Breaking News
Home / Amharic / ጥያቄ ለብአዴን! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ??

ጥያቄ ለብአዴን! አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ??

ብአዴኖች እመኑኝ ብትሞቱ እንኳን አንተዋችሁም!!!
አሸናፊ ነው ብላችሁ የሸለማችሁት ሠራዊት አዛዡ ማን ነበር ??
እመኑኝ የኛ ትውልድ በህዝብ ፊት አንበርክኮ ይጠይቃችኋል!
ብትሞቱ መቃብራችሁ ላይ ለትውልድ መማሪያ የክህደት ታሪካችሁን እንጽፈዋለን። 

በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ዛሬ በአማራ ክልል ከፌዴራል በመጡና በክልሉ ባለስልጣኖች በጦርነቱ የተሳተፉ እና
የጎላ አስተዋፅ ያበረከቱ የመከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ሀይል ሚሊሻና ፋኖ መሸለም እና ማበረታታት እንዲሁም እዉቅና መስጠት
በሚለዉ ፕሮግራም ስትሸለሙ ስትወደሱ እዉቅና ሲሰጣቹ የምትደሰቱ ፋኖወች የአማራ ልዩሀይል እንዲሁም ሚሊሻወች በእዉነት በጣም ታሳዝኑኛላችሁ::

መቼ  እንደሚገባን መቸ እንደምንረዳ አይገባኝም ! አንድነገር ልንገራቹ ይህ የሽልማት ፕሮግራም ሲዘጋጅ እዉነት የአማራ
ልዩሀይል የአማራ ፋኖ ሚሊሻ ለማጠናከር ለማወደስ እዉቅና ለመስጠት ክልሉን ለማጠናከር መስሎ የሚታያችሁ ካላችሁ በጣም ተሳስታቹሀል::

 ነገሩ እንዲህ ነዉ! የተሸለመና ያልተሸለመ በማለት የአማራ ፋኖን ልዩ ሀይሉን ሚሊሻዉን በማቃቃር አንድነት እንዳይኖር
የመከፋፈል የመበታተን በጥቅም በመደለል የአማራን ህዝብ እና የሰጥታ አካላትን ለመበታትን ፋኖን ለማዳከም የተሰራ ስራ መሆኑን ማወቅ
አለብን ብየ አስባለሁ ::

 በተለይ ለአማራ ፋኖ ከአብይ ወይም ከደመቀ እጅ ሽልማት ተበርክቶልህ የምትደሰት በአማራ ህዝብ ስም እየማልክ እተገዘትክ
አላማህን የምትስት ከሆነ አንተ ለአማራ ህዝብ ሳይሆን የቆምከዉ ለሆድህ ነዉ::

 እዉነተኛ የአማራ ልጅ ፋኖ ልዩ ሀይል ሚሊሻ የሆነ ሽልማትህ ወርቅ ብር መሬት ሳይሆን ሽልማትህ የአማራ ህዝብ ሞት መፈናቀል
መገደል ሲቆም አማራ እንደማንኛዉም ኢትዮጲያዊ በፓለቲካዉ በማህበራዊ በፓለቲካዊ ጉዳዮች እረፍት እና ሰላም ሲያገኝ ማየት
ስትችል ብቻ ነዉ::

ይህ ሽልማት በተለየ መልኩ ለአማራ የሚቆረቆሩ ፋኖዎችንና ልዩ ሀይሎችን ለማሰር ለመበተን ለመግደል ለማሰር
ከጨዋታ ዉጭ ለማድረግ ልክ የኋንስ ቦያለዉን ከፌደራል መንግስቱ ገሸሽ እንዳደረጉት ሁሉ ለመድረግ የታሰበ መሆኑን ልትዘነጉ አይገባም::

ፋኖ ነኝ

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.