ከዛሬ ጀምሮ ወደ አማራ ክልል የሚገባ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እንደማይኖር የክልሉ መንግሥት አስታወቀ።
ባሕር ዳር ፡ መጋቢት 20/2012 ዓ.ም (አብመድ) ከአገሪቱ ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ አማራ ክልል የሚገቡ ማንናቸውም ዓይነት የሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ከዛሬ መጋቢት 20/2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ጀምሮ ወደ ክልሉ መግባት የማይችሉ መሆኑን የአማራ ክልል መንግሥት የኮረና ወረርሽኝ መካላከል ኮማንድ ፖስት አስታውቋል።
ከዩኒቪርስቲ ወደ ቤተሰቦቻቸው እየመጡ የሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጅ ተማሪዎች ግን በልዩ ሁኔታ የሚገቡ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ገልጿል።
ይህ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆንም ለፀጥታ አስከባሪ ኃይል ተዕዛዝ ተሰጥቷል።