Breaking News
Home / Amharic / ስለ ቤተክርስቲያን ገንዘብ !

ስለ ቤተክርስቲያን ገንዘብ !

“ከባንክ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በርካታ አሉባልታ ይነሳል፤ቤተክርስቲያን የምትሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው።ከዓባይ ባንክ ጋር ሥራ የጀመርነው በህጋዊ አሰራር በጨረታ በተደረገ ሂደት አሸናፊ ሆኖ በመገኘቱ ነው።ከዓባይ ባንክ ይልቅ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በእሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ ያለን ገንዘብ ይበልጣል።ዓባይ ባንክ ያለን ገንዘብ ተንቀሳቃሽና ለሰራተኛው የብድር አገልግሎት በማቅረብ ለሰራተኛው የመኪና፣የቤትና የልዩልዩ ግዤዎችን ለመፈጸም የሚያስችል አገልግሎት የሚሰጥበት የባንክ አገልግሎት ነው።
በሌላ በኩል ቤተክርስቲያናችን በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ የማይንቀሳቀስ ገንዘብ አስቀምጣለች። በጣም መጠነኛ ገንዘብ በአዋሽ፣ በሕብረትና በአቢሲኒያ ባንኮች አስቀምጣለች፤ ከዚህ ውጪ በሌላ ባንክ ወይም በአማራ ባንክ የተቀመጠ ምንም አይነት የማዕከላዊ የቤተክርስቲያን አስተዳደር ገንዘብ የለም። የተቀመጠ ገንዘብ አለ ከተባለም በማስረጃ ማቅረብ ይቻላል አሁንም ቢሆን በርካታ ሥራዎችን የምንሰራው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ነው።።”
 
ብፁዕ አቡነ አብርሃም
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና
የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
+ + +
ለተጨማሪ መረጃ
+ + +
1. ድረገጽ:- https://eotceth.org
2. ፌስ ቡክ ገጽ:- የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ/Department of Public Relation,EOTC
3. ስልክ፦ +251 111 55 0098
+251111262652 +251111262818
4.eotcprdepartment@gmail.com
5. ፖስታ፦ 1283 አዲስ አበባ
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.