Breaking News
Home / Amharic / ታላቁ እስክንድር በትናንትው ምሽት በጎጃም ቡሬ ዳሞት ወረዳ ተያዘ ::

ታላቁ እስክንድር በትናንትው ምሽት በጎጃም ቡሬ ዳሞት ወረዳ ተያዘ ::

ሰበር መረጃ፦

 


ታላቁ እስክንድር በትላንትው ምሽት እጁ በጎጃም ቡሬ ዳሞት ወረዳ ከተያዘበት ሰዓት ጀምሮ የክልሉ ፕሬዝዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ ሁሉም የክልሉ አመራር “እስክንድር የፈፀመው አንዳችም ወንጀል የለም፣ በወንጀልም አይፈለግም፣ ስለዚህ አሁኑኑ በነጻ ይፈታ” የሚል ውሳኔ ቢያሳልፉም፤ የክልሉ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊና ዐማራ ጠል ነው የሚባለው፤ በተለይም ከዓብይ አህመድ መመሪያ እየተቀበለም የፋኖን ስም በተደጋጋሚ በማጠልሸቱ የሚወቀሰው፤ ከዚህ ሌላ የፋኖ አባላትን ጨምሮ ከ 15 እስከ 20 ሺህ ለሚገመቱ የነቁ ዐማራዎች በሰላም ማስከበር ሽፋን የግፍ እስር ዋና አቅጣጫ ሰጪ መሆኑ የሚነገርለት ሰማ ጥሩነህ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር በመመሳጠር፤ “እናንተ አያገባችሁም የጸጥታ ጉዳይ እኔን ነው የሚመለከተው፤ ከፌደራል መንግስት ጋር ተነጋግሬያለሁ” በማለት በዲስክ መንሸራተት ህመም የሚሰቃየውን ታላቁን የነጻነት ታጋይ እስክንድር ነጋን ለአራዊቱ የኦሮሙማ መንጋ አሳልፎ እንደሰጠው ታውቋል። ፋኖን እና የነቁ ዐማራዎችን ለማጥፋት ከዓብይ ተልዕኮ ወስዶ የሚንቀሳቀሰው የኦዴፓ ምስለኔና የኩሽ ፖለቲካ አቀንቃኙ ሰማ ጥሩነህ፤ የዐማራ ሕዝብ ቁጥር አንድ ጠላት መሆኑ ይታወቅ። ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ የኦሮሙማው ካድሬዎች በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት “ፋኖን ከጎጃም አሰልጥኖ ወደ ወለጋ በመላክ ቀውስ ሲፈጥር የነበረው እስክንድር ነው” በማለት፤ ነውረኛው የዓብይ መንግስት በኦነግ ሸኔ ሽፋን እራሱ የሚፈጽመውን አሰቃቂ የዘር ፍጅት የጄኖሳይድ ወንጀል በሰላማዊው እስክንድር ላይ በማላከክ ለመክሰስ መዘጋጀቱን የሚያሳብቅ አሳፋሪ መረጃ ከወዲሁ እያሰራጩ ነው፤ ባለቤቱ ሰርካለም ፋሲል መታሰሩን እንደሰማች እስክንድር ከአሜሪካ ከተመለሰ በኋላ የስርዓቱ ሰዎች በሕይወቱ እየዛቱ አላሰራ ስላሉት ለጊዜው ወደ ገጠር ገለል ለማለት ማቅናቱን ገልጻ፤ “አውሬ” ላለችው የፌደራል መንግስት ተላልፎ እንዳይሰጥ የዐማራ ክልልን፣ የዐማራ ሕዝብንና የአንድነት ኃይሉን ተማጽና ነበር።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.