Breaking News
Home / Amharic / በተጉለት፣ መንዝ፣ ኤፍራተና ግድም፣ በቀወት፣ ጣርማበርና ምንጃር ከአብን ሰራዊትከርመን እነሆ ተከተናል::

በተጉለት፣ መንዝ፣ ኤፍራተና ግድም፣ በቀወት፣ ጣርማበርና ምንጃር ከአብን ሰራዊትከርመን እነሆ ተከተናል::

ሳምንቱን ስንሸኘው!
በተጉለት፣ መንዝ፣ ኤፍራተና ግድም፣ በቀወት፣ ጣርማበርና ምንጃር ከአብን ሰራዊትና ከሰፊው ህዝባችን ጋር ለአንድ ሳምንት ያህል ስንመክር ከርመን ወደ በራራ ተመልሰን በምስኪኗ ቤታችን እነሆ ተከተናል።

ይህች ምስኪኗ ቤታችን ደግሞ ባለታሪክ ናት! ትላንት በሀማደ ዘመነ መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ ታውጆ ስብሰባ ማድረግ ክልክል በነበረበት ዘመን በቅድመ አብን የትግል እንቅስቃሴአችን የበኩሏን አበርክታለች….አራት ያህል ውይይቶችንም አስተናግዳለች!
——————-
ታዲያ ሰሞኑን በምንጃር አረርቲ በህዝባችን መሀል ተከስተን በነበረባቸው ቀናት እንዲህ ሲባል ሰማን፦

“ቡልጋንም ተጋኘው ክፍቱን አደረና
ከሰምን ተጋኘው ክፍቱን አደረና
ምንጃርን ተጋኘው ክፍቱን አደረና
ሸንኮራን ተጋኘው ክፍቱን አደረና
ወንዱ አስማረ ዳኘ መክደኛው ጠፋና!”
————-
“የመትረጌስ ጌታ የዲሚፍተሩን
እንዴት ነህ በሉልኝ፣ ወዴት ነህ በሉልኝ አስማረ ዳኘን።”
————-
በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የተጠለሉ አዛውንትና ህፃናትን ጎብኝተናል። ብዙወቹ እነዚህ ተፈናቃዮች በወለንጪቲ ከተማ ተወልደው ያደጉ የአካባቢው ሰወች ነበሩ፤ ግን ደግሞ “ኦሮምያ” በሚባል ክልል ውስጥ ተካለሉና ይሄው ዋጋ ይከፍላሉ።
ቤታቸውን ቀለም እየቀባ “ይህ ቤት የኔ፣ ይህኛው ግቢ የኔ….” የሚልና ድፍን ከተማ ላይ እጣ የሚጣጣል ነውረኛ ግሪሳ ነው አሉ…
“መገን አንተ! ወዴት ታደርሰን ይሆን!” አሉ ሸኩ!
———-
ወሬና ተግባር ሲለያዩ “ቃል አባይነት” ወይንም hypocrisy ይባላል። ስለሆነም ኢትዮጵያን እንወዳለን፣ ለህዝቦቿ አንድነትም እንቆማለን የሚል መንግስታዊ አካል ይህንን እንዲያረጋግጥ ይጠበቃል። ከዚህ በተረፈ ያው የአዳራሽ ውስጥ ወሬና ባዶ ጭብጨባ ሆኖ ይቀራል። አለቀ!!
———–
ለማንኛውም የሀገራችን ችግሮች ምንጩ እንደተባለው ፌስቡክ ላይ ሳይሆን ከተበላሸ አመለካከትና ከበሰበሰ የፖለቲካ ስራ ነው። ፌስቡክ ላይ የዜጎች መፈናቀል ዜና የሚወጣበት እንጅ ማፈናቀል የሚካሄድበት አይደለም። ይሄው ነው።
————-
(የሰሜን ተራሮችስ እንደ ጣናና ላሊበላ ሁሉ የአማራ ጉዳይ ይሁን ተብሎ እየተተወ ይሆን??)
መልካም ሳምንት!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.