በእውቀቱ አቻ የሌለው ስሙን መላክ ያወጣው አቻምየለህ ታምሩ ፡መፈናፈኛ የሚያሳጣ እውነት ለበቀለ ገርባ አፍሶለታል።
እውነትም አቻምየለህ!!!
የአቻምየለህ ድንቅ ፅሁፍ የሚከተለው ነው።
—-
ራሱን የረሳው በቀለ ገርባ
በቀለ ገርባ የሚባለው ሰውዬ ከኦሮሞ በላይ ኦሮሞ ለመሆን የሚያደርገው መውተርተር ሁሌም ያስደንቀኛል። በቀለ በነገድ ሲመዘን ኦሮሞነቱ ጥያቄ ውስጥ ስለሚገባ በኦሮሞ ብሔርተኞች ዘንድ ዋጋ የሚያወጣ የሚመስለው ያለ የሌለ የክፋት አቅሙን ተጠቅሞ በአማራ ላይ ሲዘምት ይመስለዋል። አንድ ሰው የነገድ ፖለቲካን የአለም መጨረሻና የሕይዎት ጥሪውን ካደረገ ፖለቲካውን በራሱ ነገድ ዙሪያ ያደርጋል እንጂ ባሪያ ያደረጉትንና ማንነታቸውን የጫኑበትን የጌቶቹን ማንነት አንጠልጥሎ እንዴት ብሎ የነገድ ፖለቲካ አራማጅ ይሆናል?
በቀለ ገርባ ከሰሞኑ ኩሽ ሜዲያ ኔትዎርክ ከሚባል ጸረ አማራ የጥላቻ ሜዲያ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ራሱ ረስቶ ከገዳ ሥርዓት ባርነት ነጻ ያወጡትን የጥንት የኢትዮጵያ አርበኞች በቃላት ሊገለጽ ከሚገባው ጥላቻ በላይ አውግዞ የነሱ ልጆች ናቸው ባላቸው የጥንቱ ቢዛሞ የዛሬው የወለጋ እና ሸዋ አማሮችን የኮድ ስም በመስጠት ወለጋ የሚንቀሳቀሰው የናዚ ኦነግ ጨፍጫፊና ዘር አጥፊ አራዊት እንዲያጠፋቸው ጥሪ አቅርቧል።
በቀለ ገርባ ልክ እንደ ሐድያው ጁኔይዲ ሳዶ ሁሉ ኦሮሞ ሳይሆን ኦሮሞ በወረራ ይዞ ባርያ ያደረገው የቢዛሞ ጰለታ ነው። ኦሮሞ ኢትዮጵያን ሲወርር አስገብሮ ጭሰኛና ባሪያ ያደረጋቸውን ነባር ነገዶች ከመሬታቸው ከነቀለ በኋላ «ገርባ» ይላቸዋል። ገርባዎች የኦሮሞ ባሮችና ጭሰኞች ናቸው። ገርባ የሚለው የኦሮምኛ ቃል የአማርኛ ፍቺው ባርያ ወይንም አገልጋይ ማለት ነው። የበቀለ አባት አቶ ገርባ አባት ስም ዳኮ ኦሮሞ ባሪያ አድርጎ ባስገበራቸው የቢዛሞ ምድር ቅድመ ኦሮሞ የኢትዮጵያ የጥንት ጎሳ በሆነው በዳካ ጎሳ ስም ነው የሚጠሩት።
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለዶክትሬት ማሟያቸው እ.ኤ.አ. በ1984 ዓ.ም. ባዘጋጁት «History of the Sayyoo Oromoo of Southwestern Wallaga, Ethiopia, from about 1730 to 1886» በሚለው ጥናታቸው ውስጥ ኦሮሞ ምዕራብ ኢትዮጵያን ከመውረሩ በፊት ከመውረሩ በፊት ደቡብ ምዕራብ ቢዛሞ [የዛሬው ወለጋ] ውስጥ ይኖሩ ስለነበሩ ጥንታዊ ነገዶች በዘረዘሩበት የመጽሐፋቸው ገጽ 73 ላይ ዳኮ ኦሮሞ የዛሬውን ወለጋን ከመውረሩ በፊት ወለጋ ውስጥ ይኖር የነበረና በኦሮሞ ተሰልቅጦ ማንነቱን ቀይሮ የጎሳ ስሙ ብቻ የቀረ እንደሆነ አቅርበዋል።
