Breaking News
Home / Amharic / የሰሜኑ ጦርነት ፍጻሜ ?

የሰሜኑ ጦርነት ፍጻሜ ?

የሰሜኑ ጦርነት ፍጻሜ እየደረሰ ያለ መሰለኝ #ግርማካሳ

 

ህዝብን ማሸነፍ አይቻልም። ለትግራይ ህዝብ ጦርነት አያስፈልገውም ነበር። የትግራይ ወጣት አንድም ቢሆን መሞት አልነበረበትም።
መከላከያ ከመቀሌ ሲወጣ፣ በመቶ ሺሆች ለረሃብ የተጋለጡና በሚሊዮኖች የተፈናቀሉ ተጋሩ: ምግብ እንዲያገኙና እንዲቋቋሙ፣ መሰረተ ልማቶች እንዲገነቡ የተቋረጡ የመንግስት አገልግሎቶች እንዲከፈቱ ፣ ሕዝቡ ሙሉ ለሙሉ ባይሆንም፣ በተወሰነ መልኩ ወደ ቀድሞ ኑሮው እንዲመለስ ለማድረግ ፣ ትልቅና ብቸኛ ትኩረት ሆኖ ሊሰራበት ይገባ ነበር። አጋጣሚዉን በመጠቀም።
ግን ወያኔዎች ያንን አላደረጉም። ቀዳሚ የሆነውን ነገር ትተው በአማራ ክልልና አፋር ክልል ውጊያ ከፈቱ። ብዙ ጥፋቶች መፈፀም ጀመሩ። ወረራዉን ለመከላከል ከመንቀሳቀስ ውጭ፣ የአማራና የአፋር ማህበረሰብ ምንም ማድረግ አልቻለም።
ከጅምሩ “ሕዝብ ያሸንፋል። ወያኔዎች መሸነፋቸው አይቀርም” ብዬ ስናገር ነበር። “ለማታሸንፉት አትደከሙ” ብዬ ሳስጠነቅቅ ነበር፡ ወረው ክያዙት ወጥተው ወደ ድርድር እንዲመጡም ስጠይቅ ነበር። ግን ሊሰሙ አልቻሉም።
ወያኔዎች፡
1ኛ – ወልቃይት በተከዜና በሱዳን በኩል ከሃያ ጊዜ በላይ ሁመራን ለመያዝ ሙከራ አድርገዋል። ሁሉንም ጊዜ ተሸንፈው፣ ብዙ ወጣት ገብረው ነው የተመለሱት።
2ኛ – በምዕራብ ጎንደር ዞን፣ ከቅማንት ኮሚቴ ከሚባለው ጋር ተቀናጅተው፣ በሱዳን በኩል ካስገቡት ሳምሪ የሚባለውን የአሸባሪ ታጣቂ ቡድንን በማሰማራት በርካታ ጊዜ ዉጊያ ከፈተው ነበር። በመተማ፣ ሽንፋና ቋራ አካባቢ። በዚያም ሽንፈት ነው ያጋጠማቸው።
3ኛ – በደቡብ ጎንደር ብዙ ሰራዊት አሰማርተው፣ ደብረ ታቦር ደጃፍ ደረሰው ነበር። በሕዝብ ትግል ሙሉ ለሙሉ፣ ብዙ ታጣቂዎች ተገድለዉባቸው፣ ተባረው ወጥተዋል።
4ኛ – በሰሜን ጎንደር ዞን፣ ደባርቅና ዳባትወረዳዎች ድረስ ዘለቀው ገብተው ነበር። በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊት አልቆባቸዋል። ከደባርቅ በማለፍ ፣ ዛሪማ ብሎም ጨው በርን የወገን ጦር ተቆጣጥሯል። የቀረቱን በሰሜን ጎንደር በኩል፣ የአደርቃይ ወረዳንና ጠለምትን ነፃ ለማውጣት ዝግጅቱ ተጠናቆ በዚያ ትዕዛዝ እየጠቀ ነው።
5ኛ – በአፋር ክልል ዞን 2 እና ዞን 4 ብዙ ወረዳዎች ወረው ይዘው ነበር። ከአፍር ምድርን ተሸንፈው ተመልሰዋል።
6ኛ – በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ እነ ፍላቂት፣ ደብረ ዘቢጥ ኮኪት የመሳሰሉትን ይዘው ነበር። ሙሉውን መቄት ወረዳ ማለት ይቻላል። አሁን ደብረ ዘቢጥ፣ ኮኪት፣ ፍላቂት፣ አርቢት፣ ገረገራ ሳይቀር ከእጃቸው ወጥቷል። ስትራቴጂክ የሆነችው ጋሸና ከተማ ደጃፍ የወገን ጦር ደርሷል።
7ኛ – በዋገምራ የደሃና ወረዳ(አምደ ወርቅ ከተማን ጨምሮ)፣ ዋግ፣ ሰቆጣ…ሁሉም በነርሱ እጅ ነበር። አሁን ደሃና ወረዳ፣ አምደወርቅ ከተማ በወገን እጅ ገብቷል። ሰቆጣ ልታይዝ ትንሽ ነው የቀራት። በዚያ በርካታ የሕወሃት ጦር እየተሸነፈ ነው።
8ኛ – ከፍተኛ ጦር ወደ ደቡብ ወሎ በማሰማራት፣ ደሴንና ኮምቦልቻን ለመያዝ በጭፍራ በኩል የጅቡቲ አዲስ አበባን የባቡር መስመር ለመዝጋት አልመው ተንቀሳቅሰው ነበር። “ደሴ ገባን፣ ሃይቅ ከተማ ገባን….” ብለው ፣ “ድል” አውጀው ነበር። ግን የወገን ጦር እንደውም በሚያስገርም ሁኔታ ተጠናክሮ በደቡብ ወሎ እጅግ በጣም ከፍተኛ ሽንፈት ሕወሃቶችን እያከናነበ ነው። ብዙ ተጋሩ ታጋዮች እጃቸውን ሰጥተዋል። እግዚአብሄር ትረፉ ሲላቸው።
9ኛ – በሰሜን ወሎ ዋድላ፣ ደላንታ፣ አምባሳል፣ ሃብሮ፣ ጊዳን፣ ቆቦ፣ ለጋ ላፍቶ በስፋት አሁንም ወረው እየተንቀሳቀሱ ነው። ሆኖም ግን በነዚህ ቦታዎች ጦርነቶች አሉ። የአየር ኃይል ጥቃት በስፋት ወያኔዎች ላይ እየተፈጸመ ነው። በዚያም ከህዝቡ የተወጣጡ ፋኖዎች፣ ሚሊሽያዎች ተድራጅተው የሽምቅ ውጊያ እየፈጸሙ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። እነዚህም አካባቢዎች ቢቆጣጠሩም ተረጋግተው መቆየት አልቻሉም።
ሳጠቃልል፣ ቀደም ሲል እንዳልኩት፣ የወያኔ ሙሉ ሽንፈትና እጅ የመስጠት መጀመሪያ ይመስለኛል። አሁን ባለው መረጃ በርካታ የሕወሃት ተዋጊዎች በግዳጅ ስለሆነ የመጡት እጆቻቸውን እየሰጡ ነው። እነ ዶር አብይ አህመድና አራት ኪሎ ያሉ፣ ባለስልጣናት፣ አንድ አይነት ሴራና ሳቦታጅ ካልፈጸሙ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ከቀጠለ፣ በትግራይ ያለው ጦርነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ብዬ አስባለሁ።

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.