Breaking News
Home / Amharic / በሀገራችን 147 ፓርቲ አለ ግን ገዥውን ወያኔ የራስ ምታት የሆነበት ለዜጎች መብት የቆመ ውስጤ አብን ብቻ ነው !

በሀገራችን 147 ፓርቲ አለ ግን ገዥውን ወያኔ የራስ ምታት የሆነበት ለዜጎች መብት የቆመ ውስጤ አብን ብቻ ነው !

መንግስት የዜጎችን በየትኛውም አካባቢ የመኖርና ንብረት የማፍራት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን ሊያከብር ይገባል፣
****
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዙሪያ ሱሉልታ ከተማ ልዩ ሰሙ ቀርሳ በሚባል አካባቢ ዛሬ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡00 ጀምሮ ብሔራቸውን መሰረት ተደርጎ እየተለዩ ቤታቸው እየፈረሰባቸው ይገኛል፡፡ በቦታው ብዛት ያላቸው የታጠቁ ኃይሎችን በማስፈር በሰው ኃይልና በሎደር ቤት እያፈረሱ ሲሆን ለምን ብለው የጠየቁ ብዙ ሰዎችም ለእስር ተዳርገዋል፡፡ የተቀሩትም ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ባሉበት ታግተው ይገኛሉ፡፡ ዜጎች በላባቸው ያፈሩትን ኃብትና የሰሩትን ቤት በማንነታቸው ምክንያት ማፍረስና ዜጎችን በክረምት ለጎዳና ህይወት መዳረግ ፍፁም ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም መንግስት ዜጎች በየትኛውም ቦታ በዘር፣ በኃይማኖት እና በማንነታቸው ልዩነት ሳይደረግባቸው የመኖርና ንብረት የማፍራት ሕገመንግስታዊ መብታቸውን በአስቸኳይ እንዲያስከብርና ሰብአዊ ቃውስ እንዳይደርስ የመከላከል ስራ እንዲሰራ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ይጠይቃል።

አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፤ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.