Breaking News
Home / Amharic / መልእክት ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ !

መልእክት ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ !

ክቡር ፕሬዘዳንት የአሰብን ጉዳይ ሊያስቡበት ይገባል

የኢትዮጵያ መንግስት በመቶ ሺዎች የወደቁበት የባድሜ መሬት ለኤርትራ መንግስት መልሰሷል ! የኤርትራ ህዝብ ንብረቶችን አንድም ሳይነካ ከነሙሉ ንብረቱ መልሷል እርስዎም በምላሹ በታሪክም በማስረጃም የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የሆነውን የአሰብን ወደብ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚመልሱ እርግጠኞች ነን ::
የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የሆነውን የአሰብን ወደብ ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ግመል አጠጡበት ብሎ በችሮታ ለኤርትራ ህዝብ እንደሰጠ የአደባባይ ሚስጥር ነው ::
የኤርትራ ህዝብ ከአሰብ ወደብ የሚጠቀመው አንድም ጥቅም የለም ! ነገር ግን በወደብ አለመኖር ምክንያት ብዙ ወጭ ለምታወጣው ኢትዮጵያ ጠቀሜታው እጅግ ዘርፈ ብዙ ነው
ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግስት ስንት የኢትዮጵያ ህዝብ ያለቀበትን የባድሜን መሬት እንደመለሰ ሁሉ የአሰብን ወደብ ለባለቤቷ ለኢትዮጵያ በመመለስ የሁለቱን ሀገራት ወዳጅነት ከፍ ወዳለ ምእራፍ እንደሚያሸጋግሩት እምነታችን የፀና ነው ::
የአሰብ ወደብ የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረትና መሬትና ይዞታ ነው ! ይህን መሬት ለባለቤቷ ለኢትዮጵያ ይመለሳል
የኢትዮጵያ ህዝብ የገነባው የህዳሴ ግድብ የኤሌትሪክ ሀይል ማመንጫም የኤርትራ መንግስት ያለአንዳች ክፍያ ከግድቡ ተጠቃሚ ይሆናል።
በጎ ሀሳብ ለበጎ ተግባር!
 
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.