#ስብርብር ያለች አፈትላኪ ዜና
—-
#ለመላዉ የአማራ ህዝብ በዛሬዉ ዕለት ከመከላከያ ዘመቻ መምሪያ የደረሰኝ ትክክለኛ መረጃ….
በሰሜን ሽዋ በንፁህ የአማራ ህዝብ ላይ የተፈፀመዉን ወረራ እና የጀምላ ግድያ በዋናነት የአቀነባበረዉ አማራ ጠል የሆነዉ ኦነጉ ጀኔራል ብርሃኑ ጁላ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ወረራዉ ከመፈፀሙ በፊት መጋቤት 19 /2011ዓ/ም ከ11ኛ ክፍለጦር አዛዥ ሚጀር ጀኔራል ጌታቸዉ ጋር በጦር ኃይሉች ኢታማዡር ሹም ቢሮ ቁጥር 102 ዉስጥ ለ3:00 ስዓት ያክል ሴራ ሸርበዉ ለወራሪዉ ኃይል የጦር መሳሪያ እና የሰራዊት አልባሳት አቅርቦት አገልግሎት የሚሠጡ 6 የመከላከያ ኦራሎች እና 11 የመከላከያ አምቦላንሶች መመደባቸዉን ተገልጿል፡፡
በነዚህ አማራ ጠል ጀኔራሎች የተቀነባበረዉ የወረራ እና የጥፋት ተልኮ በዚህ አላበቃም፡፡ በዛሬዉ ዕለት በመከላከያ ሚኒሰቴር ከጀኔራሎችና ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት ኃላፊወች ጋር በተደረገ ስብሰባ የአማራ ክልል የፀጥታ ኃላፊወችን እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የአብን አመራሮችን እንዴሁም አክቲቪስቶችን ጥፋተኛ እና ተጠያቂ ለማድረግ መወሠኑ ተገልጿል፡፡
ይህን ኃላፊነት የጎደለዉ አሳፋሪ እኩይ ተግባር አጥብቀን ልንቃወመዉ ይገባል።
~~~~||~~~~~~
ቬሮኒካ መላኩ ነኝ
ሚያዝያ 04/2011
ከቤተ አምኃራ
አማራን ከጥቃት ለመከላከል በግንባር ቀደምነት የቆሙትን እነደእነ ጄኔራል አሳምነውን የመሰለ የአማራ የቁርጥ ቀን ዉድ ልጆች ለማጥፋት የሚሸረብ ሴራ እንዳለ አያጠራጥርም። ለእንዚህ የአማራ ቁርጥ ቀን ልጆች የማያውላውል ድጋፍ መስጠትና መከታ ልንሆናቸው የሁላችንም አማራ ነን የምንልና ለአማራ ህዝብ የምንቆረቆር ሁሉ ግዴታ ነው።