ባጭሩ የበቀለ ገርባ አያት አቶ ዳኮ የሚጠሩት ኦሮሞ ቢዛሞን ከመውረሩ በፊት በቢዛሞ ምድር ይኖሩ ከነበሩ የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጎሳዎች መካከል አንዱ የሆነው የዳኮ ጎሳ አባል ናቸው። የዳኮ ጎሳ ቋንቋውንና ባሕልን ተነጥቆ ኦሮምኛ እንዲናገር የተገደደው በኦሮሞ ወረራ ገርባ ተደርጎ ነው። በመሆኑም በቀለ ገርባ ኦሮሞ ሳይሆን ኦሮሞ ባሪያ ካደረጋቸው የዳካ ቤተሰቦች የተወለደና ኦሮሞ ማንነቱን ያጠፋበት ገርባ ነው።
እንግዲህ ከኦሮሞዎች በላይ ኦሮሞ በመሆን በኦሮሞ ስም በአማራ ሕዝብ ላይ የጅምላ ፍጅትና እልቂት የሚጠራው በቀለ ገርባ በተጫነበትና ባሪያ በተደረገበት የወራሪዎቹ ማንነት ተጀቡኖ ነው። ‹ስልብ ባሪያ በጌታው ብልት ይፎክራል› ይሏል ይህ ነው።
ኦሮሞ ያስገበራቸውን ነባር ነገዶች በበቀለ አባት ስም ገርባ እያለ እንደሚጠራቸውና ጭሰኛ አድርጓቸው እንደኖረ ማወቅ የሚሻ በኦሮሞ ታሪክ ጥናት ጥርሱን የነቀለው አሌክሳንድሮ ትሪውልዚ “Boorana and Gabaro among the Macha Oromo in Western Ethiopia” በሚል ያሳተመውን ድንቅ ምርምር ያንብብ።
ከፍ ሲል የተጠቀሱት ጰለታዎችና ገርባዎች የሆኑት የበቀለ ገርባ ዘሮች ከኦሮሞ ባርነት የተላቀቁት በቀለ ገርባ የሚያወግዛቸው የኢትዮጵያ አርበኞችና መሪያቸው ዳግማዊ ዐጤ ምኒልክ ለደጃዝማች ጆቴ ቱሉ፣ ለወንድማቸው ለደጃዝማች ቲባ ቱሉና ለደጃዝማች ቁምሳ ሞሮዳ በ1902 ዓ.ም. ኦሮሞ ጰለታና ገርባ ያደረጋቸውን ባሪያ እያሉ እንዳይሸጡ ባወጡት ደንብ ነው። በነገራችን ላይ ደጃዝማች ቲባ ቱሉ የደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ታናሽ ወንድም ሲሆኑ የኢማሌድኅ አባል የነበረው የወዝሊግ ሊቀ መንበር የነበረው የዶክተር ሰናይ ልኪ አያት ናቸው። የዶክተር ሰናይ ልኪ አባት ልኪ ቲባ ቲሉ ይባላሉ። ዶክተር ሲናይ ልኪን አሜሪካን ልከው ያስተማሩት በንጉሡ ዘመን የወለጋ ጠቅላይ ግዛት እንደራሴና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት የነበሩት ዘመዱ ዶክተር ደጃዝማች ካሣ ወልደ ማርያም ደግሞ የደጃዝማች ቲባ ቱሉ ታላቅ ወንድም የደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ሴት ልጅ የአስካለ ጆቴ ልጅ ናቸው።
ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ በዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ዘመን ጊምቢን ዋና ከተማቸው አድርገው የዛሬውን ምዕራብ ወለጋን ሲገዙ ታናሽ ወንድማቸው ደጃዝማች ቲባ ቲሉ ደግሞ አሶሳን ማዕከላቸው አድርገው ከአሶሳ እስከ ኦምዱርማን ድረስ የተዘረጋውን ትሪያንግል ይገዙ ነበር። የደጃዝማች ካሳ ወልደ ማርያም እናት ወይዘሮ አስካለ ጆቴ የልጅ እያሱ ባለቤት የነበሩ ሲሆን አባታቸው ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ልጃቸውን አስካለን ለልጅ ኢያሱ ሲድሩ ስምንት መቶ ጋሻ ቡና ጥሎሽ ለልጅ እያሱ ሰጥተው ነበር።
ልጅ ኢያሱ ፍቼ ራስ ካሳ ቤተ መንግሥት በታሰሩበት ወቅት ይጎበኟቸው ከነበሩ ሁለት የቀድሞ ሴት ወዳጆቻቸው መካከል ወይዘሮ አስካለ ጆቴ አንዷ ነበሩ። ፋንታሁን እንግዳ የተባሉ የታሪክ ተመራማሪ በ1997 ዓ.ም. «በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አስተዳደር ጎልተው የወጡ የፖለቲካ ችግሮችና ትግሎች በቅርብ ባለሟሎች ሲገመገሙ» በሚል ባሳተሙት መጽሐፋቸው ወይዘሮ አስካለ ጆቴ ዶክተር ደጃዝማች ካሳ ወልደ ማርያምን ያረገዙት እስር ቤት ከነበሩት ከልጅ ኢያሱ እንደሆነና መልካቸውም ልጅ ኢያሱን እንደሚመስል እንዲሁም ወይዘሮ አስካለ ጆቴ ዶክተር ደጃዝማች ካሳ እንደ አባት የሚጠሩባቸውን ታላቁን አርበኛ ደጃዝማች ወልደ ማርያምን ያገቡት ዶክተር ደጃዝማች ካሳ ከተወለዱ በኋላ ነው የሚል የቤተ ዘመድ መረጃ እንዳለ ጽፈዋል።
ወደ ዋናው ጉዳይ ስለመለስ በቀለ ገርባ ቤተሰቦቹን ወርሮና መሬታቸውን ቀምቶ ጭሰኛ ካደረጋቸው ኦሮሞ ነጻ እንዲወጡ ያደረጉትንና አያቶችና ቅድመ አያቶቹን ባርያ ሆነው ከመሸጥ ያዳኗቸው በቀለ ገርባ “ነፍጠኛ” እያለ የሚያወግዛቸው የኢትዮጵያ አገልጋዮችና አመድ አፋሽ የተደረጉት ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ናቸው። ከወራሪና ባሪያ ፈንጋይ አባገዳዎች የበቀለ ገርባን ቤተሰቦች ነጻ ያወጡት አመድ አፋሹ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ እነ ጆቴ፣ ቲባና ሞሮዳ ባሪያ፣ ገርባና ጰለታ ያደረጓቸውን ነጻ ማውጣት ብቻ ሳይሆን እነዚህ ደጃዝማቾች ባሪያ አድርገው የሸጧቸውን የበቀለ ገርባን ዘሮች እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ እየተላላኩ የሚከፈለውን በመክፈል ከባርነት ነጻ እንዲወጡና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ያደረጉ አባት ናቸው!
