ዜና ሰማእታት…!
መስከረም 15/2016 ዓም በኦሮምያ ክልል በአርሲ ሀገረ ስብከት በሆንቆሎ ወረዳ ቤተ ክህነት ቦሌ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ዕጣ የወደቀባቸው ምስኪን የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አገልጋይ ካህናት እና ምዕመናን የኢሬቻ በዓል ከመከበሩ በፊት በኦሮሞ ነፃ አውጪ ሠራዊት ታርደው ማደራቸውን ስምዐ ተዋሕዶ ዘግቧል።
ትናንት ምሽት ማታ ከ4:00 እስከ 5:00 ባለው ጊዜ ውስጥ ውስጥ በተፈጸመው ዘግናኘረ ጭፍጨፋ በመጀመሪያ የደብሩ አለቃ ቤት በመግባት የመምህሩን ሚስት እና ልጃቸውን ከገደሉ በኋላ
በመቀጠል አራጆቹ መ/ር ዳዊት ጌታቸው፣ አበጀ ከበደ፣ ሞገስ ክንፈ፣ መርሻ ፣ ሽመልስ ተስፋዬ፣ እመቤት ስሜ፣ ቡሩክ እና መምሬ ዘሪሁንን አርደው ደማቸውንም ተቀባብለው ጠጥተውና ተቀብተው
መሄዳቸው ተነግሯል።
በዚሁ ጭካኔ የተሞላበት ጥቃት ተጎድተው በሕክምና ላይ ያሉ አገልጋዮች ይርጋ ሞገስ፣ ባዩ ካዳዬ፣ ምሕረት በላይ ይግባው፣ እቡጤ ውብሸት እና አመለ ምሕረት ናቸው። በግድያው የክልሉ መንግሥትም ጭጭ ያለ
ሲሆን ሃገረ ስብከቱም እስከአሁን ያወጣው መግለጫ የለም።
አሰቃቂው ግድያ ትናንት እንዲፈጸም የተደረገው ዜናው ተሰራጭቶ የዛሬውን የደመራ በዓል ኦርቶዶክሳውያን በጨለማ እንዲዋሉ ታስቦ እንደነበርም ታውቋል። ይህን ዜና የለጠፍኩት እንድታለቅሱ አይደለም
እንድትመዘግቡት እንጂ። ይመዝገብ። “
የዘንድሮው የእሬቻ ግብር በአሩሲ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆችን በማረድ ተጀምሯል። በቀጣይ ቀናት ደግም ምን ያሰሙን ይሆን?
አብረን እናየዋለን።