Breaking News
Home / Amharic / ስልታዊ ማፈግፈግ ወይስ ስልታዊ አማራን ማድቀቅ?

ስልታዊ ማፈግፈግ ወይስ ስልታዊ አማራን ማድቀቅ?

👉“መከላከያው በሴራ ነው የተሸነፈ አትበሉ” የሚሉ ሰዎች እንግዲያው አቅም አንሶት አልያም በበቂ መዋጋት የማይችል ኃይል ሆኖ ነው የተሸነፈ እንበል ? መርጠው ቢነግሩን ጥሩ ነው። መቼም ከራያ ጫፍ ጀምሮ ላሊበላን፣ ወልዲያን፣ ደሴን፣ ኮምቦልቻንና አሁን ደግሞ ከፊል ሰሜን ሸዋን እያስረከበ የመጣን ኃይል እያሸነፈ ነው ወደኋላ የሚያፈገፍገው ሊባል አይችልም።
በኢትዮጵያ የሚሊትሪ ታሪክ ውስጥ ወታደራዊ አሻጥር የሚሠራው በወታደራዊ አመራሩ ያውም ከአመራሩም በተወሰነው ክፍል እንጂ በምስኪኑና ህይወቱን ለሀገሩ ሊገብር በቆረጠው ተዋጊው ኃይል አይደለም።
በተወሰኑ አመራሮች የሚፈፀሙ አሻጥሮች እንዳይነገሩ በመፈለግ ሆን ብለው ነገሮችን በመሸፋፈንና “እንዲህ ካልህ ወያኔ ነህ” ከሚሉት በላይ ወያኔ የለም! ለነገሩ የአባቶቻቸውም የእነሱም ታሪክ የሚያስረዳው የወያኔ ገረዶች የነበሩና የሆኑ መሆናቸውን ነው!
ወታደራዊ አሻጥር ሲባል ከጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጀምሮ በተዋረድ ባሉ አመራሮች የሚፈፀም በወታደራዊ ሕግ የበላይ ትእዛዝን እንዳለ የመቀበል ዲሲፕሊንን abuse በማድረግ በተራ ተዋጊው ወታደር ጀርባ የሚሠራ ቁማር ነው። ይህ አይነገር የሚሉትን በደንብ ጠርጥሩ!
እነ-አክተር አይሞትም የሽርሽር ዘማቾች አሰላሳይነትን የሚፀየፉና አሳዳሪ ጌቶቻቸውን ያስከፋብናል ብለው ስላሰቡ እውነት እንዳይነገር አፋቸውን በከንቱ ይከፍታሉ የኦህዴዱ የጦር አበጋዝ ኮሎኔል ሁሴን አስር ሺህ ወታደር ከነከባድ መሳሪያቸው ለወያኔ አሳልፎ መሸጡ ሴራ ካልተባለ ምን ሊባል ነበር?! ያልተጋለጡትን ደግሞ ቤት ይቁጠራቸው። ከዚያ ውጪ “ወታደራዊ አሻጥር በመከላከያ ውስጥ አለ” ሲባል የምስኪን ወታደሮችን ፎቶ ይዘህ ለመከራከሪያ የምትወጣ ጥርብ መሐይምም ሁን የራስህን የወያኔ የገረድነት ታሪክ ለሌላው በመለጠፍ ማሸማቀቅ የምትከጅል ኮተታም ይህ ከንቱ ጥረትህ በመሬት ላይ ያለውን እውነት አይቀይረውም!
አዎ በአዛዦች የተፈፀመና እየተፈፀመ ያለ ሸፍጥ ሀገሪቱንም ፣ ወታደሩንም ፣ ህዝብንም መራር ዋጋ አስከፍሏል ፤ እያስከፈለም ነው።
በነገራችን ላይ በአማራ ህዝብ መካከል በኗሪነት ስም ስለሚኖረው የወያኔ ሴል ስንናገር “ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት ነው” ሲሉ የነበሩ ጉዶች ናቸው ዛሬ እውነቱ ሊደበቅ ከማይችልበት ደረጃ ሲደርስ ተገልብጠው የዚሁ ጉዳይ ዋነኛ አቀንቃኝ መስለው የተከሰቱት።
የዐማራ ህዝብ ሆይ አካባቢህንና ርስትህን ለመጠበቅ ፣ ሚስትና ልጆችህን ከመደፈር ለመታደግ ራስህ ቀድመህ መነሣት አለብህ እንደህዝብ ስትዘምት በሌላው ላይ መንጠላጠል ስታቆም ለሴራም ለወራሪም ዕድል ትነፍጋቸዋለህ!።
ድል ለዐማራ ህዝብ!
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.