በዐቢይ አሕመድ የሚመራው የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመው ያለው ወረራ!
ይህን ከታች የምታነቡትን ጉድ ተረኛነት እያላችሁ ተረኛነትን አታቃሉት። ተረኛነት እየተባለ ለሚቀረበው ነገር ማነጻጸሪያ እየሆነ የሚቀርበው ወያኔ ባለተራ በነበረበት ዘመን “የኢትዮጵያ” መከላከያ ሠራዊትን፣ “የኢትዮጵያ” አየር መንገድን፣ “የኢትዮጵያ” ስደተኞች ጉዳይ አስተዳደርን፣ ወዘተ የባንክ ሒሳብ ወደ ትግሬ ባንክ አላዛወረውም። የዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ የሕወሓትን የነውረኛነት፣ የተረኛነትና የአፓርታይድ ክብረ ወሰን የሰበረው በመንግሥትነት በተሰየመ በአስር ወሩ ነው።
ይህ ከታች የምታነቡት የዐቢይ አሕመድ የኦሮሙማ የአፓርታይድ አገዛዝ በኢትዮጵያ ላይ እየፈጸመው ያለው ተግባር ጦርነት የሚያስነሳ ወረራ ነው።
ዐቢይ አሕመድ ይህን ሁሉ ነገር ሲፈጽም የብሔራዊ ባንክ ገዢ ተደርጎ የተጎለተው የብአዴኑ ግዑዝ ይናገር ደሴ እና የጉዳዩ ባለቤቶች የሆኑት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦርድ አባላት አንዳች የሚያውቁት ነበር የለም።
ዐቢይ አሕመድ “የአገር መገለጫ ምልክት ነው” ሲለን የነበረውን “የኢትዮጵያ መከላከያ” ንብረት በኦሮሞ እጅ ተጠቃሎ እንዲቀመጥ ያደረገው መከላከያ ተብዮውን ለአንድ ክልል ጥቅም እንዲሰራ ለማድረግ ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ስም የሚጠራውን መከላከያ ሠራዊት በሚመለከት ከኢትዮጵያዊው ተቋም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በላይ የኦሮሞን ባንክ እንደሚያምን፤ ከኦሮሞ ውጭ ሌላውን ኢትዮጵያዊ እንደማያምን እየነገረን ጭምር ነው።
ይህ ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ስም የሚጠራውን የመከላከያ ሠራዊት ንብረት ለኦሮሞ ጥቅም በተቋቋመ ባንክ ውስጥ ተጠቃሎ እንዲቀመጥ በወሰነው ውሳኔና ሕወሓት የሰሜን ዕዝ ተብዮው የትግራይን ጥቅም ሊያስጠብቅ አይችልም ብሎ ሲያስብ በዕዙ ላይ ወረራ ፈጽሙ ጦሩ እንዲበተን ባደረገው ጥቃት መካከል ልዩነት የለም። ሁለቱም ተግባራት የአገር መገለጫ የሚባለውን መከላከያ ሠራዊት አፍርሶ ለአንድ ክልል ጥቅም እጅ የሰጠ ቅልብ ጦር ለማቋቋም ያለሙ ናቸው።