ሰበር መረጃ ጥንቃቄ:-
የዘመነ ወቅታዊ ጉዳይ÷
የመርከቦች ሽያጭና በኢንጂነር ስመኘው ግድያ ላይ የሚታመነው ዕውነት/ * ባለፈው ማክሰኞ ምሽት የአማራ ሕዝብ አንዱ የትግል አርማ የሆነውን አርበኛ ዘመነ ካሴ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የሞከረው የዓብይ አህመድ እና የብአዴን ጥምር አፋኝ ቡድን አሁንም ጥቃት ማድረሱን እንደማያቆም በርካታ ምልክቶች እየታዩ መሆናቸውን ከባህር ዳር የሚወጡ መረጃዎች አረጋግጠዋል:: በአሁኑ ወቅት በዘመኔ መኖሪያ ቤት አካባቢ የመከላከያ ኦራል በብዛት እየታየ ሲሆን ታርጋ ያልተለጠፉባቸው እና ወደ ውስጥ መስታወታቸው የማያሳይ ዘመናዊ የደህንነት መኪናዎችም በአካባቢው በተደጋጋሚ እያንጃበቡ መሆናቸው ታውቋል:: ለሁሉም በክህደት እና በሴራ ሰይጣንን የሚያስንቁት ዓብይ አህመድና ዞምቢዎቹ ብአዴኖች ስልጣናቸውን እና ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ የሚልዮን ሰላማዊ ዜጋ ሕይወት ቢቀጠፍ ግድ የማይሰጣቸው በመሆኑ ዘመነም ሆነ መላው ሕዝብ ምን እየተከናወነ እንደሆነ በንቃት እንዲከታተሉ ከሁሉም በላይ ግን ክልሉን እና ሕዝባችንን ለ እልቂትና ለውድመት የዳረገውን ብአዴን የሚባል አራሙቻ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል በጋራ መረባረብ ይኖርባቸዋል እንላለን::
*በሌላ ዜና ባህሩም ሰማዩም የብሱም የኔ ነው ያለው የኦሮሙማው ኦህዲድ ቡድን በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ቁልፍ የሆኑትን መንግስታዊ መዋቅሮችና እንደ አየር መንገድ ያሉ ስመ ጥር ተቋማት በአጭር ጊዜ በመዳፉ ስር አስገብቶ በተለይም አማራውን መርጦ ከስራ እያፈናቀለ የራሱን ሰዎች መሰግሰግን እንዲሁም እጅግ አስደንጋጭ የዘረፋ የዕዝ ሰንሰለት ፈጥሮ የሃገሪትን አንጡራ ሃብት በሙሉ እንደ ግሪሳ ወሮ መዝረፍን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል:: የባህር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክ መስሪያ ቤትን በቦርድ ሊቀመንበርነት የሚመራው ኦቦ ሮባ ጋሪ ዶክተር÷ትራንስፖርት ባለስልጣንን ኦቦ አብዲሳ ያደታ÷የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንትና የቦርድ ሰብሳቢ ሆኖ የተሾመው የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ጄነራል ይልማ መርዳሳ እንዲሁም የትራንስፖርት ሚኒስትሩ የኦህዴዱ ዋና አመራር ዶክተር ዓለሙ ስሜ በዋናነት ተቆጣጥረው ያለ ማንም ከልካይ እና ተቆጪነት ኢትዮጵያን እንደ ግል ንብረታቸው እየመዘበሩ ያሻቸውን ግፍ እየፈጸሙ ይገኛሉ:: የወያኔው የማፍያ ድርጅት ሜቴክ አንድ አሮጌ መርከብ አየር በአየር ሸጧል ብሎ ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ሲሳለቅ የነበረው ዓብይ አህመድ በሮባ ጋሪ አማካኝነት ባህርዳር እና ሀዋሳ የተሰኙ ሁለት የኢትዮጵያ ግዙፍ መርከቦችን በድብቅ ቸብችቦ መረጃውን እንደ ደሃ ቀብር ሽፍንፍን ቢያደርገውም የማታ ማታ ላይ “ግመል ሰርቆ አጎንብሶ” እንዲሉ ትሬድ ዊንድስ የተሰኘው ዓለማቀፍ የባህር ትራንስፖርት የመረጃ ምንጭ እና ልዩ ልዩ የመገናኛ ብዙሃን የሌባውን መንግስት ነውር አጋልጠው አፋችንን በእጃችን በአግራሞት ለማስጫን በቅተዋል:: ታዲያ መሸጥ የለመደ እናቱን ያስማማል እንዲሉ አንዳንድ ውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደገለጹት የኢትዮጵያ አየር መንገድም ዘራፊው መንግስት በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ካዝናው በመራቆቱ ተመሳሳይ የሽያጭ እጣ እንደሚገጥመው ጠቁመው ሰሞኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ፕሬዝዳንትና የቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት አንጋፋው ባለሙያ ግርማ ዋቄ በዓብይ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው የተነሱት ምክንያት እንዲሁም በቅርቡ ከስልጣናቸው ይወገዳሉ ተብሎ የሚወራው የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ዋናው ምክንያት ከፈረንሳይ ኩባንያ እና ከአሜሪካ ድርጅቶች ጋር ንግግር በመጀመሩ ሳቢያ ዓብይ አህመድ በሚፈጽመው በዚሁ ታላቅ ሃገራዊ ክህደት በሽያጩ ሂደት ላይ እንቅፋት ይፈጥራሉ ተብሎ በመታሰቡ ነው ሲሉ አስተያየታቸውን ይሰጣሉ:: እና በቀጣይ በምስጢር እስካሁን በኢትዮጵያ ላይ ምን ዓይነት የክህደት ወንጀል እንደፈጸመ ምን እንደተሸጠና ለመሸጥ እንደወጠነ ገና ብዙ ጉድ መስማታችን አይቀርምና ለሁሉም ሆደ ሰፊ ሆነን መጠበቁ አይከፋም ነው የምንለው::
*በነገራችን ላይ ዓብይ አህመድ ጁን 10,2018 ዓ.ም ወደ ግብጽ ተጉዞ ከፕሬዝዳንት ጄነራል አልሲሲ ጋር በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከተወያየ በኋላ “ወላሂ እመኑኝ! ግድቡ ግብጽ እስካሁን ከአባይ ውሃ በምታገኘው የውሃ ድርሻ ላይ አንዳችም ተጽዕኖ አይኖረውም” ሲል ቃል መግባቱን በወቅቱ በርካታ ዓለማቀፍ የዜና አውታሮች ዘግበውት ነበር:: ከአልሲሲ ጋር ምስጢራዊ ስምምነት አድርጎና ቃል ገብቶ ወደ ሃገር ቤት ከመጣ በኋም የህዳሴው ግድብ ዋና ኢንጂነር የሆነውን ስመኘው በቀለን “የግብጾችን የውሃ ድርሻ እንዳይጎዳ ግድቡ ከሚኖሩት 16 የኤሌክትሪክ አመንጪ ተርባይኖች 4ቱን ቀንስ” ብሎ መመሪያ ይሰጠዋል:: ስመኘው ግን ይህ የግድቡን ግንባታ ፕላን በሙሉ የሚቀይር በመሆኑ ሊሆን አይችልም እናድርግ ብንል እንኳ ለዳግም የማሻሻያ ግንባታ እጅግ ከፍተኛ ተጨማሪ ወጪ ይጠይቀናል ለሕዝቡም በግልጽ ይፋ ማድረግ አለብን” ሲል አሻፈረኝ ይላል:: በዚህ ምላሽ ዓብይ ደስተኛ አልነበረም:: ጭቅጭቁ እየበዛ ሲመጣ በወሩ ጁላይ 26,2018 ዓ.ም ማለዳ ጧት 10 ሰዓት ላይ ኢንጂነር ስመኘው ለሃገር ውስጥና ለውጭ የዜና አውታር ጋዜጠኞች መግለጫ በቢሮው ለመስጠት ጥሪ አስተላለፈ:: እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ጋዜጠኞች በቢሮው ተኮልኩለው ሲጠብቁት እሱ ከቤቱ ተነስቶ መኪናውን እያሽከረከረ ተጉዞ ላንድክሩዘር መኪናው ውስጥ ሕዝብ በብዛት በሚዘዋወርበት የመስቀል አደባባ እራሱን በጥይት ገድሎ ተገኘ የሚል አስደንጋጭ መርዶ ተሰማ:: እነ ዓብይ ግድያውን የፈጸሙበት የግድቡ ፕላን እንዲቀየር ኃይል የማመንጨት አቅሙን 4 ተርባይኖችን በመቀነስ በከፍተኛ መጠን ማውረድ የሚል ማሳሰቢያቸውን ለሕዝብ አጋልጦ በሃገር ከሃዲነት ያስወነጅለናል ከሚል ስጋት በመነጨ እንደሆነ ይታመናል:: እጅግ የሚገርመው ደግሞ ልብ ብላችሁ ከሆነ ዓብይ ከሃገር ሲወጣ አንድ ሴራ ጠንስሶ በመሆኑ የሆነ አደጋና ክስተት እንደሚፈጠር ብዙ ማስረጃዎች አሉ:: ስመኘውን ባስገደለበት ጁላይ 26 እለትም ዓብይ አህመድ ከጁላይ 26-30, 2018 ዓ.ም በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች ጋር ለመነጋገር ያቀናበት ዕለት መሆኑ ሲታወቅ የስመኘውንም የግፍ አሟሟት እንደዘበት “ስመኘው የሚባል ሰው አርፏል” ሲል እዛው መድረክ ላይ አርድቷል:: ይህ እጁ በሚልዮኖች ንጹሃን ደም የጨቀየ ሳድስት ባንዳና ለፍርድ የሚቀርብበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም::
እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል::