Breaking News
Home / Amharic / በህግ ማስከበር ዘመቻ ስም ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች ስም ዝርዝር !

በህግ ማስከበር ዘመቻ ስም ታፍነው የተወሰዱ ሰዎች ስም ዝርዝር !

ከድርጅቱ አመራሮች የግል ገፅ እንደምንረዳው እስካሁን በእስር ላይ እንደሆኑ የተረጋገጠ የአብን አመራሮችና አባላት ፣ አብዛኞቹ ወደ ፍርድ ቤት ገና አልቀረቡም። ብዙዎች ድብደባና እንግልት የደረሰባቸው ሲሆን ፣ የት እንደተወሰዱ የማይታወቁም አሉበት።
የአብን ስራ አስፈፃሚ እንደ አንድ አካል የጋራ መግለጫ እንኳን ማውጣት እንዳልቻለ እያየን ነው። በአማራ ህዝብ ላይ የሚደረገውን አንገት የማስደፋት ዘመቻ በዝምታ ይሁንታ ሰጥቶታል። የፋኖን ስም እንኳን ለማንሳት የተጠየፈ ድርጅት ሆኗል።ይህ ሁሉ ወረራ በአጠቃላይ መዋቅሩ ላይ ሲፈፀም ፓርቲው እንደ ድርጅት ያቀረበው አቤቱታም ሆነ መግለጫ የለም።
ስራ አስፈፃሚው በምንደኞችና ኤሳውያን በገሀድ ሲጠለፍ ፣ የበላይ ተቆጣጣሪው የሆነው የኦዲት ኮሚሽኑ ምን እየሰራ ነው? ማዕከላዊ ኮሚቴውስ በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት የንቅናቄውን የአፋኝ አጋርነት እንዴት ከዳር ቆሞ ያያል? ነገሩን ከወዲሁ በኃላፊነት መቀልበስ ካልተቻለ በኋላ ጣት መጠቋቆም አያዋጣም !
አሁንም የፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ እስኪደረግ ድረስ እጅ አጣጥፎ መቀመጥ በአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመ ታላቅ ኃጢአት ይሆናል። ስለሆነም የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ :-
1. ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚው የአማራ ህዝብ አደራን በዚህ ክፉ ወቅት ችላ የማለቱንና ፓርቲው የጣለበትን ኃላፊነት ያልተወጣበትን ማብራሪያ መጠየቅ ፤
2. ከመንግሥት ጋር እንሰራለን ብለው ሥልጣን የተቀበሉ አመራሮችን በዚህ መንግሥታዊ አፈና ውስጥ የነበራቸውን ድርሻ መመርመርና ከእንግዲህም ሚናቸው ከታፋኙ ወይም ከአፋኙ መሆኑን እንዲለዩ ማድረግ ፤
3. በቅርቡ እስከሚደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ድረስ የሥራ አስፈፃሚውን በትኖ አዲስ የሽግግር አስፈፃሚና የጉባኤ አመቻች ኮሚቴ መሰየም አለበት።
እስካሁን በህግ ማስከበር ዘመቻ ስም ታፍነው በእስር ላይ እንደሆኑ ከተረጋገጠ የአብን አመራሮችና አባላት ውስጥ የተፈቱት ሁለት ብቻ ናቸው። ከቀሪዎቹ አብዛኞቹ ገና ወደ ፍርድ ቤት አልቀረቡም። ብዙዎች ድብደባና እንግልት የደረሰባቸው ሲሆን ፣ የት እንደተወሰዱ የማይታወቁም አሉበት።
============
1. ዶ/ር አያሌው ታለማ – (ደቡብ ወሎ ፣ ደሴ) ፤
2. አሸናፊ አካሉ – (ምዕራብ ጎጃም ፣ ም/ሊቀመንበር) ፤
3. ግዛቸው መንበር – (አዋበል፣ ም/ሊቀመንበር ፣ ከእስር ተፈትቷል) ፤
