Breaking News
Home / Amharic / “ኃላፊነት የተሞላበት ትዕግስታችን ፍርሐት ከመሰላችሁ መሳሳታችሁን ለማሳየት ከባድ አይሆንብንም!” – Dr. Dessalegn Chane

“ኃላፊነት የተሞላበት ትዕግስታችን ፍርሐት ከመሰላችሁ መሳሳታችሁን ለማሳየት ከባድ አይሆንብንም!” – Dr. Dessalegn Chane

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ በትዊተር ገጻቸው “የአብን አመራሮች እንዲፈቱ ከመንግስት ጋር ብንስማማም ተግባራዊ መሆን አልቻለም ፣ ስለሆነም ቀጣዩ እርምጃ ህዝባዊ እምቢተኝነት ነው” ብለዋል። የእንግሊዘኛ ሙሉ መግለጫቸውን ወደ አማርኛ ተርጉመነዋል፣ እነሆ!

“እኛ የአብን አመራሮች ከታላላቅ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር የታሰሩ መሪዎቻችን እንዲለቀቁልን ተነነጋግረን ነበር። በስምምነታችን መሰረትም ከአርብ በፊት እንደሚፈቱ ተወስኖ ነበር ፣ ነገር ግን ስምምነቱ ተግባራዊ አልተደረገም።
ኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ያልተረጋጋ ፖለቲካ ወደፊት ለመጓዝ ውይይት እና ድርድር ብቸኛ አማራጮች ናቸው ብለን እናምን ነበር ፣ ያ ግን አልሆነም። ስለዚህ ቀጣዩ እርምጃ በህገወጥ መንገድ የታሰሩብን መሪዎችን ለማስፈታት የራሳችንን እርምጃ መውሰድ ነው። ኃላፊነት የተሞላበት ትዕግስታችን ፍርሐት ከመሰላችሁ መሳሳታችሁን ለማሳየት ከባድ አይሆንብንም!” ብለዋል።
 
——-የአብንን ጥሪ ሁሉም የአማራ ህዝብ የሚጠብቀው ስለሆነ መሪዎቻችን በቅርብ ካልተፈቱ ወደ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ መሄድ ግድ ነው።
86 ሰው የጨፈጨፈው አውሬው ጃዋርን ሆቴል እየቀለበ እና በ20 ኮማንዶ እያስጠበቀ በእስክብሪቶ የሚዋጋው ክርስትያን ታደለን ጨለማ ቤት ማሰቃየት ለአማራ ህዝብ ውርደት ነው::
 
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.