Breaking News
Home / Amharic / ተማሪዎቻችንን ልቀቁ !

ተማሪዎቻችንን ልቀቁ !

የታገቱት ተማሪዎች እስካሁን ድምጻቸው አልተሰማም ….

– ህዳር 20/21 የታገቱበት ቀን

– ህዳር 24 አምልጣ የወጣችው ተማሪ መታገታቸውን የተናገረችበት

– ታህሳስ 27 አቶ ተመስገን ጥሩነህ በጋዜጣዊ መግለጫቸው የታገቱ ተማሪዎች እንዳሉ ቁጥራቸውም እስከ 4 እንደሚደርስ ገለጹ

– ጥር 2 አቶ ንጉሱ ጥላሁን ስለታገቱት ተማሪዎች በሰጡት መግለጫ 21 ተማሪዎች መለቀቃቸውንና 6 ተማሪዎች ታግተው እንዳሉ ገለጹ

– ጥር 8 የኦሮሚያ የኮምዊኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወደ ዩኒቨርሲቲ ተመልሰዋል ሲሉ ገለጹ

ይህ ሁሉ ሲሆን ተማሪዎቹ ከመጀመሪያዎቹ ሳምንታት ውጪ ከቤተሰቦቻቸው ጋር አልተገናኙም ተለቀዋል ከተባለ በኀላም ምንም አይነት ማስረጃ ሊገኝ አልቻለም፡፡ ይህ ለምን እነደሚሆንና ቢያንስ የተማሪዎቹ መለቀቅ በግልፅ ታይቶ ነገሮችን ለማብረድ ምንም አልተሰራም፡፡ ይህ አስቸኳይ ፍትህ የሚፈልግ ጉዳይ ነው፡፡ ሁለት ወር ሊሞላቸው የተቃረቡት ለእኚህ ተማሪዎች ምንም አይነት ትኩረት ያለመሰጠቱ ጉዳይ አሳሳቢ ነው፡፡

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.