Breaking News
Home / Amharic / ታላቅ የምስራች – እስክንድር በአብዛኛው የፋኖ እዝ ተመርጧል ! Majority Rule ! 5 out of 9 !

ታላቅ የምስራች – እስክንድር በአብዛኛው የፋኖ እዝ ተመርጧል ! Majority Rule ! 5 out of 9 !

ታላቅ የምስራች – ለመላው የአማራ ህዝብና ለመላው የኢትዮጲያ ህዝብ

የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት ዛሬ አመራሩን በመምረጥ መመስረቱን በይፋ አበሰረ-‼️
አርበኛ እስክንድር ነጋንም መሪው በማድረግ በአብላጫ ድምጽ መርጧል ‼️‼️

*** ወንድወሰን ተክሉ***

ከሰኔ 12 ቀን 2016 እስከ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ሲካሄድ የሰነበተው የአማራ ፋኖ ማእከላዊ እዝ AMHARA Fano Central Command አመራር የመምረጥ ሂደት በስኬት ተጠናቌል ‼️‼️‼️

የአማራን ፋኖ በአንድ ድርጅት ስር አደራጅቶ ለማዋቀር ከሰኔ 12 ቀን 2016 ጀምሮ ሲካሄድ የቆየው የስብሰባ ሂደት ዛሬ ሀምሌ 9 ቀን 2016 ዓ ም የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን በመመስረት ስብሰባውን በስኬት ማጠናቀቁን አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቌል፡፡
አራት ያህል አዘጋጅ ኮሚቴ 1ኛ – ፋኖ መምህር ምንተስኖት ከአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት 2ኛ-አርበኛ አንተነህ ድረስ ከአማራ ፋኖ የጎንደር እዝ 3ኛ- ፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናውና 4ኛ- ፋኖ መስፍን የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ የዚህ ስብሰባ አስመራጭ ኮሚቴነታቸው ለአንድ ወር ያህል ሲካሄድ የቆየውን ስብሰባ ሂደት በመግለጽ የዛሬውን የስብስባውን ፍጻሜን በመግለጽ ለመላው የተከበረው የአማራ ህዝብ አንድ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት የሚባል ሀይል መቌቌሙን ገልጸው እንኳን ደስ ያለህ ሲሉ የደስታ መል እክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
🔥 የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት መስራች አባላት :-
🔥 1ኛ- የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ
🔥 2ኛ- የአማራ ፋኖ በጎጃም
🔥3ኛ- የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ
🔥4ኛ- የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሰራዊት
🔥 5ኛ- የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ
🔥6ኛ- የአማራ ፋኖ በጎንደር
🔥 7ኛ- የአማራ ፋኖ በሸዋ መሆናቸውን ከተሰራጨው አጭር ጋዜጣዊ መግለጫ ማወቅ ተችላል፡፡
እነዚህ ሰባት የአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች በጋራ ሆነው ለአንድ ወር ያህል ያደረጉትን እልህ አስጨራሽ ስብሰባን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት በመመስረትና አርበኛ እስክንድር ነጋንም የዚህ ድርጅት መሪ አድርገው በአብላጫ ድምጽ መምረጣቸውን በማሳወቅ ለመላው ህዝባችን እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል፡፡
በእኛም በኩል ወዳጅም ደስ ይበልህ ጠላትም እፈር ከአሁን በኃላ ይህንን መላውን የአማራን ፋኖ አደረጃጀቶችን አካቶ የያዘውን የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅትን በመያዝ አማራዊ አንድነታችንን አጠንክረን በአንድ የተባበረ አማራዊ ሀይል ያለንበትን የህልውናን ትግል በአጭር ግዜ ውስጥ ለድል በማብቃት ሁላችንም በጋራ ተባብረንና ተረባርብን ነገዳዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ በአጽንኦት መግለጽ የምንወደውና መላውን ህዝባችንን ልናሳስብ የምንፈልገው በዚህ አንድ ወር ውስጥ የተከሰቱትን ውስጣዊ ሽኩቻዎችን እንደ አንድ የምርጫ ጊዜ እንደተፈጸመ ጤናማ ፉክቻና ሽኩቻ በመቁጠር ከዛሬ ቀን ጀምሮ በልዩነቶቻችን ላይ ማተኮሩን ትተን በአንድነታችን ላይ ብቻ ያተኮረ የጋራ ስራ እንድንስራ የሚጠበቅብን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ዛሬ በተላለፈው መግለጫ ሰባቱ የአማራ ህዝባዊ ድርጅት መስራች ድርጅቶች በጋራ ሆነው የመሰረቱትን ድርጅትና የዚህም ድርጅት መሪ አርበኛ እስክንድር ነጋ በአብላጫ ድምጽ መመረጡን ከመግለጻቸው ባሻገር ያቀረቡት ዝርዝር የአመራር ስያሜ ስለሌለ ቀጣይ ማብራሪያ እንደሚሰጡን በማመን ልንጠብቅ ይገባል ‼️
ድል ለክንደ ነበልባሉ ፋኖ🔥🔥🔥
ድል ለታላቁ አማራ 🔥🔥🔥
ክብር ለሰማእታቱ 🔥🙏🔥
ድል ለኢትዮጲያ 🔥🔥🔥
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.