Breaking News
Home / Amharic / ቀጥታ መልእክት ከክርስትያን ታደለ (የህዝብ እንደራሴ) ለአዳነች አቤቤ (የአዲስ አበባ ከንቲባ)

ቀጥታ መልእክት ከክርስትያን ታደለ (የህዝብ እንደራሴ) ለአዳነች አቤቤ (የአዲስ አበባ ከንቲባ)

ሰላም ክብርት ከንቲባ፣
 
በመጀመሪያ ከተማሪ ወላጆችና ጉዳዩ ካሳሰባቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ከሰሞኑ በከተማችን በተፈጠረው የትምህርት ማኅበረሰብ ችግር ዙሪያ ውይይት ማድረጋችሁን በበጎ የምመለከተው ነው።
በመቀጠል ያሉኝን ጥያቄዎች አቀርባለሁ።
 
አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት ዋና ከተማና በሕገመንግስቱ አንቀጽ 49 መሰረት ራሷን ሙሉ በሙሉ የማስተዳደር ነፃነት ያላት ከተማ ነች። ይኼ እውነት በሥራ ላይ ባለው ሕገመንግስት የተቀመጠ ነው። የከተማ አስተዳደሩ የተሻሻለው ቻርተርም ይህንኑ እውነት የሚያስረግጥ ነው። የኦሮሚኛ ቋንቋ በአዲስ አበባ ትምህርት ቤቶች ፍላጎቱ ላላቸው ተማሪዎች መሰጠቱም መጥፎ አይደለም። (እንኳንስና የአገራችንን የራሳችንን የኦሮሚኛ ቋንቋ ቀርቶ ባሕር ተሻግረን እንግሊዝኛን ጨምሮ ልዩ ልዩ ቋንቋዎችን እየተማርን አይደለም ወይ! ) ይሁንና የከተማ አስተዳደሩ በካቢኔም ሆነ በክልሉ ምክርቤት ሳያስወስን፤ የተማሪዎችና ወላጆቻቸው ይሁንታ ሳይታከልበት ተማሪዎችን በግድ አንድን ቋንቋ ተማሩ ማለት ተገቢም፥ ትክክልም አይሆንም። ከዚህ የከፋው ደግሞ የአዲስ አበባ ተማሪዎችን ያለፍላጎታቸውና ከሕግ ውጭ የአንድን ክልል መዝሙር እንዲዘምሩና ሰንደቅ እንዲያውለበልቡ መገደዳቸው ነው። በየትኛው አሰራር ነው ካሪኩለም የሕገመንግስትን ድንጋጌ የሚሽረው? አዲስ አበባ የፌዴራሉ መንግስት ዋና ከተማ ነው ማለት የሁሉም የፌዴሬሽኑ አባላት ከተማ ነው ማለት ነው። የሁሉም በሆነ ጉዳይ ላይ የአንዱን ፍላጎት ብቻ ነጥሎ ማክበር በምን መልኩ ልክ ሊሆን ይችላል? የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ራሱን የቻለ መንግስት አይደለም ወይ? ሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ ሰንደቅ ይውለብለብልን፥ መዝሙር ይዘመርልን ጥያቄ ቢያነሱ ተማሪዎች የአስራ ምናምን ክልሎችን ሰንደቅ ሲሰቅሉና መዝሙር ሲዘምሩ ትምህርት በምን ትርፍ ጊዜያቸው ሊማሩ ነው? የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰንደቁን ማውለብለብና መዝሙሩን ማስዘመር ከፈለገ ለምን በራሱ ወጪ መሰል ትምህርት ቤቶችን ገንብቶ በራሱ አያስተዳድርም?
ከላይ ያነሳኋቸው መሰረታዊ ግን አስተውሎትን የሚጠይቁ ጥያቄዎችን አመራሩ መመለስ ይኖርበታል። መሰል የአግባብነት ጥያቄዎችን በመመለስ ፋንታ ድክመትን ውጫዊ ማድረግና በግልጽ የአማራ ብሔር ማኅበራዊ እሴቱ የሆነውን ፋኖነነት ያልተገባ ጭቃ መቀባቱ አማራ ጠልነት ነው። ይህ ደግሞ መንግስታዊ ኃላፊነትን ከወሰደ አንድ አመራር የሚጠበቅ ካለመሆኑም ባሻገር ነውርም፥ ወንጀልም ነው። በአመራር ልግመትና ስንፍና የሚጠሩ የሕዝብ ጥያቄዎችን በሙሉ የምዕራባውያን እጅ ያለበት አስመስሎ ማቅረብም ትክክል አይደለም። መሰል ያልተገሩ የአመራር ንግግሮች በዲፕሎማሲው ረገድ አገራችንን ብርቱ ዋጋ አስከፍለዋል። እናም ከዚህ አንፃር ደግመን ደጋግመን ከስሜት በፀዳ መልኩ የኮሚዩኒኬሽም ሥራዎችን ልናደርግ ይገባል።
በተረፈው ሰላም የሁሉም ዜጎች መሻት ነውና፤ ሁላችንም ለጋራ ሰላማችን እንትጋ። በተለይ በአመራር ደረጃ ያላችሁ ሁሉ ግጭትን ከመጥመቅ ትቆጠቡ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
ክርስቲያን ታደለ ፀጋዬ
(የሕዝብ እንደራሴ)
 

Zeleke Demeli

አንች ትናት መተሽ አገር አታተራምሽ ይልቅ የአሁኑን ሳይሆን ነገን አስቢ። ነገሌላክልልይጠይቃል።ዛሬ የጨቆንሽው ትውልድ ገልብጦ ይጥላቹሀል።ወያኔም ለቋል ለስልጣን ሳይሆን ለአገር ስሩ እባካቹህ ነገ መሞታቹህ አይቀርም ገሀነም ስትገቡ ይደረሳቹሀል።ይሄ ሁሉ አለም ቀሪነው አስቡበት ምነው ነፍሳችን በኛነው የሚወሰነው አላቹህ።

Mekoya D Mengistu

ከተማ አስተዳደሩ መንግስትና ህዝብ የሰጠውን ብዙ ሺህ ሀላፊነትና ተግባር አሽቀጥሮ በመጣል የመንደርተኝነትና የዘር ፖለቲካ ሲያቦካ ይውላል። በዚህም የአፍርካ መናኻሪያ የሆነችው ሸገር ከመቼውም ጊዜ በላይ የሌባና የደላላ መፈጫ ሆናለች። ስልጣን የእቃ እቃ መጫወቻ መሆኑ መቆም አለበት። ባስቸኳይ ተጠያቂው አካላት ከታች እስከ ከንቲባው ተጣርቶ ውጤቱም ለህዝብ ይፋ መደረግ አለበት።

Solomon Kehali Andargie

መጀመሪያም ጽፈኛው ፋኖ ምናምን እያልሽ በመርጥሽው ሚድያ ከመበጥርቅሽ በፊት የአዲስአበባ ከንቲባ መሆንሽ ቢያጠራጥርም ከኗሪዎቹ ጋር መነጋገር ነበርብሽ። የጀመራቹህት መንገድ ሀዲዱን እንደሳተ ባቡር አወዳደቃቹህ የከፋ ነው የሚሆነው ። ትንሽ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር እሮጣቹህ ፋኖ ፋኖ አትበሉ። ፋኖ በወንዶች ሜዳ ምሽግ ስባሪ ነው። አሁን የምትበጠረቂበትን ግዜ የሰጠሽ ፋኖ መስዋዕት ሆኖ ነው።

Bekele Coffee Barca

አዲስ አበባ የሁሉም ናት ትሉ አይደል የሁሉም ከሆነች ለምን የአንድ የብሔር ባንዲራ ብቻ ሊሰቀል ለምን አስፈለገ እስከ ዛሬ ድረስ ተደርጎ የማይታወቀውን ለምን ዛሬ ማድረግ አስፈለገ ????

Henok Wondimu

የክልል መዝሙር ሲጀመር ለምን ማዘመሩ አስፈለገ ኢትዮጵያ ያላት አንድ ብሄራዊ መዝሙር ነው ለትውልዱም ማስተማር እና ማሳወቅ የሚያስፈልገው እሱን ነው። ለምን እንደምትጠቡ አይገባኝም? እራሳችሁ በውስጣችሁ ያለው ህውሃት የሰበከው መርዝ ወጥቶ አላለቀም ህብረተሰቡ ከእናንተ አንድ እርምጃ ወደፊት ቀድሟል ወደኋላ ባትጎትቱት ጥሩ ይመስለኛል። እራሳችሁ ውስጣችሁን አጥሩ!!

