Breaking News
Home / Amharic / ህውሃት ከመሪነት ወደ አጋር ፓርቲነት ከከፋም ወደተቃዋሚነት የወረደችበት ቀን ! ኢህአዴግ ፈረሰ!

ህውሃት ከመሪነት ወደ አጋር ፓርቲነት ከከፋም ወደተቃዋሚነት የወረደችበት ቀን ! ኢህአዴግ ፈረሰ!

ዛሬ ሲካሄድ በዋለው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ የአዲሱን ውህድ ፓርቲ ምስረታ በተመለከተ በ27 ድጋፍ በ6 ተቃውሞ ውህደቱ እንዲካሄድ ውሳኔ አሳልፏል። 6ቱ የተቃወሙት ሁሉም የህወሓት ሰወች እንደሆኑ የደረሰኝ መረጃ ያስረዳል። ከአዴፓ፣ ከኦዴፓ እና ከደኢህዴን የተወከሉ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በሙሉ ውህደቱን ደግፈዋል። ህወሓት ደግሞ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት ጋር መክሬ እስክመለስ ድረስ ጊዜ ይሰጠኝ ብሏል። በነገው ዕለት ውህደቱን በተመለከተ ሊደረጉ ስለሚገባቸው ተግባራትና ፕሮግራሞች ለመወሰን የሥራ አስፈጻሚው ስብሰባ ይቀጥላል። በነገው ሥብሰባ ውህደቱን የተቃወሙት የህወሓት ሰወች እንደማይገኙ ታውቋል።

ይህ ፎቶ ታሪካዊ ፎቶ የመሆን እድል አለው ፡ህውሃት ከመሪነት ወደ አጋር ፓርቲነት ፡ከከፋም ወደተቃዋሚነት የወረደችበት ቀን መታሰቢያ ሊሆን ይችላል፡፡
ውጤቱም ለሃገር የሚጠቅም ከሆነም የጥሩ ጊዜ መጀመሪያ ቀን መታሰቢያ ፎቶ ሊሆን ይችላል።ካልሆነም ልክ ስንኖር ኢትዮጵያዊ ስንሞት ኢትዮጵያ እንደሚለው
ንግግር የወቅት ደስታ ፈጥሮ ያልፋል።ማን ያውቃል፡፡ለማንኛውም ህውሃት ዛሬም ተሸነፈች።

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.