Breaking News
Home / Amharic / ምርጫ ቦርድ የትጥቅ ሰራዊት ላለው ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ሰርተፍኬት መስጠቱ ፍፁም ስህተት ነው።

ምርጫ ቦርድ የትጥቅ ሰራዊት ላለው ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ሰርተፍኬት መስጠቱ ፍፁም ስህተት ነው።

” ባንድ እግራቸው ጫካ ባንድ እግራቸው ደሞ ሰላማዊ ትግል ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች አሉ”
:
ከአምንስቲ ዘገባ በፊት ኢትዮጲያ ውስጥ ሰላም ለምን ጠፋ የሚለው መታወቅ አለበት…?
ይሄን ስናይ አንዳንድ ፓርቲዎች ባንድ እግራቸው በሰላም እንታገላለን እያሉ ባንድ እግራቸው ደሞ ጫካ ያለውን ሰርዊት
የሚመሩት እራሳቸው ናቸው::
ይሄ ከባድ ስህተት ነው ምክንያቱም እነሱ ናቸው የኦሮምያን ሰላም እና የሀገሪቱን ሰላም እየበጠበጡ ያሉት። በሌላ በኩል ABO(ኦነግ) ከኤርትራ ሲመጣ 5000የታጠቀ ሰራዊት እንዳለው ነበር ያስመዘገበው ነገር ግን ትጥቅ አስፈትቶ ያስገባው 1300ውን ብቻ ነው።
ምርጫ ቦርድ የትጥቅ ሰራዊት ላለው ፓርቲ የምርጫ ቦርድ ሰርተፍኬት መስጠቱ ፍፁም ስህተት ነው።
መንግስት የታጠቀው ሃይል ከጫካ ወጥቶ ህዝብ ላይ ጦርነት እስከሚከፍት ድረስ መታገሱ ስህተት ነው።
ህዝብ ላይ ግድያ ዘረፋ እና የመሳሰሉት ብዙ ወንጀል ተስርቷል።ከዛ በኋላ መንግስት ስላም ለማስጠበቅ ጥረት በሚያደርግ ግዜ በህዝብ እና በመንግስት ላይ ከባድ ጉዳት ነው የደረሰው።
የታጠቀው አካል በህዝብ ላይ ያደረሰው ወንጀል እና በደል በአምንስቲ ዘገባ ላይ መካተት ነበረበት ስለዚህ የአምንስቲ ኢንተርናሽናል ዘገባ ሚዛናዊነት የጎደለው እና ለአንድ ወገን ያደላ ነው::

(ጀነራል ከማል ገልቹ ለ OBN ከተናገሩት)”
ትርጉም Hana Regassa Waktolla … ለማድመጥ
https://www.facebook.com/1440206995991463/posts/3464885703523572/

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.