Tg Mam Vicu Jesus

ጽንፈኛ እራሳችሁ ናችሁ የምታስተዳድሩት የመላው ኢትዮጵያ ዋና ከተማ የሆነችውን አዲስ አበባን መሆኑን እረስታችሁታል በግድ ልትጭኑብን እንጂ እና ማን የናንተን ባንዲራ ይወዳል? ??የኦሮምኛ ቌንቋ ቁቤ ተማሩ ተብለን ከፍለን ከትምህርት ሰአት ውጪ እንማር ነበር ምንም ችግር አልነበረውም አሁን ያለው የኢትዮጵያ ባንዲራ የኦሮሞስ አይደል ወይ ለምንድነው የኦሮሚያ ክልል የሆነው ተደርቦ ሊሰቀል የተፈለገው አረ እንደውም አንዳንድ ቦታ ዋናው ባንዲራ ወርዶ ይሄኛው እየተተካ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው ይሄ ደሞ የናንተ ስራ ነው እንጂ ተቃውሞ የወጣውን ሳይሆን ሊሰቅል የወጣውን ተቃወሙ ነበር …የምትመሪው የሰለጠነ በአንድነት የሚያምን ተከባበሮ አብሮ መኖር የሚወድ ህዝብ ያለበት ከተማ እንጂ እዛ መንደሬ የሆነ በጎጥ የሚያምን ህዝብ አይደለም ህዝቡን በዚህ በአናሳ ጠባብ አስተሳስባችሁ አትበጥብጡት እኛ አንድ ነን ቋንቋ አይለየንም ስንል በጎጥ የሚያምን መሪ እንዴት እዛው የመንደርሽን አስተዳድሪና የወደድሽውን ጫኚ ይሄ የብዙሃን ከተማ ነው አለመታደል እንጂ ሁሉም ከተማ የሁሉም ኢትዬጵያዊ ነበር በእናንተ ነው ይሄ ሁሉ ጉድ የታየው አሁንም እረፊ ይቺ ሰው ሁሉ በጋራ የሚኖርባትች የቀረችንን ከተማ ባይረሳችሁች አታጋቡባት እግዚአብሔር አይምሮአችሁን ይፈውስ ዘረኝነት ትልቅ በሽታ ነው የራስሽ ፍላጎት ሰለሆነ እንጂ ሁሉም ክልል ባንዲራ አለው እድሜው እንኳን አጠረ ኢህአዲግ ደህና አድርጎ በጣጥሶናል የሌላው ክልል ባንዲራ ቢሆን ችግር የለውም ብለሽ አትቀመጪም ዘላለማዊ አይደለም ይሄ ነገ ሌላ ቀን ነው።
 

Mela Queen

ውድ ክብርት ከንቲባ ” ከአዳማ ከንቲባነተዎ ጀምሮ ባለፉባቸው የሥራ ቦታዎች ሁሉበሥራዎ ጥንካሬ ከማደንቃቸው እንስት መሪዎች ግንባር ቀደሟ ነዎት (ብዙ መናገር ልብን ያዘናገል) እንዲሉ አበው የሠሞኑን አነጋገረዎ የወረደና ከርሰዎ የማይጠበቅና (የማልጠብቀው) ሆነብኝ (ክርስቶስ ለሥጋው አደላ) የተባለው ተረት መሠል አባባል አጋጥሞዎ ይሆን? አንድ ነገር ልንገረዎ የኦሮሞን ሕዝብና ቋንቋ የሚጠላ ካለ እራሱንም ኢትዮጵያንም የማይወድ ነው ። ነገር ግን ችግሩ እሱ አይመስለኝም ። ቋንቋው በታሪካዊና አገር በቀልቢተረጎም ማስታማሩ ቢቀጥል ኖሮ እስከ ዛሬ ድረስመላው ኢትዮጵያን ያዳርስና ተመራጪ ያደርገው ነበር ። ሆኖም ነፍሳቸውን ይማርና ፕሮፌሰር አሥራት እንዳሉት (ጥቁር ፈረንጅ) ለመሆን በተውሶ ፊደል መቀጠሉ በራሱ በቋንቋው ባለቤት ነን ባዮች ተፅዕኖ ሥር ወደቀ ። አሁንም በንግግረዎ ባልተለመደ ማድበስበስ ከሕገ መንግሥቱ ባፈነገጠና ለወደፊትም ማቆሚያ ወደሌለው ጥያቄ የሚከት ሃሳብ ከርሰዎ አይጠበቅም (ሌላ ጊዜም አሁንም እንደሚሉት አዲስ አበባ የሁላችንም ነች እንዳሉት የእውነት እንዲሆን የሥሩ! ይመለሱ እንወደዎታለን ይውደደዱን ማሳበቡ አይጠቅምም ።
 

