Breaking News
Home / Amharic / ኦሮምያ ዉስጥ 1 አማራ ከተገደለ ስልጣኔን እለቃለሁ – አብይ አህመድ (ዶ/ር)

ኦሮምያ ዉስጥ 1 አማራ ከተገደለ ስልጣኔን እለቃለሁ – አብይ አህመድ (ዶ/ር)

 
ምስራቅ ወለጋ ዉስጥ ከ200 በላይ ሰዎች ተገደሉ፣ 40 ሺሕ ያሕል ተፈናቀሉ::
በኦሮሚያ መስተዳድር ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ ዉስጥ «የኦነግ-ሸኔ ሸማቂዎች» ናቸዉ የተባሉ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ከ200 በላይ ሰዎች መግደላቸዉን የአካባቢዉ ነዋሪዎች አስታወቁ።ከ40 ሺሕ በላይ ነዋሪም ተፈናቅሏል።በስልክ ያነጋገርናቸዉ የዓይን ምስክሮች እንዳሉት ታጣቂዎቹ ካለፈዉ ሳምንት ሮብ ጀምሮ በወረዳዉ የሚገኙ 6 ቀበሌዎችን ወርረዉ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ነዋሪዎችን ልጅ ካዋቂ፣ ሴት ከወንድ ሳይለዩ በጥይትና በገጀራ ገድለዋቸዋል።ከጥቃቱ ያመለጡ አንድ ዓይን ምስክር እንዳሉት አማርኛ ተናጋሪ የሆኑ የአካባቢዉ ነዋሪዎች ከየቤታቸዉ እንዳይወጡ፣ከወጡም ዉጪ እንዳያመሹ የሚያስጠነቅቅ ወረቀት ባለፈዉ ነሐሴ 11 በየሥፍራዉ ተለጥፎ ነበር።«ነዋሪዉ ላንድ ሳምንት ያክል በየቤቱ ተሸሽጎ ከሰነበተ በኋላ የአካባቢዉ ባለስልጣናት ማስጠንቀቂያዉን እየገነጠሉ ስለጣሉት ነዋሪዎችም ሠላም ነዉ ብለዉ ከየቤታቸዉ መዉጣት ጀመሩ፣ወዲያዉ ግን ታጣቂዎች አካባቢዉን ወርረዉ ከየቤቱ የወጣዉን ገደሉት፤ ከብቱን ዘረፉት፤ ሰዉ እቤት ዉስጥ ተቀምጦ የቤቱን ጣራ እየነቀሉ ወሰዱት።»ይላሉ።የዓይን ምስክሩ እንዳሉት በአካባቢዉ ልዩ ኃይል ከገባ በሕዋላ ከትናንት በስቲያ ብቻ ነዋሪዎች 72 ሰዉ ቀብረዋል።ሐሮ ከተባለ ቀበሌ የተፈናቀሉ ሌላ የዓይን ምስክር እንዳሉት ደግሞ ታጣቂዎቹ በተለያዩ ቀበሌዎች የገደሏቸዉ ሰዎች ቁጥር ከ200 ይበልጣል።ከሟቾቹ ቢያንስ አራቱ የልዩ ኃይል ባልደረቦች ናቸዉ።የዓይን ምስክሩ አክለዉ እንዳሉት ከ40 ሺሕ የሚበልጥ ሕዝብ ተፈናቅሏል።ስለጥቃቱና ስለደረሰዉ ጉዳት ለማረጋገጥ ስልክ ከደወልናላቸዉ የምሥራቅ ወለጋ ዞንና የኦሮሚያ ባለስልጣናት መካከል አንዱ ማንነታችንን ከጠየቁ በኋላ «ሥራ ላይ ነኝ» በማለት ስልኩን ዘግተዋል።ሌሎቹ በተደጋጋሚ ብንደዉልም ስልካቸዉን አያነሱም።የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ ባሸባሪነት የፈረጀዉ ሸኔ የተባለዉ ታጣቂ ቡድን ወለጋ ዉስጥ በተደጋጋሚ ጥቃቶችን ያደርሳል።(ፎቶ ነቀምት፣ከክምችት)

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.