4. ገናናው አትንኩት – (ዳንግላ ወረዳ ፣ ሊቀመንበር/ሰብሳቢ) ፤
5. እንዳላመማው ዳኜ – (ምሥራቅ ጎጃም ፣ ባሶ ሊበን የጁቤ ፣ ወጣቶች ጉዳይ) ፤
6. ፈንታ ሉሌ – (ምሥራቅ ጎጃም ፣ ባሶ ሊበን የጁቤ ፣ የህ/ግነንኙነት) ፤
7. ነጋሽ ጌትነት – (ምሥራቅ ጎጃም ፣ ባሶ ሊበን የጁቤ ፣ ንቁ አባል ) ፦ በወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማርተዋል ክፉኛ የተደበደበ ፤
8. አለኸኝ ዋሌ – (ደብረ ኤልያስ -የፅ/ቤት ሀላፊ) ፤
9. ምኒሻው አባተ – (ስናን ፣ አረቡ ገበያ ፣ አባል) ፤
10. አስማማው ሞላ – (አማኑኤል ፣ አመራር) ፤
11. አለሙ ተመስገን – (አዊ ዞን ፣ አየሁ ጓጉሳ ወረዳ፣ አባልና የምርጫ ታዛቢ የነበረ) ፤
12. እንዳለው አዲስ – (አዊ ዞን ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ አባልና የመተከል አማራ አስመላሽ ኮሚቴ የቦርድ ሰብሳቢ) ፤
13. አሱባለው ባይህ – (ዳንግላ ፣ የቀድሞ የአብን የህዝብ ግንኙነት) ፤
14. ተስፋዩ ባይህ – (የዳንግላ ወረዳ የምክር ቤት አባል ፣ የሰባ ዓመት አዛውንት) ፤
15. ፍፁም አይገኝ – (ዳንግላ ወረዳ ፣ አባል) ፤
16. አማረ ተመስገን – (አዊ ዞን ፣ አዘና ወረዳ ፣ አባል) ፤
17. ጌትነት አዱኛ – (ቲሊሊ ፣ የወረዳ ሰብሳቢ) ፤
18. ኢንጂነር ብርሃኑ ስለሽ – (ማዕከላዊ ጎንደር ፣ አመራር) ፤
19. አገኘሁ ወርቄ ጎባው – (ደቡብ ወሎ ፣ መካነ ሰላም ፣ አባል) ፤
20. አባይ አረዳ – (ጎንደር ከተማ ፣ አባል )፤
21. ደግአረገ ዋለ – (ማርቆስ ፣ ደብረ ኤልያስ ፣ የአብን አባልና የምርጫ እጩ ) ፤
22. ንጉሥ ዓለማየሁ – (ጎንጅ ቆለላ ፣ ሰብሳቢ፣ ከእስር ተፈትቷል) ፤
23. ፈንታ ሉሌ – (ምስራቅ ጎጃም ዞን ፣ ባሶ ሊበን ወረዳ) ፤
24. ነጋሽ ዳኜ – ( ምስራቅ ጎጃም ዞን ባሶ ሊበን ወረዳ) ፤
25. አወቀ ካሳሁን – (አዊ ዞን ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ ሰብሳቢ) ፤
26. ፍስሐ ነጋ – (አዊ ዞን ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ) ፤
27. ታደሠ አስማማው – (አዊ ዞን ፣ ጃዊ ወረዳ ፣አባልና የምርጫ ታዛቢ) ፤
28. አጃነው ስሜነህ – ( አዊ ዞን ፣ ጃዊ ወረዳ ፣ አባልና የምርጫ ታዛቢ እንዲሁም የመተከል አማራ አስመላሽ ም/ሊቀመንበር)፤
29. ማስሬ ካሳው – (ደቡብ ጎንደር ዞን ፣ ነፋስ መውጫ የቀበሌ 02 የአብን መሠረታዊ ድርጅት ሰብሳቢ)፤
30. ታከለ ዋጋው – (ደቡብ ወሎ ዞን ፣ ተንታ ወረዳ ፣ ሊቀመንበር እና የምርጫ ተወዳዳሪ)።
31. ጋሻው ተገኘ – (ምዕራብ ጎንደር ዞን ፣ መተማ ከተማ ሰብሳቢ )።
 
በህግ ማስከበር ስም የሚደረግ መንግሥታዊ አፈና በአስቸኳይ ይቁም ❗️
 

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.