Breaking News
Home / Amharic / ሕውሃት የሚባል ወንድም ኖሮን አያውቅም!

ሕውሃት የሚባል ወንድም ኖሮን አያውቅም!

ሕውሃት የሚባል ወንድም ኖሮን አያውቅም!
በወንድማማቾች መካከል እልቂት አታባብሱ እያላችሁ መልክት ለምትልኩልኝ ወገኖቼ ግልጽ ለማድረግ የምፈልገው ነገር እንደሚከተለው ነው። ብዙዎቻችሁ ይሄን የምትሉት ከቅንነት በመነጨ ለአገራችን ሰላም ከመመኘት እንደሆነ አልጥራጠርም።
ይሁንና የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃት የሚባል ወንድም ወይንም እህት ኖሮት አያውቅም። እኛ የምናውቀው ህወሃት ከተፈጠረ የዛሬ አርባ አራት አመታት ጀምሮ አገርና ህዝብ ሲያተራምስ፣ ሲያሸብር፣ እልቂት ሲደግስ፣ ክህደት ሲፈጽም፣ ሲዘርፍ፣ አገርና ህዝብን ሲያንኳስስና ሲያራክስ፣ ህዝብን በህዝብ ላይ ሲያነሳሳ፣ ሲከፋፍል፣ በየእስር ቤቱ በንጹሃብ ዜጎች ላይ ሰቆቃ ሲፈጽም፣ በግፍ ሲገድልና ሲያስገድል፣ በሃሰት ሲወንጀልና ሲያስወነጅል፣ ብልት ሲያኮላሽ፣ ጥፍር በጉጠት ሲነቅል፣ ሲገርፍና ሲያስገርፍ፣ አገር ሲያስገነጥል፣ ኢትዮጵያን የምታህል ትልቅ አገር የባህር በር አልባ ሲያደርግ፣ ግዛት ሲያስፋፋ፣ ዘር ሲያጠፋ፣ በስልጣን ሲባልግ፣ የአማራውን ህዝብ ነጥሎ ነፍጠኛ እያለ ሲያስፈጅ፣ ወላድን ሲያመክን፣ እራሱን አግዝፎ የኢትዮጵያን ህዝብ ሲያንኳስስ፣ ዜጎችን ለርሃብ፣ ለቸነፈርና ለስደት ሲዳርግ፣ እራሱን አበልጽጎ ህዝብ ሲያደኸይ…በአጠቃላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ሲፈጽምብን ቆይቶ አሁን ደግሞ ለትግራይ ከባድ የደምና የህይወት ወስዋትነት የከፈለን ሰራዊት አስተኝቶ በውድቅት ሌሊት ከበስተጀርባ ጨፈጨፈ። አሁን ግን የግፉ ጽዋ ከመጠን በላይ ሞልቶ እየፈሰሰ ስለሆነ ከዚህ ፋሺስታዊ አሸባሪ ቡድን የተጀመረውን እራስን የመከላከልና አገርን የመታደግ ዘምቻ እንዲሳካ ብቻ በአንድነት ጥረት ማድረግ ያስፈልጋል።
አዎ! የኢትዮጵያ ህዝብ ህወሃት የሚባል እኩይ ጠላት እንጂ ህወሃት የሚባል ወንድም ወይንም እህት ኖሮት አያውቅም። ወደፊትም አይኖረውም። መፍትሄው የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ጠላት የሆነውን ህወሃት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መደምሰስና ማጥፋት ብቻ ነው። በየትኛውም የታሪክ አጋጣሚ በድል ካልተጠናቀቀ አደገኛ የሆነ ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል።
የአሁኑም የታሪክ አጋጣሚ ፍጻሜው ድርድና እርቅ ሳይሆን ምንም እንኳን የህይወትና የአካል መስዋትነት ቢያስከፍልም የጠላታችን የህወሃት መደምሰስና መሪዎቹም ተይዘው ልክ እንደ ናዚ ፓርቲ መሪዎች ልዩ ፍርድ ቤት ተቋቁሞ ለፍርድ እንዲቀርቡ ማድረግ ብቻ ነው።
ከእኩይ ጠላት ጋር ወንድምነትም ይሁን ዝምድና ፈጽሞ ሊኖር አይችልም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!
Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.