Breaking News
Home / Amharic / ታላቅ ህዝባዊ ተቃዉሞ በ አዲስ አበባ

ታላቅ ህዝባዊ ተቃዉሞ በ አዲስ አበባ

#ታላቅ #ህዝባዊ #ተቃዉሞ#አዲስአበባ
(የካቲት 3/2011)
ዉድ ኢትዮጵያውያን አዲስ አበባን ከዘር ጭቆና ነፃ ለማዉጣት በተለይም ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ የአዲስአበባ ህዝብ ከህወሀት ጋር ያደረገዉን ትንቅንቅና የከፈለዉን መስዋትነት መላዉ ህዝብ የሚያዉቀዉ ጉዳይ ነዉ። ባለፉት ሁለትና ሶስት አመታትም #ህወሀትን ሙሉበሙሉ ከ4ኪሎ ለማስወጣት ባደረግነዉ ተጋድሎ የጠፋዉን ህይወትና ንብረት የምንረሳዉ አይደለም። ሆኖም ግን የአዲስአበባ ህዝብ ይሄ ለዉጥ እንዲመጣ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር መስዋት የከፈለ ቢሆንም አሁንም #አዲስ አበባ በዘር ወረርሽኝ ከመወረርና ከመበዝበዝ አልዳነችም።

#አዲስአበባ የሁሉም ኢትየጵያውያን ብሎም የአፍሪካ መዲና ሆና ሳለ የአንድ ጎሳ ይዞታ ለማድረግ እየተደረገ ያለዉን ሴራ ተከትሎ በሚከተሉት ምክንያቶች ህዝባዊ ተቃዉሞ ለማሰማት ተገደናል። እባክዎ መረጃዉን ለሌሎችም ያጋሩ።

1ኛ. #አዲስአበባ እንደሌሎቹ ክልሎች እራስ ገዝ እና የራሷ እንደራሴ ም/ቤት ያላት ሆኖ ሳለ ከህግ ዉጭ ባልመረጥነዉና ባልወከልነዉ #ከንቲባ እየተመራን በመሆኑ፣

2ኛ. የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር ታሪኳንና ማንነቷን አደጋ ላይ በሚጥል መልኩ ለአንድ ብሄር ብቻ በህገወጥ መንገድ መታወቂያ እየታደለ በመሆኑና እስካሁንም ከ30,000 በላይ መታወቂያ በመታደሉ ድርጊቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ለመጠየቅ፣

3ኛ. ከተማችን በርካታ የዉስጥ ለዉስጥ የልማት ችግር እያለባትና በርካታ ዜጎች በድህነት እየማቀቁ ሳለ ከከተማ በጀቱ በቢሊየን ብር ተነስቶ ለኦሮሚያ ከተሞች ልማት እየተሰጠ በመሆኑ

3ኛ. የአዲስአበባ ምስኪን ደሀዎች መኖሪያቸዉ በሰበብ እየፈረሰ በርካታ እናቶችና ህፃናት ጎዳና ላይ በመጣላቸዉ ድምፃችንን ለማሰማት፣

4ኛ. በከተማ ዉስጥ ባሉ የዕምነት ተቋማት በዋናነት በቤተክርስቲያንና በመስጊዶች ይዞታ ጣልቃ በመግባት የተቃጣብንን ረገጣ ለመቃወምና ለማዉገዝ፣

5ኛ. በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች ቅጥር እንዳይፈፀም ተከልክሎ በዝዉዉር ባለሙያና አመራር ከኦሮሚያ እየመጣ እና የከተማ ነዋሪዎችን ባይተዋር እያደረገ በመሆኑ

በአጠቃላይ #የአዲስ አበባን ታሪካዊ ዳራ፣ማንነት፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን በጣሰ መንገድ የአንድ ጎሳ መጨፈሪያ ለማድረግ እየተሰራ ያለዉን የ#ፖለቲካ ሸፍጥ ለመቃወም #እሁድ የካቲት 3/2011 ህዝባዊ ተቃዉሞ የምናካሄድ ሲሆን መላዉ ኢትዮጵያዊ ከጎናችን እንዲቆም እንጠይቃለን።
ሼር ያድርጉት(አዲስ አበቤዎች )

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.