Breaking News
Home / Amharic / ለአዲስ አበባ የመንግስት ሰራተኛ የተዘጋጀው የፈተና ወረቀት ይሄውላችሁ። ተፈታኝ ዘመድ ካላችሁ አሰራጩት።

ለአዲስ አበባ የመንግስት ሰራተኛ የተዘጋጀው የፈተና ወረቀት ይሄውላችሁ። ተፈታኝ ዘመድ ካላችሁ አሰራጩት።

by Andargachew Tsige

በበኩሌ ከዋናው የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ላይ አይናችንን ልንነቅል አይገባም በሚል ስለአብይ አህመድ ነውረኛ አገዛዝ በመረጃ የተደገፉ በርካታ ጉድፎች እየደረሱኝም ብዙ ጊዜ ወደፌስ ቡክ አላመጣቸውም። ይህ ፈተና አንዱ የኦሮሞ ብልጽግና በተረኛነት ከሚፈጽማቸው ብልግናዎች አንዱ በመሆኑ ጥቂት ለማለት ወደድኩ።
አላማው ችሎታ ያላቸው ግለሰቦች ብቻ የህዝብ አገልጋዮች እንዲሆኑ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ፈተና አይደለም። በአለም ላይም አንድ መንግስት ሰራተኞቹን በሙሉ ፈተና ሰጥቶ ወድቃችኋልና ከስራ አባርሬያችኋለሁ ያለበት ታሪክ ተሰምቶ አይታወቅም። የፈተናው አላማ የአዲስ አበባን የህዝብ ስብጥር ኦሮሞ ያልሆኑ ዝርያዎችን በማፈናቀል፣ቤታቸውን በማፍረስ፣ በማስመረር ከተማዋን ለቀው እንዲሄዱ ለማድረግ እየተሰራ ካለው የአብይ አህመድና የተባባሪዎቹ መሰሪ እቅድ አካል ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ማጥፋት አልፈልግም።
አንድ ሃቅ ብቻ በማቅረብ ይህ ድርጊት የተመሰረተበትን የድንቁርና እና የሞራል ኦና ላመላክት።
በ1983 አም ያየሁት በደርግ ጊዜ የተወሰደ የህዝብ ቆጠራ የከተማው ኗሪ በአንደኛ ደረጃ 57% አማራ፣ ቀጥሎ 17% ጉራጌ፣ በሶስተኛ ደረጃ 14% ኦሮሞ እንደሆነና ሌሎች ብሄረሰቦች በሙሉ ተደምረው የተቀረውን % እንደሚሸፍኑ በዝርዝ ያሳያል። የህዝብ ቆጠራው የተደረገው በሁሉም ከሶስት መቶ በላይ በነበሩ ቀበሌዎች ሲሆን በየትኛው ቀበሌ አማራው ከ50 ከመቶ በታች ወርዶ አይታየም። አንዳንድ እንደ እንጦጦ፣ ፈረንሳይ ለጋሲዎን ስድስት ኪሎ ውስጥ በነበሩ ቀበሌዎች የአማራው ህዝብ እስከ 95 በመቶ ይደርስ እንደነበር መረጃው ያሳያል።
ከዚህ መረጃ ብቻ በመነሳት፣ በአንዳንድ ቀበሌዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰዎ 90% አማሮች ቢሆኑ በከተማው የመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ከ50% በላይ አማሮች ሆነው ቢገኙ ፈጽሞ የሚያስገርም ሊሆን አይችልም ነበር። ያስገርም የነበረው በከተማ ኗሪነቱ 14% በመቶ የሆነው ኦሮሞ ከ50% በላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ተቀጣሪ ሆኖ ቢገኝ ነበር። የኦሮሞ ብልጽግና የያዘው የተንሸዋረረ ሎጂክ ግን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ፍትሃዊ ነው የሚል ነው። እየሰሩም ያለው ይህን ለማድረግ ነው። 76ሽህ ፖሊሶች ከኦሮሞ ልዩ ሃይል ወደ አዲስ አበባ ፖሊስና ታከለ ኡማ ወዳደራጀው የከተማው ልዩ ሃይል እንዲዞሩ ተደርጓል። የአዲስ አበባ የትራፊክ ፖሊሶች በዚሁ ሎጂክ አማካይነት ብቻ ሳይሆን ከዛም በተሻገረ እብሪት ከሞላ ጎደል ሁሉም ኦሮሞች ሆነዋል። ሰሞኑን መንጃ ፈቃዳሽ የተጻፈው በአማርኛ ስለሆነ በኦሮምኛ አስተርጉመሸ ይዘሽ መዞር ነበረብሽ ተብላ ከአንድ የዘመኑ ትራፊክ ፖሊስ ጋር የተጋጨት ሴት ጉዳይ እስከ ከፍተኞች የፖሊስ ኮሚሽነሮች ደረጃ ደርሶ ሰሞኑን መካሰሻ ሆኖ ነበር። ተረኝነት በዚህ ደረጃ ክንፉን ጥሎ አብዷል።
ይህንን የድንቁርና እና የእብሪት ፍሬኑ የተበጠሰ የአብይ አህመድ የጥፋት ባቡር ማስቆም የሚቻለው ፋኖ የሚያደርገውን ትግል ከምር በመቀላቀልና በመደገፍ። አዲስ አበቤ ለራስ ስትል ተነስ። ራስክን በባለጌዎች ጫማ ከመረገጥ አድን።

ፈተናዉን ለማንበብ ሊንኩን ተጫኑ !

https://www.facebook.com/photo?fbid=744789957674113&set=pcb.744809734338802

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.