ሰበር ዜና፦
ስድስት የአሜሪካ ኮንግሬስ አባላት የዐማራ ክልሉን ጉዳይ በተመለከተ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ደብዳቤ ጻፉ።
የኮንግረስ አባላቱ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እንዲሁም በተመድ ለአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ በጻፉት ደብዳቤ በዐማራ፣ ኦሮሚያና ትግራይ ክልሎች የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።
የደብዳቤያቸው ዋና ይዘት ከሁለት ዓመታት በፊት በሰሜኑ ጦርነት በውጊያ የተሳተፉት አካላት በሙሉ ፈጽመውታል የተባለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል ለማጣራት በባለሙያዎች የተቋቋመው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች አጣሪ ኮሚሽን በሶስቱም ክልሎች ችግሩ በእጅጉ ተባብሶ በመቀጠሉ በድጋሚ የስልጣን ዘመኑ እንዲራዘም የሚጠይቅ ነው፤ የዓብይ መንግስት የኮምሽኑ እንቅስቃሴ እንዲቋረጥና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት በሃገር ውስጥ በሚቋቋመው የሽግግር ፍትህ የመብት ጥሰቶቹ እንዲጣሩ በማድረግ የህግ እርምት እወስዳለሁ ሲል በተደጋጋሚ ቢማጸንም፤ የተለያዩ አካላት ግን የወንጀሎቹ ስፋትና ጥልቀት በኢትዮጵያ መንግስት ሊፈታ የሚችል ባለመሆኑ የተመድ የባለሙያዎች አጣሪ ኮሚሽን የስራ ጊዜው እንዲራዘም ግፊታቸውን አጠናክረዋል።