ደረጃቸዉ ጠቃሚ ድርሻና ሚና አላቸዉ፣ ሁሉም በሚናዉ በአግባቡ ተገቢዉን ሲያደርግ ኢትዮጵያ ሰላሟ የተከበረ ሀገር ትሆናለች። ይሄን ከተረዳንና ከተገነዘብን አማራ ነኝ ማለት ከኢትዮጵያዊነት አያሳንስም፣ አማራ ነኝ ማለት ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ማለት አይደለም። አማራ ነኝ በሚለዉና ኢትዮጵያዊ ነኝ በሚለዉ አማራ መካከል ኢትዮጵያዊነት የአንዱ ካንዳቸዉ አይበልጥም። በነገራችን ላይ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለዉ አማራ አማራነትም አማራ ነኝ ከሚለው አያንስም። ይሄን ለማረጋገጥ አማሮችን ለይተው ከሚያርዱት ኦነግ፣ የጉምዝ አማፂያንና ወያኔ ህወሓቶች ፊት ከተገኛችሁ ሁለታችሁንም እኩል ያለ ምህረት ያርዷችሁዋል።
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር በውስጧ ያለዉ ህዝብና በዓለም የሚታወቀው የጆግራፊያዊ ክልል መሬቷ ማለት ነዉ። የህዝቡ ማንነት ደግሞ የተለያየ ከ80 በላይ የነገድ ማንነት ያለዉ ነዉ። ኢትዮጵያዊ ለመሆን ከእነዚህ ነገዶች የአንዱ አካል መሆን በቂ ነዉ፣ አብዛኞች በኢትዮጵያ ብቻ የሚኖሩ በመሆናቸዉ፣ ለምሳሌ ጉራጌ ብል ኢትዮጵያዊ የሚል፣ አማራ ብል ኢትዮጵያዊ የሚል ይመጣብኛል በአብዛኛዉ መገኛቸዉ ኢትዮጵያ በመሆኑ፣ ስለዚህ የብሔረሰብ ማንነት ከኢትዮጵያዊ ማንነት ጋር የተሳሰረ መሆኑንም ልንገነዘብ ይገባል። ኢትዮጵያ እናፈርሳለን የሚሉትን እየሰማን በፍራቻም ሊሆን ይችላል የብሔር ማንነትን የምንሸሸዉ፣ በእኔ እምነት ይህ በፍፁም ልክ አይደለም፣ የብሔር ማንነታችንን ከሀገራችን ጋር ያለዉን ቁርኝት በሚገባ ተረድተን ካጠናከርነዉ ሌሎችም ይሄን እንዲያደርጉ ካገዝን በትክክል ኢትዮዊነትን እናጠነክራለን መፍረስ የሚባለውን ጭራሽ አይታሰብም ብዬ አምናለሁ። እንጅ ከብሔር ማንነት በመሸሽ ኢትዮጵያን ከመፍረስ እታደጋለሁ የሚለዉ ትክክል አይደለም፣ ይልቅ በጣም ጥንቃቄ የምናደርገው ሌሎችን መጥላት እንደሌለብን ነዉ፣ ራስን መውደድ ተፈጥሯዊ ነዉ ይሄን ፈጣሪም ይመሰክራል፣ ” ባለ እንጀራህን እንደ ራስህ ዉደድ” ሲል መጥላት ግን ሃጢያት ነዉ፣ ሌሎችን አንጥላ፣ የህወሓት ታላቁ ዴዌ ለዚህ ሁሉ ክፋትና ተንኮል ግፍ ያበቃቸዉ በርሳቸው ላይ በፈጠሩት የበታችነት ስሜት የፈጠሩት ከልክ ያለፈ ጥላቻ ነዉ፣ ጥላቻ የሰይጣን አምልኮና ተልኮ ነዉ፣ እግዚአብሔር ከጥላቻ ያድነን።