Breaking News
Home / Amharic / ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ! Protest in Addis. Please share.

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ! Protest in Addis. Please share.

ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ!
==============
(ይህን ፖስት ኦርቶዶክስ የሆነ ሁሉ ሼርና ላይክ በማድረግ ለሁሉም ህዝበ ክርስቲያን እንድታደርሱት በእመቤቴ ስም እጠይቃለሁ)
+ + +
እጅግ በጣም በተቀናጀ መልኩ ከፍተኛ በጀት በተመደበላቸው ሽብርተኞች በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆምና መንግስትም እነዚህ ወንጀለኞች ወደ ህግ እንዳይቀርቡ እየሰጠ ያለውን ሽፋን በቶሎ አቁሞ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ልዕልና እንዲያስከብር ለመጠየቅ መስከረም 4/2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ተዘጋጅቷል። እናንተም የተዋህዶ ልጆች ከእናት ቤተ ክርስቲያን በላይ ምንም የለምና በሰልፉ እንድትገኙና ይህንን ፖስት ለሁሉም በማድረስ የበረከቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ስንል በቅዱሳን አባቶቻችን ስም እንጠይቃለን።
“ከጠላቶችህ ጋር በሰላም ኑር ነገር ግን ይህን የምልህ ከግል ጠላቶችህ ጋር ነው እንጂ ከእግዚአብሔር እና ከቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ጋር አይደለም”

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰንበት ትምህርት ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ላይ #በምሥጢርና #በግልጽ እየተፈጸሙ ያሉ እንዲሁም #ሊፈጸሙ#የታሰቡ ስውር ደባዎችን እየተመለከትን ሲሆን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ #ምእመናንም ከዚህ በታች ያሉትን የቤተክርስቲያን ጥያቄዎች ያለምንም ማመንታት በመግለጽ አቋሙን ሊያሳይ ይገባል።

1. #መንግሥት የተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት #አሳንጾ ሊያስረክብ ይገባል

2. በቤተክርስቲያን ላይ ከሩቅም ከቅርብም በመሆን ውድመት #እየፈጸሙ ያሉ ሰዎች #ሊጠየቁ ይገባል

3. መንግሥት እስከአሁን በዝምታው እርምጃ ባለመውሰዱ #ባደረሰው የቤተክርስቲያን ውድመት #በይፋ#ይቅርታ መጠየቅ አለበት

4. እንዲሁም ሌሎች ቤተ እምነቶችም #በተከታዮቻቸው #ላደረሱት ግፍ በይፋ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል

5. እስከአሁን ለደረሰው #እልቂት መንግስት #ካሳ ሊከፍል ይገባል

6. የኦርቶዶክስ ተዋሕዶን ቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ባለው ግፍ ፤ #የፖለቲካ #ፓርቲዎች የተቃውሞ መግለጫ ሊያወጡ ይገባል። ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የማያከብር ፖለቲከኛ #ሊወክለን #አይገባም

7. አክራሪና ዘረኛ ጋዜጠኞች ላይ መንግሥት #እርምጃ ሊወስድ ይገባል

8. ቅዱስ ሲኖዶስም አብያተ ክርስቲያናት ላይ የሚደርሰውን መከራ ማስታገስ የሚችል #አደረጃጀት#ሊፈጥር ይገባል

9. #መንግሥት አስጊ በሆኑ አካባቢዎች ለቤተክርስቲያንና ለምእመናን #ከለላ ሊያደርግ ይገባል

10. ከሥር ያሉ ባለሥልጣናትና አመራሮች ላይ ክትትል ሊደረግ ይገባል

በጥቅሉ ሰማዕትነትን አጉልታ በማየት ዋጋ የምትሰጥ ቤተክርስቲያን የሚደርስብንን መከራ ደስታችን እንዲሆን የምታሳስበን ቢሆንም ቅሉ በአእምሮ ሕፃናትንና በመከራችን ሁሉ ያየነውን የሰማነው እየመሰከርን የተሳሳተውን እያረምን ግፈኛውን እየተቃወምን ልንቆይ የግድ ይለን።

ነገሥታትን አሕዛብን በሥራቸው እየገሰጹ እየተቃወሙ በመከራ ኖረው ይህችን ርትዕት ሃይማኖት ያቆዩልንን የአባቶቻችንን አሠረ ፍኖት ተከትለን ለቤተክርስቲያናችን #ዘብ ጠበቃ #ልንቆም ይገባል።

በመሆኑም በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሰንበት ት/ቤቶች አንዱ የሆነው ሰንበት ትምህርት ቤታችን አሁን በቤተክርስቲያን ላይ እየደረሰ ያለውን #ሴራና መከራ #ከማውገዝ በተለየ አጥቢያ ከሚገኙ ማኅበራትና ሰንበት ትምህርት ቤቶች ጋር በጥምረት በመሥራት በተለያዩ #መንገዶች አቋማችን #የምናሳይ ሲሆን ትልልቅ ጉባኤያትን በመዘርጋትም አሁን #ቤተክርስቲያናችን ላይ #እየተፈጸመ ያለው #ሴራ ለምእመናን #መረጃ በመሥጠት ምእመኑን በተለይ ወጣቱን የማንቃት ሥራ የምንሠራ መሆኑን እንገልጻለን።

መግለጫውን ያዘጋጁ የሥራ አመራር አባላት

1. ላእከ ወንጌል ዳርዮስ ፍቃዱ
2. ዲ/ን ሞገስ አብርሃም
3. ዲ/ን ኃይሉ ብርሃኑ
4. መምህር ጌታቸው ወልዴ
5. መምህር ገረመው ገ/ማርያም
6. አቶ ሙሉጌታ ፈቀደ
7. አቶ አብርሃም አበበ

ግልባጭ:-

. ለአ/ኅ/ደ/ም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ፤
. ለአ/ኅ/ደ/ም ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ጽኅፈት ቤት፤
. ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
. ለቂርቆስ ፣ ልደታ እና አዲስ ከተማ ክፍላተ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት፤
. ለሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፤
. የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት፤
. የቂርቆስ፣ልደታ እና አዲስ ከተማ ክፍላተ ከተማ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ኅብረት፤
. ለማኅበረ ቅዱሳን፤
. ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ስርጭት ድርጅት(EOTC)፤
. ለአጋር ሰንበት ትምህርት ቤቶች፤
. ለቂርቆስ ክፍለ ከተማ አመራሮች፤
. ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.