Senayit Grumsew

ወይዘሮ አዳነች: መቼ ነው የተወያየሺው ? ከማን ጋር? ራስሽ ሰዎች እየመረጥሽ ? ዉይይቱ ለምን በቀጥታ በቴሌቪዥን ለሕዝብ አልተላለፈም? ማንን ለማሞኘት ነው?
 

Mamush Desta

በሀገራችን ስንት ቤህረሰባች አሉ የእነሱም መዝሙር ትምህርት ይሰጥ በቆንቆቸው!
 

Melaku Abegaz

“አያ ጅቦ ሳታመኻኝ ብላኝ” እንዳለው ሰውዬ ገና ዛሬ ከአባባሉ ጋር መሰል ነገር አጋጠመን። አዲስ አበባ ከተማ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የፌደራል መንግስቱ መቀመጫ፣ የሁሉም ብሄሮችና ብሄረሰቦች ባህላዊ እና ማህበራዊ እሴቶች የሚንፀባረቁባት ከተማ ነች ካልን አዲስ አበባ ላይ ሁሉም ወገን ከሌላው ጋር ሊያስተሳስረው የሚችለውን ቋንቋ ባህልና ወግ የማስተዋወቅ እና የማዳበር መብት አለው። ከዚህም አንፃር ቋንቋ አንዱ መገለጫ ነው። ስለዚህ አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ክልሎች የብሄር ብሄረሰቦች ቋንቋ በማህበረሰቡ ፈቃድ ቢሰጥ ምንም ችግር የለውም። እንደውም ጠቀሜታው የጎላ ነው። ምክንያቱም ቋንቋ ስንቅ ነው። ቋንቋ ስራ ነው። ቋንቋ ወንዝ ያሻግራል ይባላል። ይሁን እንጅ ቋንቋን ለማስተማር ወይም ለማሳወቅ የቋንቋውን ባለቤት ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የተማሪውን ወይም ቋንቋውን ለማወቅ ፍላጎት ያለውን ማህበረሰብ መብትና ፍላጎት መረዳት እጅግ አስፈላጊ ነው። አዲስ አበባ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ግን ከዚህ በተለዬ ሁኔታ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የአዲስ አበባ ከተማን ህዝብ ለማገልገል በከንቲባነት የተቀመጡ ሳይሆን በኦሮሚያው ፕሬዝዳንት በአቶ ሽመልስ አብዲሳ የተመደቡ በአዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ጉዳይ አስፈፃሚ እስኪመስሉ ድረስ ይህን ያህል በህዝብ ላይ መቆመር እና የማን አለብኝነት ስራ መስራት የበለጠ ዋጋ ያስከፍል እንደሁ እንጅ አንድነትን አያመጣም። ሌላው አዲስ አበባ የሁሉም ብሄሮች እና ብሄረሰቦች ዋና ከተማ ከሆነች ሁሉም ትምህር ቤቶች ውስጥ እንደ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ፍላጎት በሁሉም የብሄረሰብ ቋንቋ ካሪኩለም ተቀርፆ በእኩልነት መሰጠት አለበት እንጅ አቅም አለኝ ወይም ስልጣን ማማ ላይ እኔ ነኝ የወጣሁት በሚል የትዕቢት አስተሳሰብ በኃይል እና በጉልበት ፍላጎትን መጫን አግባብ አይደለም። ከዚህ በተጨማሪም ቋንቋን ማስተማር እና የአንድን ክልል ባንዲራ እና መዝሙርን በግድ እንዲጠቀሙት ማድረግ በማንአለብኝነት እና ህዝብን ከመናቅ የመነጨ የጥጋብ አስተሳሰብ ድምር ውጤት ነው። ክብርት ከንቲባዋ በእውነት ለመስራት ከፈለጉ እና አዲስ አበባ ውስጥ የተለያዩ የብርሄ ብሄረሰብ ቋንቋዎችን ለዜጎች ማስተማር ከፈለጉ ሁሉንም አንድ ሊያደርግ በሚችለው በኢትዮጵያ ባንዲራ እና በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር መጠቀም ይችላሉ። ይህ አይሆንም ካሉና በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙርና ባንዲራ አንወከልም ካሉ ህገ መንግስቱን በማሻሻል የከተማ አስተዳደሩ የራሱን የሆነ መዝሙር እና ባንዲራ እንዲቀርፅ ማድረግ ያስፈልጋል። የአንድን ክልል መዝሙርና ባንዲራ አምጥቶ በግድ ብሄር ብሄረሰቦችን ተጠቀሙ ማለት አግባብነት የለውም። ይህም ብቻ ሳይሆን ቢያንስ ቢያንስ ተማሪዎች እንዲዘምሩት የሚፈለገው መዝሙር ተማሪዎቹ በሚረዱት ቋንቋ በግልፅ ተተርጉሞ መልዕክቱን ሊረዱት ግድ ነው። ይህ ካልሆነ እና ዘማሪው ካልገባው የመዝሙሩ ትርጉም እራሱን እና የመጣበትን ማህበረሰብ የሚያንቋሽሽ፣ የሚሰድብ፣ በአሽሙር ፖለቲካዊ ቃላቶችን ተጠቅሞ ወያኔ አመጣሹን የዳቦ ስም በመስጠትና በመጠቀም የዘማሪውን ማህበረሰብ የሚነካ መሆን እና አለመሆኑን ከተማሪ እስከ ወላጅ ድረስ በግልፅ ማወቅና መረዳት አለባቸው። ከዚህ ውጪ የሆነ ተልዕኮ እና አጀንዳ ማስፈፀም ከፈለጉ ግን ክብርት ከንቲባዋ ወደ ኦሮሚያ ክልል መንግስት መስሪያ ቤቶች በመዛወር እዚያው በመስራት መንግስታቸውን ማገልገል ይችላሉ።
 

