Breaking News
Home / Amharic / ዛሬ እስር ቤት ሄጄ የታሰሩትን ሰዎች አናገርኩ ! መልሳቸውን አንብቡልኝ – ስንታየሁ ቸኮል

ዛሬ እስር ቤት ሄጄ የታሰሩትን ሰዎች አናገርኩ ! መልሳቸውን አንብቡልኝ – ስንታየሁ ቸኮል

ዛሬ ግንቦት 8/2015 ዓ,ም ከ4:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አማራነታቸው በሽብር ያስከሰሳቸው የሕሊና እስረኞችን ለመጠየቅ አቀናሁ።
 
ካብዛኛዎቹ ጋር ሚክሲኮ እንደተገናኘን የተለየዋቸው ናቸው። ዛሬ እኔ ጠያቂ ሆኜ በጠባቡ የሽቦ መስኮት ያነጋገርኳቸውን ሰዎች በጥቂቱ..
ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውገቸው ሽብርተኛ ስትባል ምን እንደተሰማዉ ጠየኩት
መልስ ” እኔን በሽብር ለመክሰስ ማስረጃ ካላቸው ወንጀሉ ለአማራ ሕዝብ መቆሜ ነው።
ዶ/ር አሰፋ ኪዳኔ ሽብርተኛ አይደለንም አማራ ነኝ።
መምህርት መስከረም አበራን ምን እንደተሰማት ጠየኳት?
መልስ ” ምንም የተሰማኝ ነገር የለም
በሽብር የጠየቁኝ ፖለቲካቸውን ስለነካሁባቸው ነው እንጅ አሸባሪ ሆኜ አይደለም።
ጋዜጠኛ ገነት አስማማው “የኔ ወንጀል ቢፈለግ አማራነት ጋዜጠኝነት ከመሆን የዘለለ አይደለም።
ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋዉ በተመሳሳይ ጥያቄ አቅርቤለት ነበር።
የቴዲ መልስ..ሁለት አመት በኢትዮ ሰላም ሚዲያ ያቀረብኩት ማየት በቂ ነው። ሰላም እንዴት አሸባሪ እንደምትሆን የጠየቁኝ ሰዎች እንጅ እኔ አላውቅም። ነገም ስለሰላም እንናገራለን ምክንያቱም ሰላም ሽብር ስላልሆነ።
የባልደራስ አባል ቢንያም ታደሰ በተመሳይ አንድ ሳምንት ጨለማ ቤት ቆይቶ አሁን ወደ ግቢዉ እንደተቀላቀለ እና እስካሁን ፍ/ቤት አለመቅረቡን ነገረኝ በ48 ሰዓት ፍርድ ቤት የመቅረብ መብቴን ማለት በራሱ ያስከስሳል።
የሽቦ አጥሩ ላይ ቆሜ በሰመመን ወደኋላ አሰብኩ ከአመታት በፊት ማዕከላዊ እስር ቤት በታሳሪነት የሚበዙት የኦሮሞ ተወላጅ ነበሩ። ያዘመን ተቀልብሶ አሁን የእስር ቤት አጥሮች ግርግሩ በአማራ ተወላጆች ተጨናንቋል። ያሳዝናል። የአማራ ፋኖ መንበረ ጨምሮ ሁሉም በአንድ ድምፅ “እኛ አማራ ነን አሸባሪ ግን አይደለንም በማለት እጃቸውን እያንገሳቀሱ ቻዉ! ቻው! ተለያየን።
አማሮቹ አንገታቸዉ አንድ ነው የተሸበረ ስነ-ልቦና አንዳቸውም ጋር ብትፈልጉ አታገኙም።
በመጨረሻም
በዓይኔ ያየሁት እነ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አወገቸው እና ዶ/አሰፋ ኪዳኔ ሄኖክ ኪዳኔ የቤተሰብ ምግብ ሲመልሱ አይቻለሁ። ለሕዝባችን ስላምታችን ካለንበት አድርስ ባሉኝ መሠረት እኔ በዚህ መልክ አደረስኩ።
ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውግቸው፣ ፕ/ር መዓረጉ ቢያበይን፣ ዶ/ር መሰረት ቀለመ ወርቅ፣ ጋዜጠኛ እና መምህርት መስከረም አበራ፣ ጋዜጠኛ ገነት አስማማው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ አስፋውን ጨምሮ እስከ 40 የሚደርሱ በሁከት እና ብጥብጥ እንዲሁም በሽብር ወንጀል ተጠርጥራችኋል በሚል በአዲስ አበባ ሶስተኛ ጣቢያ የሚገኙ እስረኞች ለ3 ቀናት የሚቆይ የርሃብ አድማ መጀመራቸውን መግለፃቸው ይታወቃል።
( ስንታየሁ ቸኮል )
 

News in Pictures

Time in Ethiopia

Multi threaded Redundant Dedicated Server in USA and in Europe.