Breaking News
Home / Amharic / ፋኖን እርዱ – በመተማ ወረዳ የሱዳን ጦር እና የተደራጁ የቅማንት ሽፍቶች…

ፋኖን እርዱ – በመተማ ወረዳ የሱዳን ጦር እና የተደራጁ የቅማንት ሽፍቶች…

በመተማ ወረዳ የሱዳን ጦር እና የተደራጁ የቅማንት ሽፍቶች በነዋሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ግድያ፣ ዝርፊያ እና እገታ እየፈፀሙ መሆኑ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 9 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ የሱዳን ጦር እና የትሕነግን አላማና ተልዕኮ እያስፈፀሙ ያሉ የቅማንት ኮሚቴ አባላትና ያደራጃቸው ሽፍቶች በነዋሪዎች ላይ ተደጋጋሚ ግድያ፣ ዝርፊያ እና እገታ እያደረሱ መሆኑ ተገልጧል። የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት በ2 ቀን ልዩነት ብቻ 13 አማራዎች በመኪና ላይ እገታ እና አፈና ተፈፅሞባቸዋል። የቅማንት ኮሚቴ እና ድጋፍ የሚሰጣቸው የተደራጁ ሽፍቶች መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ሲወጣ አሸባሪው ትሕነግ መቀሌን ተቆጣጠረ በማለት በሌንጫ አካባቢ በከፍተኛ ጭፈራና ከበሮ ድለቃ አካባቢውን ሲረብሹ መሰንበታቸው ተገልጧል። ከሰሞኑም ትሕነግ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ተከትሎ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በመፈፀም በተለይም አማራውን እየለዩ በሁለንተናዊ ዘርፍ በማዳከም ላይ እንደሚገኙ የአካባቢው ምንጮች ተናግረዋል። ሀምሌ 3 ቀን 2013 ከሽንፋ ወደ ገንዳ ውሃ በመለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ሲጓዙ የነበሩ 6 ተሳፋሪዎችን ኩሊት በተባለ ቀበሌ በማገት ዘርፈዋል፤ ሮጦ ካመለጠው ከረዳቱ ውጭ ሁሉንም አግተው ወደ ጫካ ወስደዋል። የቁጥር 4 ባለሃብት የሆኑት የአቶ አስምሮም ሾፌርን ጨምሮ ነው 6 ሰዎች የታገቱት። ይህኛው እገታ የተፈፀመው በተመሳሳይ ስፍራ 7 አማራዎች ከመኪና ላይ ታፍነው በተወሰዱ በ2ኛ ቀኑ መሆኑ ተገልጧል። በድምሩ 13 አማራዎች ታግተው በሽፍታው ቡድን ተወስደዋል። ከመካከላቸው ልጃቸው የታገተባቸው አቶ ይመነ ወርቁ የተጠየቁትን 180 ሽህ ብር ከፍለው ልጃቸው ቢለቀቅም፣ በሚያሳዝን መልኩ ብሩን ከተቀበሉ በኋላ አቶ ይመነን አግተው እንደወሰዷቸው ተነግሯል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሊያስፈትኑ ወደ አካባቢው ባቀኑ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ተኩስ ከፍተው በህይወትና በአካል ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ይታወቃል። የወያኔ ተልዕኮ አስፈጻሚዎችና የሱዳን ጦር በህዝብ ላይ እያደረሱት ያለውን የችግሩን ስፋት ተረድቶ መንግስት አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈልግለት ተጠይቋል። የሱዳን ጦር ከካሃዲ የቅማንት ሽፍቶች ጋር በመተባበር ሀምሌ 3 ቀን 2013 በመርትራድ ኢንዲቪሎ አካባቢ ተኩስ በመክፈት ቄስ አስምሮ አብዋ የተባሉ ባለሀብትን፣ በማግስቱ ደግሞ ደግአደረገ የተባሉ ባለሃብትን ካምፕና የመሀሙዴ ሁሴንን ትራክተርን አቃጥለዋል። ለአማራው መብት፣ ጥቅምና ፍላጎት መከበር ውድ ህይወቱን አሳልፎ የሰጠው የመቶ አለቃ ደጀኔ መንግስቱ ባለቤትን የወ/ሮ የሽናት ሽጉጥን ትራክተርም ዘርፈው መውሰዳቸው ተሰምቷል።
 

Source: Link to the Post

 

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.