Breaking News
Home / Amharic / ስለ ኢትዮጵያ አስገራሚ እውነታዎች::

ስለ ኢትዮጵያ አስገራሚ እውነታዎች::

#ስለ_ኢትዮጵያ_አስገራሚ_እውነታዎች (ዳንኤል ክብረት)
(ዳንኤል ክብረት)
ኢትዮጵያ ማለት የቃሉ ትርጉም እነዚያ አዕምሯቸውን የታወሩ ጠላቶቿ እንደሚያወሩት የተቃጠለ ፊት ማለት ሳይሆን ኢትዮጵያ ማለት “ለአምላክ የሚሰጥ የወርቅ ሥጦታ” ማለት ነው ትርጉሙ።
ሲተነተንም ኢት=አምላክ፣ ፈጣሪ፣ እግዚአብሔር ማለት ሲሆን ዮጵ= ቢጫ ወርቅ፣ ውድ ወርቅ፣ ልዩ ወርቅ ማለት ነው።

ኢትዮጵያ ማለት እኔና እናንተ በምናውቃት ልክ ብቻ ያለች ሀገር አይደለችም። ኢትዮጵያ ከምድር ሀገራት ሁሉ እጅግ ምስጢራዊና ረቂቅ ሀገር ናት። ይሄን ስላችሁ ደግሞ በግምት ወይም በስሜት ተገፍቼ አይደለም። በብዙ ማስረጃዎች ነው እንጅ። ይሄን ጽሁፍ ስታነብቡ ውስጣችሁ የማይቀበልላችሁ፣ የኢትዮጵያ ነገር የማይዋጥላችሁ፣ ተራ አሉቧልታ ወይም አፈ ታሪክ የሚመስላችሁ፣ ኅሊናችሁ ኢትዮጵያዊያን በጠባብነት በዘረኝነት ወይም በገንዘብና በክህደት የታወረ ጥቂት ትኖራላችሁ። አልፈርድባችሁም። ምክንያቱም የኢትዮጵያ ማንነት አልገባችሁምና ነው።

(((ብሉይ ኪዳን)))
1ኛ) ሊቀ ነብያት ሙሴን የአመራርነት ጥበብ ያስተማረው #ኢትዮጵያዊው_ዮቶር ነው። ስለዚህ ለእስራኤል ከፈርዖን ነጻ መውጣት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና አለበት ማለት ነው። ቴዲ አፍሮ በጥቁር ሰው አልበሙ ላይ የዮቶርን ኢትዮጵያዊነት ለመጥቀስ ሞክሯል። የዮቶር እርስት ውብ ሀገር ኢትዮጵያ ነች።

2ኛ) አሁንም የሊቀ ነብያት ሙሴ ሚስት #ሲጳራ ኢትዮጵያዊት ነች።ሐበሻዊት ሲጳራ የኢትዮጵያዊው የዮቶር ልጅ ነች። ሙሴ ይቺን ሴት በማግባቱ ወንድሙ አሮንና እህቱ ማርያም ያጉረመርሙበት ነበር።

3ኛ)የመጀመሪያው ካህን መልከጼዴቅ ኢትዮጵያዊ ነው ይህ ካህን በክርስትና አስተምህሮ የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ተደርጎ ይቆጠራል።

4ኛ) በሀገረ እስራኤል የራሷ ቦታ ያላት (ዴር ሡልጣን) ብቸኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ ነች። ይሄንን ቦታ ምዕራባዊያንና አንዳንድ የምስራቅ ሀገራት ለመውሰድ ቢሞክሩም እንዳልተሳካላቸው ታሪክ ይዘክራል።

5ኛ) ከባቢሎን ዘመን አስቀድሞ የነበረው ብቸኛው የሰው ልጅ ቋንቋ (ግዕዝ) የሚገኘው ኢትዮጵያ/ቤተ ክርስትያን/ ውስጥ ነው። ይሄን ቋንቋ እኛ የቋንቋው ባለቤቶች ብናቃልለውም ቅሉ ዓለም ግን እጅግ የሚያከብረው ትልቅና ቀዳሚ ልሣን ነው። ይሄንን ደግሞ ራሳቸው ምዕራባዊያን ይመሰክራሉ። በዚህ ቋንቋ ብዙ እልፍ ድርሳናትና ምስጢራት ተከትበዋል።

6ኛ) ጻዲቁ አባታችን የሄኖክ የልጅ ልጅ #ኖኅ የተቀበረው ኢትዮጵያ/ጎንደር/ ውስጥ ነው። የሰው ልጅ ከሰማይ ከተጣሉት መላዕክት (ኔፍሊሞች) በተማረው ምድራዊ ጥበብ ምክንያት ልቦናው ከፈጣሪው ራቀ። ለምሳሌ ኮኮብ ቆጠራ፣ በአንገት የሚታሰሩ በጆሮ የሚንጠለጠሉ በእጅና እግር ጣቶች የሚታሰሩ ከንፈርንና ገላን የሚቀቡ ሁሉም ምድራዊ ጌጣጌቶች የመጡት ከወደቁት መላዕክት ወይም ከኔፍሊሞች ነው። እነዚህ መላዕክት የሰውን ልጅ ከፈጣሪው እንዲርቅ ዝሙትን፣ መዳራትን፣ ያለ አግባብ መብላትና መጠጣትን አስተማሩት። በዚህም ምክንያት የሰው ልጅ ኅልቆ መሳፍርት ሀጢያትን በመስራቱ እግዚአብሔር ምድርን በንፍር ውኃ መላት። ሁሉም አለቁ። ኖኅና ቤተሰቦቹ ብቻ ቀሩ። ይህ ሰው መቃብሩ የሚገኘው ኢትዮጵያ ውስጥ ነው።

7ኛ) ኖኅ ራሱንና ልጆቹን ከንፍር ውኃ ያዳነባት መርከቡን ያሳረፋት #ኢትዮጵያ_ጣና አካባቢ ከሚገኘው አራራት ተራራ ላይ ነው::
8ኛ) የመጀመሪያው ሰው አዳም የተፈጠረው ከአራት ባህሪያተ ስጋ ነው። ከእነዚህም መካከል ደግሞ የተፈጠረበት እሳት ውኃና ነፋስ የተገኘው ከኢትዮጵያ ነው። ከዚህም በመነሳት ዳንዶች #አዳምና_ሄዋን_ኢትዮጵያዊያን ናቸው ይላሉ። እውነት ነው።
ኢትዮጵያ የሰው ዘር መገኛ ነች።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.