Breaking News
Home / Amharic / ትችት በፋኖ ላይ ! critics about FANO

ትችት በፋኖ ላይ ! critics about FANO

የበታች የፋኖ አባላትን የላይኛው የፋኖ መሪ ወታደራዊ ተክለ ቁመና ባለው መልኩ ካልተቆጣጠራቸው የሚደርሰው ጉዳት ምን ሊሆን ይችላል⁉️
1ኛ፦ የተማከለ ትዕዛዝ እና ቁጥጥር ማነስ፡- ከፍተኛው የፋኖ መሪ የታችኛው የፋኖ አባላትን በብቃት ማስተዳደር እና መምራት ሲሳነው፣ በደረጃው ውስጥ የመደራጀት እና የመደናገር ዕድሉ ከፍተኛ ነው። ይህ በተለያዩ ክፍሎች መካከል ቅንጅት እንዳይኖር ያደርጋል። በዚህም ምክንያት የሀብት አጠቃቀምን በአግባቡ አለመጠቀም እና በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሊኖር የሚችለውን አለመግባባት ያስከትላል።
2ኛ፦ በቂ ያልሆነ ስልጠና፡- የላይኛው የፋኖ መሪ ከታች ያሉ ብርጌዶችን፣ የሻለዎችን እና አባላት ተገቢውን ስልጠና እንዲያገኙ ካላረጋገጠ በእያንዳንዱ አደረጃጀት መካከል ዝቅተኛ የብቃት እና ውጤታማነትን ያስከትላል። ይህ በክዋኔዎች ወቅት ወደ ስህተቶች ሊመራ ይችላል፣ ለምሳሌ ሁኔታዎችን የተሳሳተ ግምት።
3ኛ፦ የሞራል እና የመነሳሳት መቀነስ፡- ውጤታማ አመራር አለመኖሩ የታችኛው የፋኖ አባላትን ሞራል እና ተነሳሽነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል። በፋኖ መዋቅር ውስጥ የታያዙ ራሳቸውን አደራጅተው ዱር ቤቴ ያሉ የላይኛው አመራር የማያውቃቸው ፋኖዎች አለቆቻቸው ድጋፍ እንደሌላቸው ወይም እንዳልተመሩ ሲሰማቸው፣ ሞራላቸው ሊቀንስባቸው ይችላል፣ ይህም በአጠቃላይ አፈፃፀማቸው እና ለሥራቸው ያላቸውን ቁርጠኝነት ይነካል።
4ኛ፦ የውስጥ ግጭቶች ስጋት መጨመር፡- ከከፍተኛው መሪ ትክክለኛ መመሪያ ከሌለ በድርጅቱ ውስጥ ስልጣን ለመያዝ ወይም ተፅዕኖ ለመፍጠር በሚሯሯጡ የፋኖ አባላት መካከል አለመግባባቶች ወይም ፉክክር ሊፈጠር ይችላል። ይህ ትኩረትን ከዋናው ተልእኮ ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚያዞር እና አጠቃላይ ውጤታማነትን የሚያደናቅፍ ውስጣዊ ግጭቶችን ያስከትላል።
5ኛ፦ ያልተፈቀዱ ተግባራትን ሊፈጽም የሚችል፡- ከከፍተኛው መሪ ግልጽ መመሪያ በሌለበት ጊዜ፣ አንዳንድ የጦር ሰራዊት አባላት ያለአግባብ ፈቃድ ወይም ቁጥጥር ጉዳዩን በእጃቸው ሊወስዱ ይችላሉ። ይህ ያልተፈቀዱ ውጤቶች ለምሳሌ ከጠላቶች ጋር የሚደረግ ግንኙነት ወይም የአለም አቀፍ ህግ ጥሰትን የመሳሰሉ ያልተፈቀዱ መዘዞችን ሊያስከትል ይችላል።
በማጠቃለል የፋኖ የላይኛው አመራር በእያንዳንዱ ቀበሌ ያሉ የፋኖ አባላትን በብቃት መቆጣጠር እና መምራት ሲሳነው፣ አለመደራጀትን፣ በቂ አለመሆንን ጨምሮ በርካታ አሉታዊ መዘዞችን ያስከትላል። ስልጠና፣ የሞራል መቀነስ፣ የውስጥ ግጭቶች እና ያልተፈቀዱ ድርጊቶች የመጋለጥ እድል ይጨምራል።
