Breaking News
Home / Amharic / ህዝቡ ለምን ዝም ይላል?

ህዝቡ ለምን ዝም ይላል?

 

እነ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ብልጽግናዎች ከማሰር ወደ ኋላ አይሉም፡፡ ምክንያቱም ህዝቡን ስለናቁት፡፡

ጀነራል ተፈራን ሲያስሩ ህዝብ ዝም አለ፡፡ ዘመነ ካሴን ሲያስሩ ህዝብ ዝም አለ፡፡ በአስር ሺሆች ፋኖዎችን ሲያስሩ ህዝብ ዝም አለ፡፡ እንደ ጎበዚኦእ ሲሳይ ያሉት ሲያስሩ ህዝብ ዝም አለ፡፡ ለነ ወልቃይት ለሁለት አመት ባጀት ሲከለክሉ ህዝብ ዝም አለ፡፡ ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ መግባት አይቻልም ብለው ዜጎች ሲያግዱ ህዝብ ዝም አለ፡፡ በነ ወለጋ በሺሆች አማራዎች ፣ ባቀኑት አገራቸው ሲጨፈጨፉ፣ በመቶ ሺሆች ሲፈናቀሉ ህዝብ ዝም አለ፡፡ 13 ሺህ ተማሪዎች እንደገና መፈታን አይችሉም ተብሎ የጭካኔ መመሪያ ሲወጣ ህዝብ ዝም አለ፡፡ ለአማራ ክልል ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ በጦርነቱ የወደሙትን መልሶ ለመገንባት ፣ ህዝቡ ለማቋቋም ከተጠየቀው ከ1% ብቻ ሲመደብ፣ በሌላ በኩል ግን ለኦሮሞ ክልል የትናየት ገንዘብ ሲሰጥ ህዝብ ዝም አለ፡፡

ታዲያ ህዝብን ቢንቁ ምን የሚያስገርም ነገር አለ፡፡

ግርማ ካሳ

 

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.