Besufikad Desta Mulatu

ፈጣሪ እንዳንች አይነት ከሃዲወችን ከኢትዮጰያ ያጥፋልን ።
 

Mekuriaw Muluken

አሁን ላይ ህዝብን ማወያየቱ መልካም ነው።ነገር ግን ከፈረሱ ጋሪው እየቀደመ ተቸግረናል ማለትም አንድ ነገር ከመተግበሩ በፊት ህዝብን አወያይቶ ፣ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበት፣ ጥናት ተደርጎበት፣ የሚመለከታቸው የአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት ተወያይቶና አምኖበት የተባለው ነገር ተግባራዊ ቢደረግ ለግጭት አይዳርገንም ነበር ። ነገር ግን የአሁኑ መንግስታችን ይህን ከማድረግ ና ህግንና ተቋማዊ አሰራርን ከመከተል ይልቅ ኮሚቴ በማዋቀር እና በአመራሩ ግላዊ ፍላጎት ነገሮችን ሲተገበሩ ይታያል ይህ ደግሞ ግጭት እየቀሰቀሰ አገሪቱን ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል። በመሆኑም መንግስትና አመራሩ የሚነገረውን ሀሳብና አስተያየት ተቀብሎ በህግና ተቋማዊ በሆነ አሰራር አየተመራ አገሪቱን የማያስዳድር ከሆነ የተረኝነት እና የአባገንነት አባዜ ተጠናውቶታል ማለት ነው የጊዜ ጉዳይ እንጂ የአሳዳጊውን የህወሀትን እጣፈንታ እንደሚገጥመው አልጠራጠርም።
 

