Breaking News
Home / Amharic / ለአማራ እና አማራ ወዳጆች የድጋፍ ጥሪ !

ለአማራ እና አማራ ወዳጆች የድጋፍ ጥሪ !

#ጋሻ_የአማራ_ድጋፍ_አሰባሳቢ_ግብረኋይል #ለአማራ_እና_አማራ ወዳጆች_የድጋፍ_ጥሪ የአማራ ተወላጅና የአማራ ወዳጅ ለሆናችሁ በሙሉ የቀረበ ጥሪ፦ አደጋ የተደቀነበትን የአማራ ህልውና ኑና በጋራ እንመክት!! ፠ በኖቬምበር 10ቀን 2021ዓ ም የሰሜን ሸዋ አማራ በወራሪው የትህነግና ኦነግ ሰራዊት ጦርነት የተከፈተባቸው ቀን ነው። በጎጃም ከቡሬ አንስቶ እስከ ጎሃጺዮን ባለው ቀጠና ድረሰ እጅግ መጠነ ሰፊ የሆነ የኦነግ ሰራዊት ሰፍሮ ለወረራ አሰፍስፎ በመጠባበቅ ላይ ነው። ፨ ሐምሌ 13ቀን 2021 በወሎ ራያና በጎንደር ማይጸብሪ ግንባር የተጀመረው የወረራ ጦርነት ዛሬ በ5ኛ ወሩ ላይ ወያኔ ከጎንደርና ወሎ ተሻግራ ሰሜን ሸዋ ደርሳ ከኦነግ ጋር ጥምረት በመፍጠር የተናበበ መጠነ ሰፊ ወረራ በጎጃምና በሸዋ ላይ በመክፈት ላይ ናቸው። ብዙ ወገኖቻችንም ተፈናቅለው ለረሃብና ለበሽታ ከመጋለጣቸውም በላይ በመጠሊያ እጦት በየሜዳው ወድቀው ይገኛሉ። ጀግናው ጄ/ል አሳምነው ጽጌ «አማራ ከ500ዓመት በፊት እንደገጠመው የህልውና አደጋ-በዚህ ትውልድ በጠላት የመከበብ አደጋ ተደቅኖበታል» ያለው እውን እየሆነ ነው። ስለሆነም የአማራው ልጆች ወራሪ ጠላታቸውን በሁሉም አቅጣጫ እየተፋለሙት ይገኛሉ። ጋሻ! የአማራ የህልውና አደጋ ዓለም አቀፍ ድጋፍ አሰባሳቢ ግብረኃይል ይህንን የህዝባችንን የህልውና አደጋ በሁሉም ዘርፍ ለመደገፍ ቅዳሜ ኖቬምበር 13ቀን 2021 የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቴሌቶን አዘጋጅቷል። ፠ በዳያስፖራ ያለው መላው አማራና የአማራ ወዳጆች መሳተፍ ወገናዊ ግዴታ በሆነበት በዚህ የአማራው ህልውና ድጋፍ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እንድትሳተፉ ግብረኃይሉ በአክብሮት ይጋብዛል። የዕለቱ ተጋባዥ እንግዶች የአማራን እና መላው ሃገራችን ያሉበትን ወቅታዊ ሁኔታ በዝርዝር የሚያቀርቡበትና በቀጣይ የአማራና የሃገራችን እጣፈንታ ላይ አቅጣጫ የሚጠቁሙበት ዝግጅትም ስለሆነ የአማራና የአገራችን ህልውና ይመለከተኛል ያገባኛል የሚል ሁሉ ይህ ፕሮግራም እንዳያመልጠው ይመከራል። #ቅዳሜ_ኖቬምበር_13_ቀን_2021 ፨ በእንግሊዝ 5PM ፨ በ Eastern Europe 6PM ፨ በአሜሪካ DC 1PMፕሮግራሙ ይጀመራል። ፠ የቴሌቶኑ መግቢያ ዙም ሊንክ በዋዜማው ጀምሮ የሚሰራጭ ሲሆን ዝግጅቱ በተለያዩ ሚዲያዎችም በቀጥታ ስርጭት ይተላለፋል። አማራ ሆነን ለአማራው ካልቆምን ሌላው ለህልውናቸን እንዲቆምልን መጠበቅ የለብንም! ህልውናችንን የምናረጋግጠው ስንደጋገፍ ብቻ ነው! የተደቀነብንን የዘር ማጥፋት አደጋ ድል የምንመታው በአንድ ላይ ስንሰባሰብ ብቻ ነው!

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.