Breaking News
Home / Amharic / ለአማራ ባንክ ምዝገባ !

ለአማራ ባንክ ምዝገባ !

የባንክ አክሲዮን ምስረታ ሂደት ቅደም ተከተል
ከ170,000 በላይ ባለ አክሲዮኖች የተሳተፉበት አማራ ባንክ አማ የአክሲዮን ሽያጭ ከ9 ቢሊዩን ብር ካፒታል በላይ በመሠብሰብ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።
የሽያጭ ክንውኑ እንዲሳካ የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ ከፍተኛ አስተዋኦ ነው።
ባንኩ ቅርንጫፍ ከፍቶ አገልግሎት እስኪጀምር ድረስ ለሚኖሩት ቀሪ ስራዎች የባለሙያ ቀጥተኛ ተሳትፎ አስገዳጅ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበን ፕሮጀክቱን በሁለት ዕግሩ እንዲቆም በቀጣይ ስራዎች በንቃት መሳተፍ አለብን ።
ለግንዛቤ ይሆን ዘንድ፥ የተከናወኑ እና ቀሪ የባንኩ ምስረታ የስራ ሂደቶች በዳሰሳው የሚከተሉት ናቸው።
1) የባንክ አክሲዮን ለማቋቋም የተስማሙ አስተባባሪዎች ተሰብስበው ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ ሰነድ ማርቀቅ፤
(በ2011 ዓ.ም የተሰራ)
2) የአክሲዮን ድርጅቱን የንግድ ስም ማውጣት፤( በ2011 ዓ.ም የተሠራ)
3) የንግድ ስም በንግድ እና ኢንደስትሪ ማስመዝገብ( የካቲት 09 ቀን 2011 ተከናወነ)
4) የመጀመሪያ የአስተባባሪዎች ጉባኤ ማካሄድ( ግንቦት 2011 ዓ.ም የተከናወነ)
5) አማራ ባንክ አክሲዮን ካፒታል መሠብሰብ ይችል ዘንድ አላማውን አቅርቦ ባንክ ሂሳብ ቁጥር እንዲከፍት በብሄራዊ ባንክ ማስፈቀድ ( ነሃሴ 2011 ተከናወነ)
6) የአክሲዮን ሽያጭ ባንክ አካውንት መክፈትና የሽያጭ በማስታወቂያ በመንገር ባንክ ለመመስረት የሚያስችል ካፒታል መሠብሰብ (ከመስከረም 2012 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ተከናወነ)
ቀጣይ (ቀሪ)ክንውኖች፦
7) አማራ ባንክን ለመመስረት የመሥራቾች ጠቅላላ ጉባኤ በማካሄድ ባንኩን ሊመሩ የሚችሉ ከ9-13 የሚደርሱ እጩ የቦርድ አባላትን በመጠቆም መምረጥ/ማስመረጥ እና በባንኩ የወደፊት ተግባራት ላይ ተወያይቶ በሰነድ በመፈረም ውልና ማስረጃ ማፅደቅ።
8) በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡት የቦርድ አባላት ፥ ዋና ስራስኪያጅ ወዘተ ለብሄራዊ ባንክ በመላክ ሹመታቸው እንዲፀድቅ መከታተል፤
ሹመታቸው የፀደቀው የባንኩ አዲስ አመራር አካላት በጋዜጣ ከወጣ በኋላ ስራቸውን በይፋ ይጀምራሉ፤
ቀጥሎ…
9) ለባንኩን ቅርንጫፍ ህንፃ መምረጥ፥ ሊዝ መዋዋል፥ የውስጥ ዲዛይን ስራ መጨረስ እና ቅርንጫፍ መክፈት፥ የሰው ሃይል ቅጥር፥ የውጭ ኮረስፖንደንት ባንክ ጋር ግንኙነት መፍጠር፥ የመተግበሪያ ሶፍትዌሮችን መትከል፥ ቅፆችን እና የመስሪያ ቁሳቁሶችን ጨረታ የማውጣት ስራ እና በግዥ ማሟላት…፤ሁሉንም ጎን ለጎን ማካሄድ ይቻላል፤
10) አማራ ባንክ በአምሳያው ይፋዊ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር የመነሻ መስፈርት አሟልቶ ከብሄራዊ ባንክ የስራ ፈቃድ(operation license) ተቀብሎ አገልግሎት መጀመር የመጨረሻው ጉዞ ይሆናል።
 

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.