Breaking News
Home / Amharic / በህወሀት እና ኤርትራን በሚመራው ፓርቲ (ህግደፍ) መሀል እርቀ-ሰላም—

በህወሀት እና ኤርትራን በሚመራው ፓርቲ (ህግደፍ) መሀል እርቀ-ሰላም—

በህወሀት እና ኤርትራን በሚመራው ፓርቲ (ህግደፍ) መሀል እርቀ-ሰላም ለማውረድ ያሰበ ጉዞ ሰኞ ወደ ኤርትራ ሊደረግ ነው!

በህወሃትና ህግደፍ መሀል አለ የተባለውን ጥርጣሬ እና አለመግባባት ለመቅረፍ ያሰበ ጉዞ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ህብረት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ጠቅላይ ፅ/ቤት፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት እና የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮችን ያቀፈ ቡድን ወደ አስመራ ሰኞ እንደሚጓዝ ዛሬ ተገልፁዋል። የሚድያ ተወካዮች፣ አርቲስቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አክቲቪስቶች እና ታዋቂ ግለሰቦች ቡድኑን ተቀላቅለው እንደሚጓዙ የፕሮግራሙ አዘጋጆች ዛሬ ተናግረዋል።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.