እነዚህን ምልክቶች በሚገባ ተመልክተናል። የአንዱ አባል ስህተት የሁሉ ስህተት ተደርጎ ሊወሰድ የሚችልበት አጋጣሚ አለ። ድርጅት የማይቆጣጠረው ግለሰብ ካለ እና ግለሰብ የድርጅቱ አካል ከሆነ ፥ የግለሰቡ አቋም የድርጅቱ ተደርጎ ይወሰዳል። የግለሰቦች አቋም የድርጅት አይደለም ለማለት በመጀመሪያ ግለሰቦችን በድርጅታዊ መመሪያ፣ ዲሲፕሊን መምሪያ፣ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ እና የድርጅቱ አባላት ከሚመለከታቸው ስራ ውጭ ያለድርጅቱ ወይንም ተጠሪ ለሆኑት የድርጅቱ የላይኛው አመራር ሳያሳውቁ የሚያደርጉትን ያልተገባ ግንኙነት፣ መግለጫ መስጠት በሚገባ እርምት መስጠትና ማስተካከያ ማድረግ ይገባል። ህዝብ ዝም ብሎ አያምንም። ህዝብ የሚያምነው የሚያየውንና የሚሰማውን ነው።
ለምሳሌ ያህል፡ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ የሆነው ማርሸት የሚባል ግለሰብ “ዐማራ የዘር ማጥፋት ተግባር አልተፈጸመበትም” የሚል ትልቅ ቅጥፈትና ክህደት ፈጸመ። በመጀመሪያ ማርሸት ዐማራ ላይ የዘር ማጽዳት እንጅ “የዘር ማጥፋት አልተፈጸመበትም” ማለቱ በስህተት ከሆነ መታረም የሚገባውና በድፍረትና ወንጀሉን ማቃለል ከሆነ ደግሞ ራሱ ወንጀል መሆኑ ታውቆ ድርጅታዊ ማስተካከያ የሚጠይቅ ነው። ዐማራ ላይ ጄኖሳይድ ተፈጽሟል ለማለት 60 ሚሊዮን ዐማራ ማለቅ የለበትም። ሌላው ይቅርና ማይካድራ ላይ የተፈጸመው የአመት ታሪክ ያለው የዐማራ ጄኖሳይድ ነው።
በዐማራ ላይ የዘር ማጽዳት ነው የተፈጸመው ማለት እጅግ አደገኛ ተንኮል ነው። የመጀመሪያው በዐማራ ላይ ጄኖሳይድ ያስፈጸሙና የፈጸሙ ብአዴንን፣ ህወሓትን እና ኦነግ ኦህዴድን ነጻ ማውጣት ነው። ሁለተኛው፡ ዐማራ የዘር ማጽዳት ነው የተፈጸመበት ማለት በሌላ አገላለጽ ትግራይ ላይ ተመሳሳይ ድርጊት ወልቃይትና ራያ ላይ ተፈጽሟል እና አሁን የተያዘው የብአዴን፣ ህወሓት እና እህዴድ ብልጽግና ትግራይን ወልቃይትና ራያ ላይ የማስፈርን ዕቅድ የሚደግፍ ነው። ሶስተኛውና ጠለቅላሉ፡ የዐማራን ትግል፣ ዐማራ ላይ የተፈጸመውን አጠቃላይ የዘር ጭፍጨፋ በዓለማቀፍ ደረጃ ዝቅ ማድረግ ነው። በዚህ ትችትን ያስተናገደው ቃል አቀባዩ የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሴን በማወደስና ፎቶውን በመለጠፍ አድበስብሶ ለማለፍ ሞከረ። አርበኛውን ማወደሱና ፎቶውን መለጠፉ ራሱ ሌላ ፖለቲካዊ ይዘት ያለው ሆኑ ፤ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ስለድርጊቱ ምንም ማብራሪያ አልሰጠም። የግለሰብ አቋም ነው እንበልና እንለፈው ቢባል እንኳን በዚህ ዙሪያ የሚደናገሩ እና የድርጅቱ አቋም የሚመስላቸው ቡድኖች ካሉም ጥርጣሬያቸውን በቅንነት ማጥራት መሞከር ያስፈልግ ነበር። ከዐማራ ህዝብ የሚበልጥ ግለሰብ የለምና የግለሰብን ስህተት ለሰፊው ህዝብ የድርጅቱን አቋም ማጥራት ያስፈልጋል። በዚህ ከቀጠለ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የምናመጣው ናቸው ወንድሞች ቢኖሩንም በብዙዎች ዘንድ ለትችትና ለስጋት ይዳረጋል። ማጥራት ክፋት የለውም።
