የግል ት/ቤቶችን እነ ሽመለስ አብዲሳ መዝጋት ጀመሩ -አፓርታይዱ አፍጦ ወጣ #ግርማካሳ
በአለምገና የሚገኘው ኤቨረስት ትምህርት ቤት በኦህዴድ ባለስልጣናት መዘጋቱን ዘሃበሻ ዘገበ።
“ወላጆች በኦሮሚያ መስተዳድር ፅህፈት ቤት ድምፃቸውን እያሠሙ ነው” ያለው ዘሃበሻ፣ ወላጆች ከህዝብ ተቃውሞ እያቀረቡ እንደሆነ ገልጿል።
4,800 ተማሪዎች ይማሩበት የነበረውን ይህን ትምህርት ቤት የዘጋው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ እንደሆነ የዘገበው ዘሃበሻ፣ “በዚህ ትምህርት በሚጀመርበት ወቅት መዘጋቱ አግባብ አይደለም፣ አሁን ልጆቻችንን የምናስተምርበት ትምህርት ቤት አናገኝም” ብለዋል ወላጆች እየተናገሩኢ እንደሆነም አስፍሯል።
ከአንድ ሳምንት በፊት በጃዋር መሐመድ “መመሪያ” የኦሮሞ ክልል ርእሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ ፣ በአማርኛ በሚያስተምሩ የግል ትምሀርት ቤቶች ላይ እርምጃ እንደሚወስድ መግለጹ ይታወቃል። ይኽው እርምጃው በአለም ገና ጀምሮታል።
በአለም ገና ሆነ በብዙ በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች፣ ኦሮምኛ የማይናገሩ፣ ሕብረ ብሄራዊ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን በብዛት ይኖራሉ። በተለይም በአለም ገና፣ በቢሾፍቱ፣ በአዳማ፣ በሞጆ፣ በሰበታ፣ በቡራዩ …ባሉ ከተሞች ብዛት ያላቸው ኦሮምኛ የማይናገሩ ነው።
አብዛኛው ነዋሪ የአፍ መፍጫ ቋንቋው ኦሮሞኛ ሳይሆን፣ በግድ በኦሮምኛ ካልተማርክ በሚል በአማርኛ የሚያስተምሩ ትምህርት ቤቶችን ለመዝጋት መዘጋጀት የለየለት ዘርኘነት ነው። አፓርታይድ ነው።
ይህ አይነቱን እንቅስቃሴ መታገስ የሚያስፈለግ አይመስለኝም። ለሰላም፣ ለመረጋጋት፣ ለአገር አንድነት ሲባል ዝም ሲባሉ ሰዎቹ መረን እየለቀቁ ነው። ስንታገሳቸው የፈራን እየመሰላቸው ነው።
አራት ኪሎ የተቀመጠው የዶ/ር አብይ አስተዳደርም ከሃይለማሪያም የባሰ ልፍስፍስና ከወሬ ባለፈ መሄድ ያልቻለ ደካም አስተዳደር ነው። ዶ/ር አብይ ስለ ፍቅር፣ ስለመደመር፣ ስለ ሞራል ያወራል፣ ሰዎች እየሰበሰበ። ግን ኢሞራል፣ ዘረኛ.፣ ከፋፋይ፣ ክፋት የተሞላበት ስራ እርሱ በሚመራው ድርጅት ኦህዴድ ሲፈጸም ግን ዝም ብሎ ያያል። ምንም ማድረግ አልቻለም።