Breaking News
Home / Amharic / ለኮሚሽኑ ከተሾሙት ዉስጥ አንድም አማራ አልተወከለም ። ዝርዝሩን ተመልከቱ !

ለኮሚሽኑ ከተሾሙት ዉስጥ አንድም አማራ አልተወከለም ። ዝርዝሩን ተመልከቱ !

Achamyeleh Tamiru

በነውረኛነቱ ፋሽስት ወያኔን የሚያስንቀው የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ

የኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ ዛሬ ይፋ ባደረገው “የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነሮች” ዝርዝር ሰብሳቢውንና ምክትል ሰብሳቢዋን ኦሮሞ ሲያደርግ ለይስሙላ እንኳን አንድም የአማራ ነገድ ተወላጅ አልተካተተም። በኮሚሽነርነት የተሾሙት የአስራ አንዱ ሰዎች “ብሔር፣ ብሔረሰብና ሕዝብነት” የሚከተለውን ይመስላል፤

1. ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ – ሰብሳቢ – [ኦሮሞ]
2. ወይዘሮ ሂሩት ገብረስላሴ – ምክትል ሰብሳቢ -[ኦሮሞ]
3. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌቱ – [ኦሮሞ +]
4. አምባሳደር ዶክተር አይሮሪት መሃመድ -[አፋር]
5. ወይዘሮ ብሌን ገብረመድህን – [ትግሬ]
6. ዶክተር ዮናስ አዳዬ – [ደቡብ]
7. አቶ ዘገየ አስፋው – [ኦሮሞ]
8. አቶ መላኩ ወልደማሪያም – [ደቡብ]
9. አምባሳደር መሃሙድ ድሪር – [ሶማሌ]
10. አቶ ሙሉጌታ አጎ – [ደቡብ]
11. ዶክተር አምባዬ ኦጋቶ – [ሲዳማ]

የአፓርታይዱ አገዛዝ ሌላው ነውር የይስሙላው ፓርላማ ከዘረዘራቸው 42 እጩዎች ውስጥ የስም ዝርዝራቸው የሌለውን ብሌን ገብረመድህንን፣ ሙሉጌታ አጎንና አምባዬ ኦጋቶን ኮሚሽነሮች አድርጎ መሾሙ ነው። የይስሙላው ፓርላማም የስም ዝርዝራቸው ከ42ቱ እጪዎች ውስጥ ያልነበሩትን እነዚህን ሰዎች ተቀብሎ ሾመታቸውን አጽድቋል።

    • አንድም አማራ እንኳን ለይስሙላ ያልተካተተበት አገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኦሮሙማው የአፓርታይድ አገዛዝ የተቋቋመው አማራን ለመታገል በተፈጠረው ብአዴን በሚባለው ዘግናኝ ፍጥረት ፍቃድና ይሁንታ ጭምር ነው።

One comment

  1. ጉድ በል ጎንደር የአማርኛ አስተማሪ ከወለጋ መጣ!

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.