***
ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም የደቡብ ጎንደር ዞን አመራሮች ላይ የግድያ ወንጀል ለመፈፀም አስባችሁ ነበር በሚል በፖሊስ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የንቅናቄያችን የደቡብ ጎንደር ዞን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ም/ሰብሳቢ አቶ ቢሰጥ አሰፋ እና የደርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አዱኛ ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር፡፡
በዕለቱ በዋለው ችሎትም ፓሊስ አሉኝ ያላቸውን ምስክሮችና የተጠርጣሪዎችን የስልክ ልውውጥ ከኢትዮ ቴሌኮም ያላቀረበ ሲሆን ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠውም ጠይቋል። ተጠርጣሪዎች በበኩላቸው ፓሊስ በተሰጠው ጊዜ አለኝ የሚለውን ማስረጃ አለማቅረቡን ገልፀው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ሊሰጠው አይገባም ሲሉ ተቃውመዋል።
የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው የደብረታቦር ወረዳ ፍርድ ቤት የፓሊስን የተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ በ5ሺህ ብር ዋስ እንዲፈቱ ውሳኔ የሰጠ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹም ዛሬ ከእስር ተፈተዋል።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!