Bereket Tsega

ክብርት ከንቲባ ጥያቄ:-
ቋንቋ መግባቢያ ነዉ ባንዴራ ማንነት ነዉ ቋንቋን ደግሞ በመማር ብቻ ሳይሆን በመልመድም ይነገራል ስለሆነም የክልሉ ቋንቋ በሚነገርባቸዉ ሁሉ ባንዲራ ያስፈልጋል ወይ? ለምሳሌ አፋን ኦሮሞ ሶማሌ ክልል ቢሰጥ የኦሮሞን ባዴራ ልትሰቅሉ ነዉ ወይ? የሚያደናግር እና የሚያነጋግር አጀንዳ ጀርባዉ ይነበብ አዲስ አበባን ደግሞ ሚያስፈልጋት የኢትዮጵያ ባንዴራ እንጅ የክልል ባንዴራ አደለም፡፡
 

Takele Ashebir

አላማቸው ቀስ በቀስ አድስ እበባ የኛ ነው ለማለት ነው ይህን ባያ�ቡት መልካም ነው ተከባብሮ መኖርን የመሰለ ነገር የለም እራስ ወዳድ ና ስግብግብነት የሚታይበት አካሄድ ነው ብሔራዊ ባንድራችን ሁላችንንም ስለሚወክል እርሱ ብቻ ይውለብለብ!
 

Wondmnew Hunegnew

አዲሥ አበባ የሁላችንም ናት ማለትም 11 በላይ ክልሎች ከ80በላይ ብሄሮች ተከባብረው የሚኖሩባት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ናት እናም ሥልጣንን መከታ በማድረግ በብሄርተኝነት አንድን ክልል ከፍ በመድረግ በሌሎች ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩ ተገቢ አይደለም። ምክኒያቱም ዘላቂነት የለውም የፌደራል ዋና ከተማ ለይ የአንድ ክልል ሰንደቅ አላማ እንዴት ከፍ ይላል ምንም በማያውቅ ህዝብ ላይ ትልቅ ጠባሳ ጥሎ ለማለፍ ካልሆነ ሌላ ምንም አይነት ጥቅም የለውም ሥለዚህ ሰባዊነት ይሰማቹህ ህውሀት 30 አመት ካደረሰብን ግፍ እና መከራ በላይ እያሠቃያቹህን ነው ።እና ፋኖ ማለት ደግሞ ያለምንም ደመወዝ ትጥቅ እና ሥንቅ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ተሥልፎ ለኢትይጵያ የህይወት መሥዋትነት የሚከፍል የወጣቶች አደረጃጀት እንጅ እንደ ሸኔ ህፃናትን የሚደፍር የሚያርድ የሚያዋርድ የባንዳ ሥብሥብ አይደለም ፋኖን ማጠልሸቱ ይብቃ ሲጨንቅሽ ፋኖ ድረሥ ሲመችሽ ፋኖ ይፍረሥ የምትይው አይደለም ።
 
Besufikad Desta Mulatu

ፈጣሪ እንዳንች አይነት ከሃዲወችን ከኢትዮጰያ ያጥፋልን ።
 
Manasbo Getu

የምትሠሩት ስራ ፈጽሞ ትክክል የማይሆን ሽንገላ የመረጣችሁን ህዝብማ ክዳችሁ የማያውቀውን ቀንበር ካልጫንባችሁ እያላችሁ ነው ይህንን ሆን ብላችሁ አዲስ አበባ ውስጥ ሌላ ብዙ ቋን�ቋ ተናጋሪ ህዝብ እያለ ግን ከኦሮሞኛ ውጭ ሌላ የለለ በማስመሠል ወይም ለሌላው ትርጉም ሳትሠጡ ለምን ኦሮሞ ብቻ ይህ የእውነትም ተረኝነትንም በግልጽ የሚያመላክት ጉዳይ ነው
 
Gabriel Shebale

የኦሮሚያ ሕዝብ መዝሙር toxic and divisive ነው።
በዛ ነው።በዛ ላይ ጠባብነታችሁን እንጂ ኦሮሞን እና ኢትዮጵያነትን አይወክልም።
በኃይል የተጫነ በኃይል ይወድቃል!
 
Ye Mareyame Meazi

ከአዲስ አበባ ላይ እጅሽን አንሼ ት/ቤት የፓለቲካ ማራመጃ አይደለም የኦሮሚያ ባንዲራና መዝሙር ሸገርን አይወክልም በጣም ጠባቦች ናቹህ በበታችነት ስሜት ባንዲራም ሆነ ቋንቋ ልትጭኑብን መሞከር መውደቂያቺህ ነው ብልፅግና የደነዘዙ ዘረኞች ስብስብ ነው
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.