Breaking News
Home / Amharic / በማንነቴ ምክንያት ከስራ እና ከደሞዝ እንድታገድ ተደርጊያለሁ።

በማንነቴ ምክንያት ከስራ እና ከደሞዝ እንድታገድ ተደርጊያለሁ።

ጋዜጠኛ ደሳለው ጥላሁን
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
ነሐሴ 10 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ
በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ውስጥ ከ 10 ዓመት በላይ በጋዜጠኝነት እና በተለያዮ የስራ ኃላፊነት ደረጃዎች ላይ አገልግሏል፤ በቅርቡም ከሐምሌ 04 ቀን 2011 ዓ.ም ከሚሰሩበት ተቋም ከስራ እና ከደሞዝ ኢ-ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንደታገደ ይገልፃል።
ጉዳዮን በማስመልከት የአማራ ሚዲያ ማዕከል አቶ ደሳለው ጥላሁንን ስቱዲዮ ድረስ በመጋበዝ ቆይታ ያደረገ ሲሆን በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ውስጥ የማያቸውን የመልካም አስተዳደር እና ብልሹ አሰራሮች እንዲስተካከሉ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ የግሌን ጥያቄና አስተያየት በማቅረብ ስሞግት ከዚህም በተጨማሪ የበላይ አካሎች ጋር በመሄድ እንዲስተካከል ስጥር ነበር ብሏል።
ጋዜጠኛ ደሳለው እንዲሚለው ተቋሙ የትምህርት እድል ሰቶኝ እሱንም አጠናቅቄ ስመለስ ለትምህርት ደረጃዬ የሚመጥን የስራ ደረጃ እንዳገኝ ተቋሙ ባወጣው የስራ ደረጃ እድገት ማስታወቂያ ወጥቶ ተፈትኜ ውጤቱን እየጠበኩ ሳለ በድንጋት ፈተናው እንደተሰረዘ እና ማግኘት የሚገባኝን ጥቅም እንዳላገኝ ተደርጊያለሁ ብሏል።
የድርጅቱን ብልሹ አሠራር በመሞገቴና እንዲስተካከል በመጠየቄ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት ዋና ኃላፊ አቶ በቀለ ሙለታን ጨምሮ አብዛኛው የኢዜአ ኃላፊዎች እንዲሁም የበላይ ተጠሪዎች የኦህዴድ ጓድ በመሆናቸው ከዚህም በተጨማሪ የሚያከናውኗቸው ተግባራት ሁሉ ማንነትን መሰረት ያደረገ ተግባር በመሆኑ እንድገለል እና በብሔር ማንነቴ ምክንያት ከስራ ገበታዬ እና ከደሞዜ ታግጃለሁ ብሏል።
ለበርካታ ዓመታት ሳገለግልበት ከነበረበት ተቋም ሞራሌን እና የግል ስብዕናዬን በሚነካ መልኩ በፌዴራል ፓሊስ እና በተቋሙ ጥበቃ ተመናጭቄ እንድወጣ ሆኗል ሲልም ጋዜጠኛው ቅሬታውን ገልጿል።
ጋዜጠኛ ደሳለው ይህንን ጉዳይ እስከጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ድረስ ያሳወቀ ቢሆንም ማንም ትኩረት ሊሰጠው አልቻለም።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ድርጅት በዲስፕሊን ኮሚቴ እየታዬ ነው በሚል ሰበብ ግዜ በመግዛት ከፍተኛ የሆነ የሞራል የስነ ልቦናና የኢኮኖሚ ጫና እየደረሰብኝ ይገኛልም ብሏል።
አቶ ደሳለው ጥላሁን ባለትዳርና የ3 ልጆች አባት ሲሆን ከአስር ዓመታት በላይ ካገለገለበት ተቋም በድንገት ሐምሌ 04 ቀን 2011 ዓ.ም ከስራና ከደመወዝ ታግዶ ከወር በላይ ቢቆጠርም ተጨባጭ መፍትሄ ባለማግኘቱ እሱም ሆነ ቤተሰቡ የከፋ ችግር ላይ ይገኛሉ።
አሁን ላይ ኢዜአ, ገቢዎች, ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በኦነግ ተወረዋል
ዘገባው :- Amhara media center 

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.