ሌላው ከሰሞኑን ፋኖ የቆየ ሞላ የሚባል የዐማራ ፋኖ በጎጃም ፋኖ የአለም አቀፍና ቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ሃላፊ “ ከጉሙዝ ፣ ከትግራይና ከኦሮሞ ተወካዮች ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጅቴን አጠናቅቄያለሁ” የሚል መግለጫ በሮሐ ሚዲያ በኩል አስነብቧል። አያይዞም
“የአማራ ክልል መንግስት ፋኖ ነው ፣ የአራት ኪሎ መንግስት ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊን ያሳተፈ ነው” የሚለው ሀሳብ ሰጥቷል። ስለዚህ ንግግር አንድ ተራ አርሶ አደር የፖለቲካውን መዳረሻ የሚመረምርና ምን ማለት እንደሆነ የሚረዳው ነው። ይሄን ያለው የዐማራ ፋኖ በጎጃም የአለም አቀፍና ቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ሃላፊ የግል ሀሳብ ነው ሊባል አይችልም። የግል ሀሳብ ነው እንበለው ቢባል እንኳን እንደ ድርጅት ማብራሪያ እና እርምት የሚያስፈልገው ነው። የዐማራ ፋኖ እንደዚህ አይነት ለትችት እና በአቻ ፋኖዎች ውስጥ ጥያቄ የሚያስነሱ ጉዳዮችን በዝምታ ካለፈ ለትችት የተዳረገ ነው። ተችቱ ደግሞ በዐማራ አንድነት ላይ ትልቅ እንቅፋት የሚሆን ነው። በነገራችን ላይ ቅድሚያ ባለቤቱ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ስለሆነ ተጠያቂነቱን ወደ እሱ አመጣነው እንጅ ይሄ ጉዳይ ሁሉንም የፋኖ አደረጃጀቶች የሚያጠቃልል ጊዳይ ነው። የፋኖ የፖለቲካ ኃይሎች ተራ አክቲቪስቱ የሚለቀውን ፎቶ እየለቀቁ ስራን ለማስመስከር ከሚሞክሩ ፤ የትግላቸውን ሁኔታ ቢያጠሩ፣ ውዥንብሮችን ቢያጠሩ፣ ርዕዮተዓለማዊ ሂደቶች ላይ ጥናት ቢያካሂዱ መልካም ነበር።
አንድ ቀበሌ ላይ የተደረገን ተኩስ እንደ ትልቅ ግብ መቁጠር ስራ ለዐማራ የህልውና ትግል እጅግ አደገኛ እንቅፋት ነው። ጦርነቱ ከክልሉ መውጣት ያልቻለው፣ የዐማራ ትግል ወደ ከንድነት ያልመጣው ከላይ የተነሱ ትችቶችን አለማጥራት እና የግለሰቡ አቋም ነው ተብሎ እንዲታለፍ ተድበስብሶ በሀሜትና በጥርጣሬ እርስ በእርስ እንዲተያይ በመደረጉ ነው። የትም ያሉ ፋኖዎች ወንድሞቻችን ናቸው። ውድቀታቸው ውድቀታችን፣ ሞታቸው ሞታችን፣ ድካማቸውም ድካማችን፣ ስኬታቸው ስኬታችን ነው። ለዚህም ከጀርባ አሽማጠን ለማለፍ ህሊናችን አይፈቅድም። ጠላቶቻቸው ጠሊታችን ነውና የጠላታቸውን ጥቃት በጋራ እየተከላከልን ፤ ጠላት በሰርጎ ገብና በብአዴን ገመድ political suicide ሊፈጽምባቸው ሲያደላድል እንጋፈጥላቸዋለን‼️ ከራሳችን በላይ ስለምንወዳቸው!!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.