ሳንድራ ሼል የሚባሉ ተመራማሪ «From slavery to freedom : the Oromo slave children of Lovedale, prosopography and profiles» በሚል ርዕስ እ.ኤ.አ. በ2013 ዓ.ም. ባሳተሙት መጽሐፍ የኦሮሞ ባላባቶች ባሪያ አድርገው የሸጧቸውን የምዕራብ ኢትዮጵያ ነገዶች አባላት ዝርዝርና ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ደቡብ አፍሪካ ድረስ በመላላክ ገንዘብ ጭምር እየከፈሉ ነጻ እንዲወጡና ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ስላደረጓቸው ገርባዎች፣ ጰለታዎችና ባሮች ይናገራል። ጥናቱ የኦሮሞ ባላባቶች ከወለጋ ባሪያ አድርገው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሸጧቸውን ሰዎችና ዳግማዊ ምኒልክ ገንዘብ እየከፈሉ ያስለቀቋቸውን ባሮች ትውልዶች ጭምር አካቷል። በኦሮሞ ባላባቶች ከተሸጠበት ከደቡብ አፍሪካ ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ገንዘብ ከፍለው ነጻ ያወጡት ያንዱ ሰው ትውልዶች በደርግ ዘመን ከኢትዮጵያ ወደ ካናዳ ተሰደው አሁንም ድረስ ካናዳ ውስጥ እንደሚኖሩ ጥናቱ ያሳያል።
በዐፄ ምኒልክ በባርነት ከመሸጥ የተረፉት ውለታ ቢሶቹ እነ በቀለ ግን ይህን እውነት ማወቅም መናገርም አይፈልጉም። ገርባ መሆኑን የሚያውቁት ትክክለኞቹ ኦሮሞዎች ይጠራጠሩኛል ብሎ ስለሚያስብ ታማኝ ኦሮሞ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚያደርገው መፍጨርጨር በአማራ ላይ እንዲነሳ የማይጠራው ጨፍጫፊ ኃይል የለም።
በኃይል በተጫነበት ባሕል፣ ማንነትና ቋንቋ እንድናውቀው የሚውተረተረው በቀለ ገርባ ስለቋንቋ መጨፍለቅ አብዝቶ ሲያወራ ይሰማል። ይህ የበቀለ ገርባ መቆርቆር ግን ግን የአማራ ጥላቻ እንጂ ከልብ የመነጨና እውነት አይደለም። በቀለ ገርባ የቋንቋ መጨፍለቅ የሚያሳስበው ቢሆን ኖሮ ከሁሉ በፊት እሱ ራሱን የተጫነበተን ቋንቋና ባሕል አሽቀንጥሮ ጥሎ ወደ ጥንተ ማንነቱ በመመለስ ራሱን ይሆን ነበር። ሆኖም ግን በቀለ ኦሮሞ ወርሮ ገርባ ያደረጋቸውን የሱ ዘሮች ቋንቋ ጨፍልቆ እንዳጠፋውና ማንነታቸውን እንደቀየረው መናገር አይፈልግም።
በቀለ ኦሮሞን ነጻ ሊያወጣ እታገላለኹ የሚለው ከተጫነበት የሰው ማንነት ራሱን ነጻ ሳያወጣ ነው። ነጻነትን የማያውቁ ነጻ አውጪዎች የተባለው ለበቀለ ገርባና መሰል ራሳቸውን በኃይል ከተጫነባቸው የወራሪ ነጻ ሳይወጡ ባሪያ ያደረጓቸውን ነጻ ለማውጣት የሚውተረተሩትን ጰለታዎች፣ ዳለቻዎችና ገርባዎች ነው። በእውነቱ የበቀለን ዘሮች ኦሮሞ በባርነት ሰንሰለት ካሰረበት ጨለማ ወደ ብርሀን እንዲወጡ ያደረጉትንና የነሱ ዘሮች ናቸው በሚባቸው ላይ ፍጅትና ሽብር የሚያውጅ ቢኖር ራሱን የረሳና ነጻ በመውጣቱ የሚቆጭ ኢሰብአዊ ፍጡርና ፈጽሞ ራሱ የረሳ ብቻ ነው።