Breaking News
Home / Amharic / ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አይሮፕላን እንዳይሳፈሩ ተከለከሉ ! ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ !

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ አይሮፕላን እንዳይሳፈሩ ተከለከሉ ! ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለኢትዮጵያ ዲያስፖራ !

ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የጆርጅያና አካባቢው ሀገረስብከት ሊቀጳጳስ ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ለግንቦቱ ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ቲኬት ቆርጠው
ከአትላንታ ወደ ኢትዮጵያ በረራ ለማድረግ ኤርፖርት ሲደርሱ የገጠማቸው ግን እጅግ አስገራሚ ነው ::

ቲኬት የቆረጡት በኢትዮጵያ አየር መንገድ በመሆኑ ቦርዲንግ ፓስ ለመውሰድ ፓስፓርታቸውን ሰጥተው ሲጠባበቁ ቲኬቱ NoGo (Cancelled) እንደተደረገ፣ ቢጫ (Yellow Card) ካርዳቸውም (Deactivate) እንደማይሰራ ( ቢጫ ካርድ አዲስ ከተሰጣቸው ሁለት ወር እንዳልሆነ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል) በዚህ ምክንያትም ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ እንደማይችሉ በኢትዮጵያ አየር መንገዱ ሠራተኛ ተነግሯቸዋል።

ብፁዕነታቸውም ለምን እንዲህ እንደሆነ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞቹን ብሎም ኃላፊዎቹን ቢጠይቁ ትዕዛዙ ከላይ እንደሆነ የተፈጠረውንም ምንም እንደማያቁት ቢነገራቸውም አምባሳደሩ ጋር ደውለው ቢጠይቁም የአምባሳደሩ ምንም እንደማያውቁ እና አጣርተው ለብፁዕነታቸው በስልክ እንደሚያሳውቁ ምላሽ ቢሰጡም እስካሁን ማንም ምላሽ ሳይሰጣቸው ዛሬ ኤርፓርት ተጉላልተው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።

ማሳሰቢያ!
የዲያስፓራ አባል የሆናችሁ ወደ ኢትዮጵያ እንዳትሄዱ። ልትታሰሩና ልትታገቱ ትችላላችሁ።
MEMBERS OF ETHIOPIAN DIASPORA ARE ADVISED NOT

TO TRAVEL TO ETHIOPIA BECAUSE, IT IS VERY UNSAFE
AND YOU CAN BE ARRESTED OR DISAPPEAR.

© ኢትዮ ቤተሰብ

 

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.